ክፍለ ጊዜ 6/19

ገጽ 1/4 ሞያዊ እንክብካቤ አሰጣጥን መለማመድ የሚቻልበት መንገድ፡- ሰውን በጣም የመቅረብ አዝማሚያዎች
ሞያዊ እንክብካቤ አሰጣጥን መለማመድ የሚቻልበት መንገድ፡- ሰውን በጣም የመቅረብ አዝማሚያዎች
ልምምድየሚደረግባቸውችሎታዎች፡

 

ተግባራትን ለማከናወን በሚሠሩ እና ግንኙነቶችን ለመገንባት በሚሠሩ ሥራዎች መካከል ቀጣይነት ባለው መልኩ ሚዛን ስለመጠበቅ ግንዛቤ ማግኘት

ሞያን በተላበሰ መልኩ የአስተማማኝ እንክብካቤ ሰጪ ባህሪን ተግባራዊ የማድረግ ክህሎቶች።

የአስተማማኝ እንክብካቤ ሰጪ ዘይቤ ምን እንደሆነ ማወቅ እና ተግባራዊ ማድረግ

የክፍለጊዜውጭብጥ፡

በክፍለ ጊዜ 4 ውስጥ ሰውን በጣም የመቅረብ ባህሪን በመገንዘብ እና እንክብካቤ ሰጪዎች ለህጻናት አስተማማኝ መሠረት ሊሰጧቸው በሚችሉበት መንገድ ላይ ሰርታችኋል። በዚህ የስልጠና ክፍለ ጊዜ ውስጥ ደግሞ የአስተማማኝ እንክብካቤ ሰጪ ዘይቤን እና ህጻናት እንክብካቤ ሲሰጣቸው ምን ዓይነት ምላሽ እንደሚሰጡ በዝርዝር ታጠናላችሁ። ህጻናት ደህንነት/ምቾት/ ተሰምቷቸው ከሰዎች ጋር መስተጋብር እንዲያደርጉ፣ እንዲጫወቱ እና እንዲማሩ እንክብካቤ ሰጪዎች ምን ዓይነት ባህሪ ነው ማሳየት ያለባቸው? በተጨማሪም ህጻናት መለያየትን ስለመቋቋም የሚማሩት በጣም በትንሽ ዕድሜአቸው ነው። እያንዳንዱ ህጻን መለያየትን እና ከዚያ የሚመነጨውን ጭንቀት ለመቋቋም የሚረዱ ዘዴዎችን የሚማረው ከመጀመሪያ እንክብካቤ ሰጪዎቹ ነው። በመሠረቱ ህጻናት አራት የመቋቋሚያ መንገዶች አሏቸው (እነዚህ ዘዴዎች የአቀራረብ አዝማሚያዎች ተብለው ይጠራሉ)። እነዚህን አዝማሚያዎች መለየትን ትማራላችሁ እንዲሁም ከህጻኑ ጋር በሚኖራችሁ መስተጋብር ውስጥ ምላሽ መስጠት የምትችሉበትን መንገድ የተመለከተ ምክር ታገኛላችሁ።

 

የክፍለጊዜውዓላማዎች፡

የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋነኛ ዓላማ ሞያዊ እንክብካቤን ተግባራዊ ማድረግ ስለሚቻልበት መንገድ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው።
ለምን እና እንዴት፡-

ሞያን የተላበሰ እንክብካቤ ከህጻኑ ጋር በሚኖር የስነ-ልቦና እና ማህበራዊ ግንኙነት ላይ ያተኩራል። ከዚህ ጎን ለጎን ብዙ ተጨባጭ ሥራዎችን መሥራት ይኖርባችኋል፡- ዳይፐር መቀየር፣ ምግብ ማዘጋጀት፣ ህጻናቱን መመገብ፣ ወዘተ። በተጨማሪም ከግንኙነት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን እና የተጨባጭ ተግባራት ሥራን ማመጣጠን በምትችሉበት መንገድ ዙሪያ ውይይት ታደርጋላችሁ። በእንክብካቤ ሰጪ እና በህጻን መካከል ባለው ግንኙነት ውስጥ ምን ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ በዝርዝር ትወያያላችሁ።

ወደ የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ከመምጣቱ በፊት ህጻኑ ችላ መባል ወይም ነውጠኛ ወላጆችን፣ በርካታ የተለያዩ እንክብካቤ ሰጪዎችን ወይም ሥራ የበዛባቸው እና በሥራ የዛሉ ሠራተኞችን አሳልፎ ሊሆን ይችላል። በዚህም የተነሳ በርካታ ህጻናት ለእንክብካቤ ጤናማ ምላሽ አይሰጡም እንዲሁም ጤናማ ምላሽ እስከሚሰጡ ድረስ ረጅም ጊዜ ሊወስድ ይችላል። ስለዚህ ህጻናት ለእንክብካቤ ምን ዓይነት ምላሽ እንደሚሰጡ፣ የአቀራረብ አዝማሚያቸውን እና ህጻኑ መተማመን እንዲሰማው ምን ዓይነት ምላሽ መስጠት እንደምትችሉ እናጠናለን።