ክፍለጊዜ 3/21

ገጽ 2/6፡- አንድ ህጻን የአደራ እንክብካቤ ቤተሰብ ውስጥ ሲመደብ መጀመሪያ ላይ ምን ይሰማዋል? የሽግግር ጊዜውን መገንዘብ

አንድ ህጻን የአደራ እንክብካቤ ቤተሰብ ውስጥ ሲመደብ መጀመሪያ ላይ ምን ይሰማዋል? የሽግግር ጊዜውን መገንዘብ

ህጻኑ ወደ አደራ ቤተሰቡ ሲመጣ እና ስትገናኙ ለሚኖረው ሁኔታ መዘጋጀት አለባችሁ ምን አልባትም አዲሱ ቤተሰብ እንዲመቸው ህጻኑን ለማገዝ ያሏችሁን ክህሎቶች በሙሉ የምትጠቀሙበትን ዕድል ለማግኘት በጉጉት ልትጠብቁ ትችላላችሁ።

ወደ አደራ ቤተሰቡ ለመጀመሪያ ጊዜ መምጣት ከአደራ ቤተሰቡ በበለጠ ሁኔታ ለህጻኑ በጣም ከባድ እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል፡- ምን አልባትም የሚረብሹ ክስተቶች እና ግራ መጋባቶችን አሳልፎ ሊሆን ይችላል፤ በተለይም ደግሞ ህጻኑ ከወላጆቹ የተወሰደው ከፈቃዳቸው ውጭ ከሆነ። ህጻኑ በሚገባ ተዘጋጅቶ የነበረ ቢሆንም እንኳን በሌላ መተካት ለህጻናት ከባድ ነገር ስለሆነ የአደራ ቤተሰቡ ውስጥ የደህንነት ስሜት እስኪሰማው ድረስ ብዙ ጊዜ ወስደው ምቾት እንዲሰማው ማድረግ ያስፈልጋል።

እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነገር፡- ቤተሰብን ማጣት እና ከዚያ ጎን ለጎን ደግሞ ከሌላ ቤተሰብ ጋር መገናኘት
የሚከተለው ታሪክ አንዲት በአደራ ቤተሰብ ውስጥ ያለች የአሥር ዓመት ልጅ በአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ውስጥ ስላሳለፈችው የመጀመሪያ ዓመት ላይ ይሰማት ስለነበረ ስሜት ነው። በወቅቱ ልጅቱ ስድስት ዓመቷ ነበር፡-

“ምንም እንኳን ለእኔ ሩህሩህ የነበሩ ቢሆንም ለእኔ አዲስ ስለነበሩ ብቻ (የአደራ ቤተሰቦቼን) በጣም አልወደድኳቸውም ነበር። እናቴ እና ጓደኞቼ ሁል ጊዜ ይናፍቁኝ ነበር፤ እና የአደራ ወላጆቼ ለእኔ ጥሩ ነገር ባደረጉልኝ ቁጥር እናቴን ነበር የሚያስታውሰኝ ። በጣም መጥፎ ልጅ ብሆን ነው የወሰዱኝ ብዬ አስብ ነበር። ክፍሉ አዲስ ነበር እንዲሁም ቤታቸው ያልወደድኩት የተለየ ሽታ ነበረው። ስጀምር በጣም ፈርቼ ስለነበር ሳያዩኝ በጣም አለቅስ ነበር፤ እንዲያውም አንድ ጊዜ ለመጥፋት ሞክሬ የነበረ ቢሆንም በየትኛው አውቶብስ መሳፈር እንዳለብኝ ማወቅ ስላልቻልኩኝ ተመልሼአለሁ። አንድ ነገር ሲሰጡኝ እናቴ ያንን ነገር ለመግዛት አቅሙ ስላልነበራት ነው የወሰዱኝ ብዬ አስብ ስለነበር ተከፍሏችሁ ነው እኔን የምትንከባከቡኝ እንጂ ምንም አትወዱኝም ብዬ እጮህባቸው ነበር። እንደዚያ ማለቴ በጣም ያሳዝናቸው ስለነበር እኔም አሳዘንኳቸው ብዬ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማኝ ነበር፤ ነገር ግን ያንን የማደርገው ስለወሰዱኝ በጣም እናደድ ስለነበረ ነው። ከወደድኳቸው እናቴ ትናደድብኛለች ብዬ እፈራ ነበር። ጓደኞቼ እና እናቴ እኔን ከነጭራሹ ረስተውኛል ብዬ አስብ ሰለነበር (የአደራ ቤተሰቦቼ) ወደድሮው ቤቴ ሲወስዱኝ እና ለጓደኞቼ ደብዳቤ እንድጽፍ ሲያግዙኝ በጣም ደስ ብሎኝ ነበር። አሁን በጣም እንደሚወዱኝ አውቃለሁ፤ እና አንዳንድ ጊዜ መጀመሪያ ላይ እዚህ መኖር ስጀምር እንዴት መጥፎ ባህሪ አሳይ እንደነበረ እያወራን እንስቃለን…”
ይህ ታሪክ አንድ ህጻን የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ውስጥ ሲገባ መጀመሪያ ላይ ከአዲሱ አካባቢ ጋር ራሱን ለማላመድ በሚሞክርበት ወቅት እንዴት የመደናገጥ፣ የከባድ ሀዘን እና ግራ የመጋባት ሁኔታ ውስጥ እንደሚሆን የሚያሳይ ነው።

ህጻኑ የእውነት እርስ በእርሱ የሚጋጭ እና የተቃወሰ ሁኔታ ውስጥ ነው የሚሆነው -ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸውን ሰዎች አጥቶ በዚህ የመለያየት ስሜት ውስጥ እያለ ወላጅ ሊሆኑት እና ሊቀርቡት የሚፈልጉ ሰዎችን መልመድ ይኖርበታል። ከአንድ ሥራ ያለምንም ማብራሪያ ብትባረሩ እና ከዚያ እየወጣችሁ እያለ ተመሳሳይ ሥራ ላይ ሊቀጥሯችሁ የሚፈልጉ ሁለት በጣም አዎንታዊ አመለካከት ያላቸው ሰዎች አገኛችሁ እንበል – ታምኗቸዋላችሁ? ላታምኗቸው የምትችሉበት ሰፊ ዕድል አለ…

በቀጣዮቹ ክፍለ ጊዜዎች (“መለያየትን ወደ ጽናት መቀየር” እና “እኔ ማን ነኝ?”) ሰውን ስለ መላመድ እና ህጻናት መለያየትን ስለሚያስተናግዱበት መንገድ ተጨማሪ ብዙ ነገሮችን ትማራላችሁ። በዚህ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ያሉት ቀጣይ ርዕሶች ህጻኑ ከቀድሞ ተንከባካቢዎቹ ወደ እናንተ እንክብካቤ በሚሸጋገርበት ወቅት የሚያሳያቸውን ባህሪዎች ከመጀመሪያው ጀምሮ ማስተናገድ እንድትችሉ ያዘጋጇችኋል።

Watch this video with Saleh, who grew up in a SOS Children’s Village in Tanzania. He shares some of his experience with missing his family and having a secure relationship to his SOS-mother, with whom he is able to share and discuss everything that comes to his mind.