ክፍለ ጊዜ 6/21

ገጽ 3/4 ርዕስ ለ፡- የአስተማማኝ እንክብካቤ ሰጪ ባህሪ የሚያካትታቸው ነገሮች

ርዕስ ለ፡- የአስተማማኝ እንክብካቤ ሰጪ ባህሪ የሚያካትታቸው ነገሮች

ከህጻናት ጋር በተያያዘ በግንኙነት ላይ በሚሠራ ሥራ ላይ በምታተኩሩበት ወቅት ከምንም በላይ ማሳየት ያለባችሁ ባህሪ ምን ዓይነት ነው?

ዋናው ነገር የምታደርጉት ነገር (ተግባሩ) ሳይሆን የምታደርጉበት መንገድ (ከግንኙነት አንጻር ያለው ጥራት) ነው።ከአንድ ህጻን ጋር መስተጋብር የምታደርጉበት መንገድ (በተለይም ደግሞ የህይወቱ የመጀመሪያ ሁለት ዓመታት ላይ) ህጻኑ መለያየትን እንዴት ማስተናገድ እንዳለበት እና ከሌሎች ሰዎች ጋር በምን መልኩ መስተጋብር ማድረግ እንዳለበት የሚማርበት የትምህርት ሂደት ነው። ይህ ትምሀርት የሚቀሰመው ከመጀመሪያ እንክብካቤ ሰጪ(ዎች) ነው እንዲሁም የህጻኑን የአቀራረብ አዝማሚያ የሚቀርጹት ትንሽ ዕድሜ ላይ ከእንክብካቤ ሰጪዎች ጋር የሚደረጉ መስተጋብሮች ናቸው።

መተማመን የሚሰማው ህጻን – መተማመን ያለበት የአቀራረብ አዝማሚያ

እንክብካቤ ሰጪዎች መተማመን ያለበት የአቀራረብ አዝማሚያን ተግባራዊ ሲያደርጉ

እንክብካቤ ሰጪዎች አስተማማኝ የሆነ ባህሪ ሲያሳዩ እንክብካቤ ሰጪው በሚሄድበት ጊዜ ህጻኑ የማዘን ሁኔታ ይኖረዋል፤ ነገር ግን ለረጅም ሰዓት አዝኖ አይቆይም። በክፍለ ጊዜ 4 ውስጥ እንዳየነው ብዙም ሳይቆይ ዳዴ ብሎ መሄድ እና በመጫወት እና በማሰስ ብዙ ጊዜ ማሳለፍ ይጀምራል።.ጥሩ እንክብካቤ ሰጪዎች ያሉት አነስተኛ ዕድሜ ላይ ያለ ህጻን መተማመን የተሞላበት የአቀራረብ አዝማሚያን ያዳብራል።ህጻኑ ዕድሜው እየጨመረ ሲመጣ ስለ ራሱ አዎንታዊ የሆነ አስተሳሰብን እንዲሁም ስለ ሰዎች፣ ህጻናት እና እንክብካቤ ሰጪዎች አዎንታዊ እና እምነት የተሞላበት አመለካከትን ያዳብራል። እገዛ ሲያስፈልገው እንክብካቤ እና እገዛን ይጠይቃል።

ከእኩዮቹ ጋር መጫወት ከመቻሉም በላይ የሆነ እንቅስቃሴ ሲሰለቸው ጓደኛውን ትቶ በመሄድ ሌሎች የጨዋታ አጋሮችን ማግኘት ይችላል። ከሌሎች እንክብካቤ ሰጪዎች ይልቅ አንዳንድ እንክብካቤ ሰጪዎችን በጣም ስለሚቀርብ የሚቀርባቸውን እንክብካቤ ሰጪዎች ይመርጣል፤ እንዲሁም ከሌሎች እኩዮቹ ይልቅ አንዳንድ እኩዮቹን በመምረጥ ከእነሱ ጋር ጓደኝነቶችን ይመሰርታል። ህጻኑ ሲያድግ ማህራዊ ግንኙነቶችን በደንብ ማስተናገድ የሚችል ከመሆኑም በላይ በትምህርት ቤቱ እና በሌሎች ተቋማት ውስጥ አቅሙ የሚፈቅደውን ያህል ለመማር ይችላል። ይህ የሚሆነው እንክብካቤ ሰጪዎች አስተማማኝ በሆነ መልኩ ከህጻኑ ጋር መስተጋብር ካደረጉ ብቻ ነው።

አስተማማኝ የሆነ እንክብካቤ አሰጣጥ ማለት ምንድን ነው?

ለህጻኑ አስተማማኝ ግንኙነትን ለመስጠት እና በህጻኑ ውስጥ በመተማመን የተሞላ የአቀራረብ አዝማሚያን ለማዳበር እንክብካቤ ሰጪዎች የሚያደረርጉትን ነገር ሳይንስ አጥንቷል። ይህን የሚያሳዩ እና የሚያብራሩ አምስት ቪዲዮዎች እና ጽሁፍ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡- 

 

እርስ በእርስ የሚደረግ መስተጋብር

አብዛኛውን ጊዜ ህጻኑ ንክኪ ሲፈልግ ምላሽ ይሰጣሉ። በተጨማሪም አብዛኛውን ጊዜ በራሳቸው ተነሳሽነት ከህጻኑ ጋር ንክኪ በማድረግ ያነቃቁታል። ዜማ ያለው ድምጽን እና ግልጽ ስሜት የሚነበብበት የፊት ገጽታን በመጠቀም የሚሰማቸውን ነገር ያሳያሉ። ህጻኑን ያነጋግሩታል እንዲሁም ከእሱ ጋር አይን ለአይን ለመተያየት ጥረት ያደርጋሉ።

ይህ ቪዲዮ በሦስት የተለያዩ ሁኔታዎች አማካኝነት “እርስ በእርስ የሚደረግ መስተጋብር” የሚያካትታቸውን ነገሮች በተግባር ያሳያል። እርስ በእርስ የሚደረግ መስተጋብር ማለት ከአንድ ህጻን ወይም ልጅ ጋር ምላሽ ሰጪ የሆነ መስተጋብር ማድረግ ማለት ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ከአንድ ጨቅላ ህጻን ጋር እንክብካቤ ሰጪዋ እንዴት አይን ለአይን እንደምትተያይ፣ ዜማ ያለው ድምጽ እንደምትጠቀም እና ህጻኑን እሹሩሩ በማለት የመረጋጋት እና የመተማመን ስሜት እንዲሰማው እንደምታደርግ አስተውሉ። በሁለተኛ ደረጃ አነስተኛ ዕድሜ ላይ ካለ ህጻን ጋር፡- እንቅስቃሴው እንዴት የራሱ ምት እንዳለው አስተውሉ። በሦስተኛ ደረጃ አንዲት እንክብካቤ ሰጪ ከወንድ ልጆቿ ጋር የምግብ ዕቅድ ስታዘጋጅ፡- እዚህ ጋር ትልቁ ነገር እንክብካቤ ሰጪዋ ልጆቹ የሚሉትን ነገር ማዳመጧ እና ትኩረት መስጠቷ ነው። በውይይቱ ውስጥ መሳተፍ እና የውይይቱ ጥንካሬ ደግሞ ሌሎች ቁልፍ የሆኑ ቃላት ናቸው።

ስሜትን ማገናዘብ

ስሜትን ባገናዘበ መልኩ ይንቀሳቀሳሉ። የሚሰሯቸው ሥራዎች አሏቸው (ህጻኑን ልጅ/ልጁን መመገብ፣ ልጁን ልብስ ማልበስ፣ መዝሙሮችን መዘመር ወይም ሌሎች ተግባራትን ማከናወን፣ ወዘተ) ነገር ግን የልጁን ስሜት “በማንበብ” ሥራዎቹን የሚያከናውኑት እንደሁኔታው በመሆን ነው፡- ህጻኑ ያዘነ ከሆነ ጫማ እያደረጉለት እያሉ ህጻኑን ያጽናኑታል፤ ህጻኑ ጫማ ማድረግ ካስደሰተው ጫማ ማድረግ ለህጻኑ ጨዋታ ይሆናል፣ ወዘተ። ስሜትን ማገናዘብ ማለት ጥብቅ ደንቦችን ከመከተል ይልቅ ህጻኑን የምታነሳሱት ከእሱ ጋር በመገናኘት እና አሁን ህጻኑ የሚሰማው ስሜት ምንድን ነው የሚለውን በመረዳት ነው ማለት ነው።

የቤት ሥራዋን መሥራት ያቃታት ህጻን ያለችበትን ይህን ቪዲዮ ተመልከቱ። እንክብካቤ ሰጪዋ የምትንቀሳቀሰው ስሜትን ባገናዘበ መልኩ ነው እንዲሁም የህጻኗን ስሜት “ታነባለች”። እንክብካቤ ሰጪዋ እንዴት ከሁኔታው ጋር ራሷን እንደምታስኬድ እና ህጻኗን በመገንዘብ እንደምትቀርባት አስተውሉ።

ለህጻኑ ተደራሽ መሆን

ህጻኑ ሊያገኛቸው ይችላል። ህጻኑ ችግር ካጋጠመው፣ ካዘነ፣ ወይም የሆነ ነገር ካስፈለገው የሚያጽናናው እና የሚያባብለው እንክብካቤ ሰጪ ከጎኑ አለ፤ ይህም አስተማማኝ መሰረት ይሰጠዋል። እንክብካቤ የሚሰጠው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወዲያውኑ እንዲሁም ህጻኑ መልሶ የመተማመን ስሜት እስከሚሰማው ነው።

በዚህ ከታንዛኒያ የተወሰደ ምሳሌ ውስጥ እናትየው ህጻናቱ እገዛ ፈለልገው ሲጠሯት እየሰራች ያለችውን ማንኛውንም ነገር ጥላ በመምጣት ለህጻናቱ ከጎናቸው እንደሆነች ታሳያቸዋለች።

የህጻኑን ስሜት መጋራት፤ እንደ ህጻኑ ግን ያለመሆን

ህጻኑ የተናደደ፣ ያዘነ ወይም በጣም የተጨነቀ ከሆነ እንክብካቤ ሰጪዋ የህጻኑን ስሜት ትጋራዋለች፤ እንደ ህጻኑ ግን አትሆንም። ምንም እንኳን ህጻኑ ቢደሰትም ወይም ቢናደድም እንክብካቤ ሰጪዋ አትደሰትም ወይም አትናደድም፤ የተረጋጋ ስሜት ውስጥ ትሆናለች እንጂ። እንክብካቤ ሰጪዋ ህጻኑን አትቆጣውም ወይም አትቀጣውም። ጥብቅ ልትሆን ትችላለች ነገር ግን እንደ ህጻኑ አትናደድም እንዲሁም ህጻኑን የምታነጋግረው ርህራሄ በተሞላበት እና በተረጋጋ መንገድ ነው። ህጻኑ ሲናደድ እንክብካቤ ሰጪዋም የምትናደድ ከሆነ ህጻኑ ይበልጥ ያለመተማመን ስሜት ይሰማዋል።

በዚህ ከታንዛኒያ የተወሰደ ምሳሌ ውስጥ ምንም እንኳን ህጻኗ የተበሳጨች እና በማማረር ላይ ያለች ቢሆንም የህጻኗ እንክብካቤ ሰጪ የተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ እንደሆነች አስተውሉ። ስሜቷን እንደምትረዳት ህጻኗ እንድትገነዘብ ታደርጋለች እንጂ አትቆጣትም ወይም አትበሳጭም። የህጻኗን ስሜት ትጋራታለች፤ እንደ ህጻኗ ግን አትሆንም። ህጻኗም ወዲያውኑ ትረጋጋ እና መጫወት ትጀምራለች።

አእምሮን መመርመር

እንክብካቤ ሰጪዎቹ ህጻኑ ምን እንደሚሰማው እና እንደሚያስብ ማወቅ ይፈልጋሉ እንዲሁም ህጻኑ የሚገኝበትን ስሜት እና የህጻኑን ሀሳብ መልሰው ለማንጸባረቅ ይሞክራሉ። ህጻኑ ቃላትን መረዳት ከመጀመሩ አስቀድመውም እንኳን ህጻኑ ምን እየተሰማው እና እያሰበ እንደሆነ ሲያሰላስሉ ህጻኑን ያነጋግሩታል።

ይህ ቪዲዮ አንድ አእምሮን የምትመረምር እንክብካቤ ሰጪን የሚያሳይ ነው። እንክብካቤ ሰጪዋ ልጁን ታዳምጠዋለች እንዲሁም የሚገኝበትን ሁኔታ እና የሚሰማውን ስሜት እንዲገነዘብ ታግዘዋለች። መጽሀፍ መጣል ምንም ማለት እንዳልሆነ እና ሁሉም ነገር ደህና እንደሚሆን በመንገር እንክብካቤ ሰጪዋ ህጻኑ የሚሰማውን ስሜት የማወቅ ፍላጎት እንዳላት ታሳያለች እንዲሁም የሚገኝበትን ሁኔታ እንዲገነዘብ ታግዘዋለች።

የመወያያ ጥያቄዎች

ከህጻናቱ ጋር የምታሳልፉትን አንድ መደበኛ የሥራ ቀን ብትመለከቱ፡- ህጻናቱ ንክኪ በሚፈልጉበት ወቅት ለህጻናቱ ምላሽ በመስጠት ላይ ለማተኮር የምትችሉት የትኞቹ እንቅስቃሴዎች ላይ ነው?

  • የእርስ በእርስ ግንኙነት፡- አንድ እንክብካቤ ሰጪ እና ሌሎች ህጻናት እርስ በእርስ ሲገናኙ (ሲዘምሩ፣ ሲጫወቱ፣ ወዘተ) ብዙ ትኩረት ሰጥታችሁ የምትመለከቱባቸው እንቅስቃሴዎች በየቀኑ አሏችሁ? ተጨባጭ ተግባራትን በማከናወን ላይ እያላችሁ ከህጻናቱ ጋር እርስ በእርስ የምትገናኙባቸውን እንቅስቃሴዎች ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው?

  • ስሜትን ማገናዘብ፡- አንድ የዕለት ተዕለት ተግባርን አስቡ እና አንድ ህጻን ማድረግ ላለበት የሆነ ነገር (መመገብ፣ ልብስ መልበስ፣ ወዘተ) የሚሰጠውን ምላሽ አስቡት። ይህን ህጻን ተግባሩን እንዲያከናውነው ለማነሳሳት ምርጡ መንገድ ምንድን ነው? የዚህን ህጻን ስሜት ከግምት ውስጥ ልታስገቡ የምትችሉት በምን መልኩ ነው (ምርጥ ውጤት የሚያስገኘው የትኛው የእንክብካቤ ሰጪ ባህሪ ነው)?

  • ለህጻኑ ተደራሽ መሆን፡- አንድ ህጻን የእኛን ትኩረት ወይም ድጋፍ የሚፈልግ ከሆነ (ከፈራ፣ ያለመተማመን ስሜት ከተሰማው፣ ህመም ከተሰማው) እገዛ ከማድረጋችን በፊት ምን ያህል መቆየት አለብን? እገዛ ለማግኘት ህጻኑ ማሳየት አለበት ብሎ እንክብካቤ ሰጪው የሚያስቀምጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች መኖር የለባቸውም፤ ህጻኑ እገዛ ካስፈለገው እገዛ ይደረግለታል። ብዙ ህጻናት ኖረው ያሉት እንክብካቤ ሰጪዎች ጥቂት ከሆኑ በተቻለ መጠን ተደራሽ እንድንሆን ይህን ችግር ለማስወገድ ምን ማድረግ እንችላለን?

  • የህጻኑን ስሜት መጋራት፤ እንደ ህጻኑ ግን ያለመሆን፡- አንድ ህጻን ምቾት በሚያጣበት፣ በሚናደድበት፣ በተደጋጋሚ በሚጨቃጨቅበት፣ በሚነጫነጭበት ወይም በሚበሰጫበት ወቅት፡- የህጻኑ ስሜት በእኛ ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ ያሳድራል እንዲሁም ምን ዓይነት ምላሽ እንድንሰጥ ያደርገናል? ራሳችን ላይ የሚኖረውን ለውጥ ማስተዋል የምንችለው እና ምንም እንኳን ህጻኑ ምክንያታዊ ባይሆንም ወይም በጣም ኃይለኛ ስሜት ውስጥ ቢሆንም መረጋጋት፣ ቆፍጠን ማለት እና ርህራሄ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? የትኞቹ ህጻናት ናቸው ሊያናድዱን እና ሊያበሳጩን የሚችሉት? አነዚህ ህጻናት የሚሰማቸው ስሜት እንዳይሰማን ልዩ ትኩረት ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? ስለ ህጻኑ ሀሳቦች እና ስሜቶች ከማሰብ ጋር ተያይዞ፡- ከህጻናቱ ጋር የተያያዘ ሥራ እየሠራን እያለ ህጻናቱን ልናናግራቸው የምንችለው እንዴት ነው?

  • አእምሮን መመርመር – የህጻኑን ሀሳቦች እና ስሜቶች መልሶ ማንጸባረቅ፡- ህጻናትን ስለራሳቸው ሀሳቦች እና ስሜቶች ልናነጋግራቸው እና ሌሎች ሰዎች የሚያስቡትን ነገር እና የሚሰማቸውን ስሜት እንዲገነዘቡ ልናሰለጥናቸው የምንችለው እንዴት ነው? አብራችኋቸው ሥራዎችን እየሰራችሁ እያላችሁ ህጻናትን ማነጋገር የምትችሉት እንዴት ነው? ለምሳሌ፡- ከአንድ ህጻን ጋር አንድ ተግባር በምታከናውኑበት ወቅት ከዚያ በተጨማሪ ህጻኑ ላይ ስለምታዩት ነገር ማውራት፡- “አሁን ደግሞ በዚህ አሻንጉሊት ልትጫወት ነው፤ ይህን አሻንጉሊት ከዚህ በፊት አይተኸው ስለማታውቅ ትንሽ እንደፈራኸው አይቼአለሁ፤ አይዞህ አብረን እንመልከተው” ወይም “አሁን ጡጦህን እየጠባህ ነው፤ በጣም ርቦሀል፤ ጡጦ መጥባት በጣም ደስ ይላል፤ ደስተኛ ያደርግሀል፤ አይደል?”፣ ወዘተ። .

የሚመከሩ መልመጃዎች
  • ከህጻናት ጋር መስተጋብር የምታደርጉባቸውን መንገዶች እንዴት ማሻሻል እንደምትችሉ ተወያዩ (እርስ በእርስ መገናኘት፣ ስሜትን ማገናዘብ፣ ወዘተ)።
  • የዕለት ተዕለት ምሳሌዎችን ፈልጋችሁ ከግንኙነቶች ጋር በተያያዘ የምትሰሩት ሥራ ላይ እንዴት ማሻሻያዎችን ማድረግ እንደምትችሉ ተወያዩ።
  • ግንኙነቶች ላይ ከሚሰራ ሥራ ጋር በተያያዘ በተለይ ምን ችግሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተወያዩ (“በጣም ሥራ ይበዛብኛል፣ አዲስ ነገር ማድረግ ከባድ ነው፣ በጣም ብዙ ህጻናት ናቸው ያሉት እና እኔ ደግሞ ብቻዬን ነኝ”፣ ወዘተ) እና ከእነዚህ ችግሮች ውስጥ አንዳንዶቹን እንዴት ማስወገድ እንደምትችሉ ተወያዩ።
  • የሚከተሉት ያለፈባቸው አሉታዊ አመለካከቶች እንዴት የአስተማማኝ እንክብካቤ ሰጪ ባህሪያትን ተግባራዊ እንዳታደርጉ እንቅፋት ሊሆኑባችሁ እንደሚችሉ ተወያዩ፡-
    • “ወላጆቼ ሁል ጊዜ ይቆጡኝ ነበር፤ በሥራዬ ላይ ይህን እንዳላደርግ መከላከል የምችለው እንዴት ነው?”
    • “የአደራ እንክብካቤ ሰጪዎች እንደመሆናችሁ መጠን ከህጻናቱ ጋር የግል ግንኙነት ሊኖራችሁ አይገባም።”
    • “ይሄን ሁሉ ለማድረግ ጊዜው እና ጉልበቱ የለንም።”
    • “ህጻናቱ እኔን በጣም መቅረብ ከጀመሩ ትቼአቸው ስሄድ ያዝናሉ  እኔም አዝናለሁ።”

እነዚህ አመለካከቶች በሙሉ በውስጣቸው የያዙት የተወሰነ እውነት አለ፤ ነገር ግን ልታስወግዷቸው ይገባል ምክንያቱም ለህጻን ልጅ ዕድገት ጥሩ አይደሉም። አዎን፣ ከራሳችሁ ወላጆች ጥሩ እንክብካቤ ያላገኛችሁ ከሆነ ጥሩ እንክብካቤ ሰጪ መሆንን የግድ መለማመድ የሚኖርባችሁ ቢሆንም ያንን ማድረግ ትችላላችሁ።

ከህጻናት ጋር የግል ግንኙነቶችን መመስረት እና በጣም እንዲቀርቧችሁ መፍቀድ እንዲያውም በጣም አስፈላጊ የሆነ የአደራ እንክብካቤ ሰጪው ሥራ ነው።

አዎን ህጻናት በጣም እንዲቀርቧችሁ ከፈቀዳችሁላቸው ስትሄዱ ያዝናሉ፤ ነገር ግን ይህ የህይወት አንድ አካል ስለሆነ ከእንክብካቤ ሰጪ ጋር የግል ግንኙነት መመስረትን ፈጽሞ ሳይማሩ ከሚቀሩ በጣም ይሻላቸዋል። የቅርብ ግንኙነት ለማንኛውም ህጻን ከፍተኛ ዋጋ ያለው ነገር ነው።

መወያያዎች

የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻችሁን በአዲስ መልኩ በማደራጀት ከግንኙነቶች ጋር የተያያዙ ሥራዎችን መሥራት ሰለምትችሉበት መንገድ ፡-

ልጆቻችሁ የት እና መቼ ሊያገኟችሁ እንደሚችሉ እንዲያውቁ ምን አልባት ሥራችሁን አዲስ እና ይበልጥ ቀልጣፋ በሆነ መንገድ መከፋፈል ትችሉ ይሆናል።
ልጆቻችሁን ልታካትቱ የምትችሉባቸው ተጨማሪ የዕለት ተዕለት ተግባራት ይኖሩ ይሆን?