ክፍለ ጊዜ 1/21

ገጽ 4/5: ርዕስ ለ፡- በፕሮግራሙ ውስጥ የመጀመሪያው መልመጃ

ርዕስ ለ፡- በፕሮግራሙ ውስጥ የመጀመሪያው መልመጃ፡- ስለ መቀራረብ እና ስለ መለያየት ያላችሁ የግል ዕውቀት

ህጻናት ከተንከባካቢያቸው ጋር መለያየት በሚደርስባቸው ወቅት የሚያሳዩትን ባህሪ በተመለከተ አስቀድሞ ያላችሁን ጠቃሚ ዕውቀት እንድታውቁት የሚረዳችሁ በዚህ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ያለው የመጀመሪያው መልመጃ ነው። ይህም የአደራ ቤተሰብ ልጆችን ለመረዳት እና ከአደራ ቤተሰብ ልጆች ጋር የተያያዘ ሥራ ለመሥራት እንዴት የህይወት ተሞክሮዎቻችሁን እንደ ግብዓት መጠቀም እንደምትችሉ ለማወቅ ይረዳችኋል።
በአደራ ቤተሰብ ወላጆቹ መካከል ወይም በአደራ ቤተሰብ ወላጆቹ እና በተቆጣጣሪው( የስራ መሪው) መካከል የሚደረጉ ቃለ መጠይቆች፡-
• የቃለ መጠይቁ ዓላማ በልጅነታችሁ (በማደግ ላይ እያላችሁ) አስፈላጊ ከሆኑ ሰዎች ጋር ስለ መቀራረብ ምን ምን እንደምታውቁ እንዲሁም በልጅነታችሁ (በማደግ ላይ እያላችሁ ) መለያየት ሲያጋጥማችሁ በምን መልኩ እንዳስተናገዳችሁት ማወቅ ነው። በተጨማሪም እያንዳንዱ የአደራ ቤተሰብ ወላጅ በህጻናት እንክብካቤ ባለሞያነት በሚሠራበት/በምትሰራበት ወቅት የራሱን/የራሷን የልጅነት ተሞክሮ መጠቀም ስለሚችልበት/ስለምትችልበት መንገድ መወያየት ነው።
• አንድ ተሳታፊ ለሌላ ተሳታፊ ለ20 ደቂቃ ቃለ መጠይቅ ያደርጋል።

• ከዚያም ቦታ ይቀያየሩ እና ሌላኛው ሰው ቃለ መጠይቅ ያደርጋል።

ቃለ መጠይቆቹ ከተደረጉ በኋላ ስላላችሁ ዕውቀት እርስ በእርስ ትወያያላችሁ።

በቀላሉ ጥያቄዎቹን ጠይቁ እና መልሶቹን አዳምጡ። እባካችሁ መልስ በመስጠት ላይ ያለውን ሰው አታቋርጡ በጥሞና አዳምጡ። .

ቃለ መጠይቅ
የህይወታችሁ መጀመሪያ፡-

    • እናትዎ እርስዎን ነፍሰጡር በነበሩበት ወቅት ወላጆችዎ ምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ነበሩ (የሚኖሩት የት ነበር፣ ስንት ዓመታቸው ነበር፣ ስንት ልጆች ነበሯቸው)?

    • የእናትዎ እርግዝና እና እርስዎ የተወለዱበት ሁኔታ ምን ይመስል እንደነበር ያውቃሉ? (ወላጆችዎ ስለዚያ የሚያወሩት ታሪክ ነበረ?

    • ተወልደው 3 ዓመት እስኪሞላዎት ድረስ የተንከባከበዎት ማን ነበር?
    • በባህላችሁ መሠረት ለህጻናት እንክብካቤ የሚሰጥበት ባህላዊ መንገድ ምን ዓይነት ነው?

    • ወላጆችዎ እርስዎን ስለተንከባከቡበት መንገድ በጣም ምርጥ የሚሉት ነገር ምንድን ነው?

    • ይህ ስለ ቤተሰብ ህይወት ምን እሴቶችን ሰጥቶዎታል?
    • ከወላጅዎ ወይም ከተንከባካቢዎ ጋር ካሳለፉት የልጅነት ጊዜ የሚያስታውሱት በጣም የመተማመን እና የምቾት ስሜት የፈጠረብዎት ሁኔታ ምንድን ነበር?
    • ለመጀመሪያ ጊዜ እንደከበደዎት የሚያስታውሱት ለረጅምም ይሁን ለአጭር ጊዜ ከማን ጋር ሲለያዩ ነበር?
    • በምን መልኩ አስተናገዱት- ምን አሰቡ፣ ምን ተሰማዎት፣ ምን አደረጉ?
    • ይህን መለያየት ለመቋቋም በምን መልኩ ጥረት አደረጉ -ምን አሰቡ፣ ምን ተሰማዎት፣ ምን አደረጉ? (በተንከባካቢዎ ተናደዱ?፤ “ውስጥዎ በረዶ ሆነ?”፤ ረስተውት እና ችላ ብለውት ህይወትዎን ለመቀጠል ሞከሩ?፤ ሀዘን ተሰማዎት?)

    መለያየት በከበደዎት ጊዜ እንዲረሱት ለመርዳት ብለው አዋቂዎች ካደረጉልዎት ነገሮች ውስጥ በጣም የረዳዎት ምን ነበር?

Your professional development:
• በአደራ ስለሚያሳድጉት/ጓት ልጅ ምን ይሰማዎታል?

• በዕለት ተዕለት ሥራዎ ውስጥ በጣም አስደሳች እና በጣም አስቸጋሪ የሚሆንብዎት ምንድን ነው?

• ልጁ/ልጅቷ ካሉበት/ካሉባት ችግሮች ውስጥ ከራስዎ ልጅነት የሚያስታውሱት አለ? ይህ ግንዛቤ ከልጁ/ከልጅቷ ጋር በተያያዘ የሚሠሩት ሥራ ላይ በምን መልኩ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል?
• የተሻለ የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ባለሞያ ለመሆን እርስዎ ሊሰሩበት የሚገባው በጣም ወሳኝ ነገር ምንድን ነው ብለው ያስባሉ?

• ባለቤትዎ/ተቆጣጣሪዎ/የስራ መሪዎ/ በዚህ ዕድገት ውስጥ እርስዎን ለመደገፍ ምን ማድረግ ይችላሉ?