ክፍለ ጊዜ 3/19

ገጽ 1/6፡- ለአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ልጅን መቀበል

ለአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ልጅን መቀበል

ልምምድ የሚደረግባቸው ችሎታዎች፡-

  • •  ህጻናት ተንከባካቢዎች ላይ ለሚኖሩ ለውጦች ምላሽ ስለሚሰጡበት መንገድ ግንዛቤ መፍጠር።

     በአደራ ቤተሰባችሁ ውስጥ ልጁ/ልጅቷ የመተማመን ስሜት እንዲሰማው/እንዲሰማት ማገዝ።

የክፍለ ጊዜው ጭብጥ፡-

በዚህ የስልጠና ክፍለ ጊዜ ህጻናት ለአዲስ ቤተሰብ እና ሁኔታ ሊሰጡ ስለሚችሉት ምላሽ እና በዚህ አዲስ ቦታ (በአደራ ቤተሰባችሁ ውስጥ) በምን መልኩ ልጁ/ልጅቷ የመተማመን ስሜት እንዲሰማው/እንዲሰማት ማድረግ እንደምትችሉ መሰረታዊ ግንዛቤ ታገኛላችሁ።

 

የክፍለ ጊዜው ዓላማዎች፡-

የዚህ ክፍለ ጊዜ ዓላማ ህጻናት አዲስ ቦታ ላይ ሲመደቡ ስለሚሰጡት ምላሽ ለእናንተ ግንዛቤ ማስጨበጥ እና የምደባውን የመጀመሪያ ወቅት ለመቋቋም የሚረዷችሁ ምክሮችን መስጠት ነው። 

በዚህ ቪዲዮ ውስጥ በታንዛኒያ የኤስ ኦ ኤስ-ፌርስታርት አሰልጣኝ የሆነችው ሁስና አንድ የአደራ ቤተሰብ ልጅ ወደ ቤተሰቡ ሲመጣ ማድረግ ስላለባቸው አቀባበል ለእንክብካቤ ሰጪዎች ቡድኗ እንዴት እንዳስተማረች ታስረዳለች። አንድን ህጻን መቀበል ለህጻኑ ብቻ ሳይሆን ለአጠቃላይ ቤተሰቡም ጭምር የሽግግር ሂደት ነው። እርስ በእርስ አንዳችን አንዳችንን መረዳት የምንችልበትን ሁኔታ እንዴት መፍጠር እንደሚቻል ሁስና በሚገባ ታስረዳለች።