ክፍለ ጊዜ 20/21

ገጽ፡- 1/7 የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊዎችን እና ህጻናትን ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር መልሶ መቀላቀል – ለፕሮግራም ሥራ አስኪጆች እና ለኤስ ኦ ኤስ የተዘጋጀ መመሪያ

የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊዎችን እና ህጻናትን ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር መልሶ መቀላቀል – ለፕሮግራም ሥራ አስኪጆች እና ለኤስ ኦ ኤስ የተዘጋጀ መመሪያ

የመልሶ መቀላቀል ፕሮግራም ሥራ አስኪያጆች ይህንን እንድታነቡ በትህትና እንጠይቃለን this

 

የርዕስ መግቢያ

ይህ ክፍለ ጊዜ ከኤስ ኦ ኤስ መንደሮች ለመውጣት እና በአካባቢው ማህበረሰብ ውስጥ የማህበረሰብ አሳዳጊ ለመሆን መዘጋጀት ስለሚቻልበት መንገድ ለተለያዩ የኤስኦኤስ አሳዳጊዎች እና ለተቆጣጣሪዎቻቸው ወይም ለፕሮጀክት ሥራ አስኪያጆቻቸው ደረጃ በደረጃ የተቀመጠ ማዕቀፍ የሚሰጥ ነው። ክፍለ ጊዜው እንደ የአደራ ቤተሰብ/አሳዳጊዎች ሆነው በማህበረሰቡ ውስጥ ለመኖር ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ከመውጣታቸው በፊት፣ በሚወጡበት ወቅት እና ከወጡ በኋላ የወላጆችን እና የልጆቻቸውን የስነ-ልቦና ደህንነት እንዴት መገንባት እንደሚቻል የሚገልጹ አራት ርዕሶች አሉት፡-

ርዕስ ሀ፡ የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊዎች ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ወጥተው የማህበረሰብ አሳዳጊ ለመሆን በንቃት እራሳቸውን ማዘጋጀት የሚችሉት እንዴት ነው?

ርዕስ ለ፡ ለህጻናት መረጃ የምንሰጣቸው እና በለውጡ ውስጥ የምናሳትፋው እንዴት ነው?

ርዕስ ሐ፡ በማህበረሰቡ ውስጥ ካሉ አዋቂዎች እና እኩዮቻቸው ጋር አስተማማኝ የሆኑ አዳዲስ ግንኙነቶችን እንዲመሰርቱ ለህጻናት እና ለወጣቶች እገዛ የምናደርገው በምን መልኩ ነው?

ርዕስ መ:- ማህበረሰቡ ውስጥ ከገቡ በኋላ ተጨባጭ ክህሎቶች እንዲኖሯቸው ለህጻናት እና ለወጣቶች ስልጠና የሚሰጥበት መንገድ።

 

ልምምድ የሚደረግባቸው ብቃቶች/ችሎታዎች

  • ከኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊነት ወደ ኤስ ኦ ኤስ የማህበረሰብ አሳዳጊነት ሽግግር በሚደረግበት ወቅት ስለሚጠብቁት ነገር በግልጽ ሀሳብ መለዋወጥ።
  • በጋራ ሀሳብ ልውውጥ የሚደረግበት እና ዕቅድ የሚታቀድበት ቡድን መመስረት (ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ከመውጣት በፊት፣ በሚወጡበት ወቅት እና ከወጡ በኋላ)።
  • በሁሉም የሽግግሩ ምዕራፎች ወቅት ህጻናት ደህንነት እንዲሰማቸው ለማድረግ የሚያስችሉ ክህሎቶች።
  • በሂደቱ ውስጥ የህጻናትን መብቶች ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ክህሎቶች።

    የክፍለ ጊዜው ዓላማ

    • ይህ ክፍለ ጊዜ በጋራ ለመስራት እና በኤስ ኦ ኤስ መንደር ውስጥ ካለው ህይወት ወጥታችሁ በማህበረሰባችሁ ውስጥ የኤስ ኦ ኤስ የማህበረሰብ አሳዳጊ በመሆን አዲስ ህይወት በምትጀምሩበት ወቅት ለሚኖረው የስነ-ልቦና እና የግንኙነት ሽግግር ለመዘጋጀት የሚያግዛችሁ ይሆናል።