ክፍለ ጊዜ 3/21

ገጽ 6/6፡- የሥራ ዕቅድ፡- ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት የሚሠሩ ሥራዎች

የሥራ ዕቅድ፡- ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት የሚሠሩ ሥራዎች

ሥራችሁን እንዴት እንደምትሰሩ የሚገልጽ ዕቅድ አዘጋጁ፡-
• እባካችሁ የሚቀጥለውን ክፍለ ጊዜ ከመጀመራችሁ በፊት ሥራችሁን እንዴት እንደምትሰሩ የሚገልጽ ዕቅድ ጻፉ።
• ከህጻኑ ጋር በተያያዘ የምትሠሩትን ሥራ በትዕግስት እና ሁኔታውን በመቆጣጠር መሥራት የምትችሉት እንዴት ነው?

• ህጻኑ ደህንነቱ እንደተጠበቀ እንዲሰማው እና እንዲረጋጋ እንዲሁም ከዕለት ዕለት የማይቀያየር እና ለመገመት ቀላል የሆነ ዓለም ውስጥ እንደሚኖር እንዲሰማው የሚያደርጉ የዕለት ተዕለት ፕሮግራሞችን እና እንቅስቃሴዎችን ማዘጋጀት የምትችሉት እንዴት ነው?
• ለማሻሻል የምትክሯቸውን አሠራሮች ዝርዝር አዘጋጁ እንዲሁም ምን እንቅስቃሴዎችን/ የትኛው የቀን ሠዓት ላይ እንደምታከናውኑ አስቀምጡ።

• እባካችሁ በኋላ ላይ ተመልሳችሁ ልታዩአቸው እንድትችሉ እና ህጻኑ ሲያድግ እንደ ማስታወሻ እንዲሆነው ከእነዚህ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አንዳንዶቹን እንዴት በቪዲዮ እንደምትቀርጹ አቅዱ።

ለፍላጎትዎ እናመሰግናለን እና እስከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ድረስ በስራዎ መልካም ዕድል!