ክፍለ ጊዜ 15/19

ገጽ 1/7 በእንክብካቤ ውስጥ ያለፉ ወጣቶችን በማህበረሰብ ውስጥ ለሚኖራቸው ህይወት ማዘጋጀት

በእንክብካቤ ውስጥ ያለፉ ወጣቶችን በማህበረሰብ ውስጥ ለሚኖራቸው ህይወት ማዘጋጀት

ልምምድ የሚደረግባቸው ችሎታዎች፡-

  • ከእንክብካቤ ወደ አዋቂነት ህይወት እና ራስን ችሎ ወደመኖር የሚደረገውን ሽግግር መረዳት
  • በምስራቅ አፍሪካ በእንክብካቤ ውስጥ ያለፉ ወጣቶች ያሉባቸውን ሦስት ዋና ዋና ተግዳሮቶች መረዳት
  • ልምድ ያላቸው በእንክብካቤ ውስጥ ያለፉ ወጣቶችን ከማዳመጥ ምን ልንማር እንችላለን?
  • ከህጻንነት ጀምሮ የዕለት ተዕለት ክህሎቶችን እና ራስን መቻልን መለማመድ
  • ከእንክብካቤ የሚወጡ ታዳጊዎችን ማዘጋጀት
  • ከእንክብካቤ በኋላ ማለማመድ እና በማህበረሰቡ ውስጥ ማካተት

 

የክፍለ ጊዜው ጭብጥ፡- በዚህ የስልጠና ክፍለ ጊዜ ውስጥ በምስራቅ አፍሪካ በእንክብካቤ ውስጥ ያለፉ ወጣቶች ከሚያጋጥሟቸው ዋና ዋና ተግዳሮቶች ጋር ትተዋወቃላችሁ። ከእንክብካቤ ከወጡ በኋላ ስለሚኖረው ህይወት ለመወያየት እና በእንክብካቤ ውስጥ ያለፉ ወጣቶችን ለዚያ ለማዘጋጀት (በማህበረሰብ ውስጥ ራሳቸውን ችለው እንዲኖሩ ከህጻንነታቸው ጀምሮ እንድታዘጋጇቸው) የሚያነሳሳ ነገር ታገኙበታላችሁ።

የክፍለ ጊዜው ዓላማዎች፡- ከእንክብካቤ ከወጡ በኋላ በማህበረሰቡ ውስጥ ለሚኖራቸው ህይወት ህጻናትን እና ወጣቶችን በማዘጋጀት ከእንክብካቤ ለሚወጡ ወጣቶች የምትሰጡትን ድጋፍ እንድታቅዱ ማገዝ። ከሚከተሉት ርዕሰ ጉዳዮች ውስጥ በአንደኛው ወይም ከዚያ በላይ ላይ ማተኮር ትችላላችሁ፡-

1. ህጻናቱን ከጨቅላ  ዕድሜያቸው ጀምሮ በክህሎቶች እና ራስን በመቻል ዙሪያ ማሰለልጠን።

2. ከእንክብካቤ የሚወጡ ወጣቶችን ማዘጋጀት።

3. ከእንክብካቤ ከወጡ በኋላ ማለማመድ እና በማህበረሰቡ ውስጥ የማካተቻ ዘዴዎች።