የስልጠና ክፍለጊዜ 17/19

ገጽ 1/9 በማገገሚያ ማዕከላት እና በአደራ ቤተሰቦች ውስጥ

በማገገሚያ ማዕከላት እና በአደራ ቤተሰቦች ውስጥ

ከጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ጋር የተያያዘ ሥራ መሥራት

መለማመድ የሚያስፈልጉ ችሎታዎች፡-

  • ህጻናት ለምን ጎዳና ላይ ለመኖር እንደሚወስኑ መገንዘብ
  • የተለያዩ የቤተሰሰብ ግንኙነት ያላቸው ወይም የሌላቸው የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ምድቦችን ማወቅ
  • የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናትን ጥንካሬ፣ ጽናት እና ድምጽ እንዲሁም ለሰው እምነት እንደሌላቸው መገንዘብ
  • ህጻናት የመተማመን ስሜት ሲያንሳቸው የሚያሳዩአቸውን ሰውን የመቅረብ ባህርያት ማጥናት እና መገንዘብ
  • የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ለእንክብካቤ የሚሰጡትን ምላሽ እና እምነት የተሞላበት ግንኙነትን እንዴት መፍጠር እንደሚቻል ማጥናት

   

   

  የክፍለ ጊዜው ጭብጥ፡-በዚህ የስልጠና ክፍለ ጊዜ ውስጥ በመልሶ ማገገሚያ ማዕከላት እና በቤተሰብ እንክብካቤ ተመድበው ለሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ምርጥ የእንክብካቤ አገልግሎት ለመስጠት መንፈሳችሁ ይነሳሳል። አብዛኛውን ጊዜ በወላጆቻቸው እና በተንከባካቢዎቻቸው ላይ እምነት ያጡ ህጻናትን እንዴት መረዳት እና ማነጋገር እንደምትችሉ እና ከእነሱ ጋር እንዴት እምነት ያለበት ግንኙነት መመስረት እንደምትችሉ ትማራላችሁ።

  የክፍለ ጊዜው ዓላማዎች፡-

  የመልሶ ማገገሚያ ሰራተኞች፣ የአደራ ቤተሰቦች/ ዘመዶች/ ቤተሰቦች እና የኤስ ኦ ኤስ (እናቶች ከጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ምደባ ጋር በተያያዘ የሚከተሉትን ጉዳዮች እንዲገነዘቡ እና እንዲያስቡ ማገዝ፡-

  • የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናትን መረዳት እና ማክበር።
  • የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት እንክብካቤ ስንሰጣቸው ምን ዓይነት ምላሽ እንደሚሰጡ፡- የመተማመን ስሜት ሲያንስ የሚታዩ ሰውን የመቅረብ ባህርያት
  • ዘመድ ያላቸው እና የሌላቸው ህጻናት፡- ቤተሰብ የሚያስፈልገው ለማን ነው?
  • በጎዳና የግንኙነት መረባቸው ውስጥ ባሉ ሰዎች በኩል ህጻናትን ማነጋገር
  • ከመልሶ ማገገም በኋላ የአደራ ቤተሰብ ማቅረብ

   

  አባሪ፡- የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ፕሮጀክቶች ምሳሌዎች። መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚሠሩ ሌሎች ሥራዎች ማስፈንጠሪያዎች።