ክፍለ ጊዜ 5/21

ገጽ 1/5 የእንክብካቤ ሰጪ ዘይቤ እና የህጻናት የአንጎል ዕድገት

የእንክብካቤ ሰጪ ዘይቤ እና የህጻናት የአንጎል ዕድገት

..

ልምምድየሚደረግባቸውችሎታዎች፡
  • በአፍላ ዕድሜ ወቅት አካላዊ ንክኪ እና ማነቃቂያ ስለሚያስገኛቸው አዎንታዊ ውጤቶች ሳይንስ የደረሰባቸውን ግኝቶች መረዳት።
  • የአካላዊ ማነቃቂያ እንክብካቤ በዕለት ተዕለት አሠራሮች ውስጥ የሚዘጋጅበትን እና ይህም የአንጎል ዕድገትን የሚደግፍበትን መንገድ ማቀድ (በተለይም ደግሞ 0-24 ወራት ዕድሜ ላላቸው ህጻናት)።  

 

የክፍለ ጊዜው ጭብጥ፡-

የክፍለ ጊዜው ጭብጥ፡-
በዚህ የስልጠና ክፍለ ጊዜ አካላዊ ንክኪ እና ማነቃቂያ ትንሽ ዕድሜ ላይ ያሉ ህጻናት አንጎላቸው ሥራውን እንዲሠራ እና እንዲያድግ እንዴት አስፈላጊ እንደሆኑ ትማራላችሁ እንዲሁም ትገነዘባላችሁ። እንድትለማመዷቸው የምትመከሯቸው ነገሮች ይኖራሉ እንዲሁም የአንጎል ዕድገትን የሚደግፉ የዕለት ተዕለት ተግባራት ይሰጧችኋል። ከጊዜያቸው ቀድመው የተወለዱ እና በቀላሉ ሊጎዱ የሚችሉ ህጻናትን ማነቃቃት የምትችሉበትን መንገድ በተመለከተ ምክሮች ይሰጧችኋል።

 

የክፍለጊዜውዓላማዎች፡–:
የክፍለ ጊዜው ዓላማ ህጻናት ትንሽ ዕድሜ ላይ እያሉ አካላዊ ማነቃቂያ እንደሚያስፈልጋቸው እና ማነቃቂያ እንዴት አንጎልን እንደሚያሰራ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው። ገና የተወለደ ህጻን አንጎል ውስጥ ያለው የአንጎል እንቅስቃሴ አነስተኛ እና ያልተረጋጋ ነው እንዲሁም አንጎሉን ንቁ ሊያደርገው እና ሊያሳድገው የሚችለው አካላዊ ማነቃቂያ ብቻ ነው።

የአካላዊ ማነቃቂያ እና እንቅስቃሴ ማነስ በተለይም ደግሞ ለህጻናት እና ታዳጊ ህጻናት በጣም አደገኛ ነው፡- በአካላዊ ዕድገት፣ በህይወት በመቆየት ዕድል፣ በምግብ ፍላጎት እና ምግብ መፍጨት፣ በእንቅልፍ መምጣት እና መሄድ፣ በህጻኑ በሽታን እና ተውሳኮችን የመከላከል ችሎታ እንዲሁም ከተወለደ በኋላ ሰውን በጣም የመቅረብ ሥርዓቱ ሥራ በሚጀምርበት ሁኔታ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ይህን ግንዛቤ በመጠቀም የቋሚ ፕሮግራሞቻችሁ አካል ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ የዕለት ተዕለት አሠራሮችን ትማራላችሁ እንዲሁም እነዚህ አሠራሮች የአደራ ቤተሰቡ የዕለት ተዕለት ህይወት አካል መሆን ስለሚችሉበት መንገድ ትወያያላችሁ።