ክፍለ ጊዜ 4/21

ገጽ 1/5፡- ሰውን የመቅረብ መሠረታዊ ንድፈ ሀሳብን መገንዘብ፡- ለሞያዊ አሠራሮች የሚያገለግላችሁ መመሪያ

ሰውን የመቅረብ መሠረታዊ ንድፈ ሀሳብን መገንዘብ፡- ለሞያዊ አሠራሮች የሚያገለግላችሁ መመሪያ

Cልምምድ የሚደረግባቸው ችሎታዎች፡-
• ሞያን የተላበሱ የቅርርብ ባህሪያትን ተግባራዊ የማድረግ ክህሎት።

• ምን ምን እንደሚያካትት ማወቅ፡- “አስተማማኝ መሰረት መፈለግ” እና “ማሰስ” እምዲሁም ከእነዚህ ሁለት ተግባራት ጋር በተያያዘ ህጻናትን እና ታዳጊዎችን መደገፍ የሚቻልበት መንገድ።

• አስተማማኝ መሰረት የሆነ እንክብካቤ ሰጪ ባህሪ ምን ምን እንደሚያካትት ማወቅ።

የክፍለ ጊዜው ጭብጥ፡-

በዚህ ክፍለ ጊዜ ከሰው ጋር የመቀራረብ ንድፈ ሀሳብ አነስተኛ ዕድሜ ላይ ላሉ ህጻናት አስፈላጊ መሆኑን እና በዚህ ጉዳይ ላይ ያላችሁ ግንዛቤ የተቀሩትን ክፍለ ጊዜዎች በምትከታተሉበት መንገድ ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ታጠናላችሁ፡-

• የዕለት ተዕለት ግንኙነቶች እና እንቅስቃሴዎች።
• ግንኙነቶች ላይ መሥራት፣ ወዘተ።

ከሰው ጋር ስለመቀራረብ ባህሪ፣ አስተማማኝ መሠረት የሆነ እንክብካቤ ሰጪ ባህሪያት እና የማሰስ ባህሪ ትማራላችሁ።

የክፍለ ጊዜው ዓላማዎች፡-
• የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋነኛ ዓላማ እንክብካቤ የመስጠት አሰራርን ለማሻሻል እና የህጻናትን ዕድገት ለማረጋገጥ መሠረታዊ ሰውን የመቅረብ ንድፈ ሀሳብ እንዴት አስፈላጊ እንደሆነ መገንዘብ ነው።

• የተረጋጉ ወላጆች የሌሏቸው ህጻናት ከእንክብካቤ ሰጪ መለወጦች እና መተካቶች ጋር በተያያዘ በከፍተኛ ሁኔታ ለለውጦች ተጋላጭ ናቸው፤ ይህም በኋላ ላይ ሰው ከመቅረብ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ሊያስከትልባቸው ይችላል። የህጻኑ ማህበራዊ እና የስነ ልቦና ዕድገት እናንተ የእንክብካቤ ሰጪው ሰውን የመቅረብ ባህሪ ወሳኝ ስለመሆኑ ባላችሁ ግንዛቤ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የተመሰረተ ነው።

በቀጣዮቹ ክፍለ ገዜዎች ውስጥ መልካም አሠራርን በማዳበር ላይ ትሰራላችሁ።