ክፍለ ጊዜ 6/21

ገጽ 2/4 ርዕስ ሀ፡- ተግባራት ላይ እና ግንኙነቶች ላይ የሚሠራ ሥራ

ርዕስ ሀ፡- ተግባራት ላይ እና ግንኙነቶች ላይ የሚሠራ ሥራ

ህጻናት ከእንክብካቤ ሰጪዎች ጋር እንዴት ትስስር መፍጠር እንዳለባቸው፣ ከእነሱ ጋር በጣም ቅርበት እንዲሰማቸው ማድረግ እንዳለባቸው፣ ነገሮችን እንዴት ማድረግ እንዳለባቸው እና ከሌሎች ጋር እንዴት መስተጋብር ማድረግ እንዳለባቸው ከእናንተ መማር አለባቸው።እንዴት ሰው የሚቀርቡ ሰዎች መሆን እንዳለባቸው የሚማሩት እናንተ በግንኙነቶች ዙሪያ ያሉ ሥራዎችን ከምታከናውኑበት  መንገድ ነው። ከዚህ አንጻር እናንተ የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ሰጪዎች እንደመሆናችሁ መጠን ከራሱ ቤተሰብ ውጭ በተመደበው ህጻን ህይወት ውስጥ ትልቁን ቦታ የምትይዙ ሰዎች ናችሁ። የሚያስተምሯቸው ወላጆች የሏቸውም፤ ስለዚህ ሊያስተምሯቸው የሚችሉት የአደራ ቤተሰብ ወላጆቻቸው ናቸው።

ከወላጆቻቸው ሊማሩ ይገባቸው የነበሩ ነገሮችን አሁን የግድ ከእናንተ መማር አለባቸው። ይህ ኃላፊነት አንዳንድ ጊዜ ሸክም ሊሆን ቢችልም ስጦታም ጭምር ነው፡- ከተሳካላችሁ ለህጻኑ አስተማማኝ የሆነ መሰረት (ለህይወቱ አዎንታዊ መሠረት) ሰጥታችሁታል ማለት ነው። 

በርካታ ህጻናትን መንከባከብ ያለባችሁ ከሆነ ይህን ማድረግ በተጨባጭ ቀላል አይደለም፤ ስለዚህ ሥራውን እንመልከት።

ከህጻናት ጋር የተያያዘ ሥራ በምትሰሩበት ወቅት ሁል ጊዜም የምትሰሩት ሁለት የተለያዩ ሥራዎችን ነው። በርካታ ተጨባጭ ነገሮችን ትሰራላችሁ፡- ከህጻናቱ ጋር እንቅስቃሴዎችን ማዘጋጀት፣ ልብስ ማልበስ፣ ማስተኛት፣ ማጠብ፣ ዳይፐራቸውን መቀየር፣ ወዘተ። ይህም የህጻኑን ፍላጎቶች (ምግብ፣ እንቅልፍ፣ እንቅስቃሴዎች) ለማሟላት እና በቀን ውስጥ ለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መደበኛ ፕሮግራም ለመከተል አስፈላጊ ነው። ይህን ሁሉ በምታደርጉበት ወቅት ግንኙነት ላይ መስራትንም እንዲሁ ተግባራዊ ታደርጋላችሁ፡- ልብስ በምታለብሱበት ወቅት ከዚያ በተጨማሪ ህጻኑን ታናግራላችሁ፣ ለህጻኑ ምላሽ ትሰጣላችሁ፣ የህጻኑን ትኩረት ታገኛላችሁ፣ ፈገግ ብላችሁ ህጻኑን ትደባብሳላችሁ፣ ወዘተ። ይህም ህጻኑ መተማመን እንዲሰማው፣ ቅርርብን ለማጠናከር እንዲሁም በአጠቃላይ ማህበራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ትምህርት እንዲያገኝ አስፈላጊ ነው።

ቪዲዮውን ተመልከቱ እና ተጨባጭ ሥራ በምትሰሩበት ወቅት እንዴት ከህጻናቱ ጋር መስተጋብር ማድረግ እንደምትችሉ ተወያዩ

ጥያቄዎች

  • እናንተ ትልቅ ቦታ የምትሰጡት ወይም ዋናው ነገር ምንድን ነው (በአደራ ቤተሰብ እንክብካቤያችሁ ውስጥ በተግባራት ላይ የሚሠራ ሥራን እና በግንኙነቶች ላይ የሚሠራ ሥራን አመጣጥናችሁ የምታስኬዱት እንዴት ነው)?
  • በራሳችሁ ቤተሰብ ውስጥ ተግባራትን እና ግንኙነትን አመጣጥናችሁ የምታስኬዱት እንዴት ነው? ወላጆቻችሁ ይህን የሚያደርጉት እንዴት ነበር?
  • በአደራ ቤተሰብ እንክብካቤአችሁ ውስጥ ያላችሁን ዓይነት ሚዛን ሊኖራችሁ የቻለው ለምንድን ነው (ምክንያቱ “ሁል ጊዜም የማደርገው እንደዚህ ነው”፣ “በጣም ሥራ ይበዛብኛል” ነው)?
  • ተግባር ላይ እና ግንኙነቶች ላይ የሚሠሩ ሥራዎችን አመጣጥኖ ከማስኬድ ጋር በተያያዘ በየቀኑ የሚያጋጥሟችሁ ችግሮች ምንድን ናቸው?
  • “ለአንድ ህጻን ጊዜ እና ትኩረት መስጠት” እና “ለሁሉም ህጻናት ጊዜ እና ትኩረት መስጠት” የሚሉትን ነገሮች አመጣጥናችሁ የምታስኬዱት በምን መልኩ ነው? ብዙ ህጻናት ሲኖሯችሁ ለአንድ ልጅ ምን ያህል ትኩረት መስጠት እንዳለባችሁ እና ለሁሉም ህጻናት ምን ያህል ትኩረት መስጠት እንዳለባችሁ መወሰን ሁል ጊዜም አስቸጋሪ ነው።
  • ተጨባጭ ተግባራትን ከማከናወን ጎን ለጎን በተቻለ መጠን ከግንኙነቶች ጋር የተያያዙ ብዙ ሥራዎችን ለመስራት ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ግንዛቤ የመገምገሚያ ነጥቦች

  • ወላጆቻቸውን ባጡ ህጻናት ህይወት ውስጥ በጣም ትልቁን ቦታ የሚይዙት እንክብካቤ ሰጪ ባለሞያዎች የሆኑበት ምክንያት ምንድን ነው?
  • ተግባራትን በማከናወን ሥራዎች ላይ በምታተኩሩበት ወቅት ምን አስፈላጊ ነው?
  • ከግንኙነቶች ጋር በተያያዙ ሥራዎች ላይ በምታተኩሩበት ወቅት ምን አስፈላጊ ነው?
  • ሁለቱንም በአንድ ጊዜ ማድረግ ምን ይከብዳል?

ርዕስ “ለ”ን ከመጀመራችሁ በፊት አንዳንድ የሚመከሩ መልመጃዎችን ከፈለጋችሁ “አሁን ማድረግ የምንችላቸው ነገሮች” የሚለውን ተመልከቱ። የሚከተለውን አስተውላችሁ ጻፉ ወይም ሞባይል ስልካችሁን ወይም ካሜራችሁን በመጠቀም ቅረጹ፡- የዕለት ተዕለት ተጨባጭ ተግባራትን የምታከናውኑበትን መንገድ። ቪዲዲውን ተመልከቱ እና ተጨባጭ ሥራዎችን በምትሰሩበት ወቅት እንዴት ከህጻናቱ ጋር መስተጋብር ማድረግ እንደምትችሉ ተወያዩ። በቀን ውስጥ የተለያዩ ሁኔታዎች ላይ አንዳንድ ጊዜ ተጨባጭ ሥራዎችን እንዴት በጣም አስፈላጊ ሆነው ልታገኟቸው እንደምትችሉ እና አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እንዴት ከግንኙነት ጋር በተያያዘ የሚሠሩ ስራዎችን በጣም አስፈላጊ ሆነው ልታገኟቸው እንደምትችሉ ተወያዩ።

“ህጻናትን በማስተናገድ እና አንድን ተግባር በማከናወን መካከል መምረጥ ትቻለሁ። በዚህ ክፍለ ጊዜ ሁለቱንም በአንድ ጊዜ ማድረግን ተምሬአለሁ። ዘና ብዬአለሁ እንዲሁም ልጄም ይዝናናል። በዚህ መልኩ አብሬአቸው ለመጫወት እችላለሁ፤ እነሱም ሊያቅፉኝ ይችላሉ። ይህን በማድረጌ ምንም ቢፈጠር አብሬአቸው እንደምሆን ያውቃሉ።”

የእንክብካቤ ሰጪ አስተያየት