ክፍለ ጊዜ 19/21
ገጽ 1/5 ከመማር ሂደቱ ያገኘናቸው የሞያ ብቃቶቻችንከመማር ሂደቱ ያገኘናቸው የሞያ ብቃቶቻችን
ልምምድ የሚደረግባቸው ችሎታዎች፡-
- የአደራ ቤተሰብ ወላጆች እንደመሆናችሁ መጠን ያሳያችሁትን ዕድገት ስልታዊ በሆነ መልኩ መገምገም።
የክፍለ ጊዜው ጭብጥ፡-
በክፍለ ጊዜ 19 በዚህ ስልጠና ውስጥ በሚከተሉት አራት ዘርፎች የሠራችሁት ሥራ ያስገኘውን ውጤት ታጠናላችሁ፡-
- በአጠቃላይ የአደራ ቤተሰብ ልጁ ዕድገት እና የህጻን/እንክብካቤ ሰጪ ግንኙነት።
- ህጻናትን መንከባከብን በሚመለከተው ንደፈ ሀሳብ ዙሪያ የአደራ ቤተሰብ ወላጆች ያላቸው ብቃት።
- በአደራ ቤተሰብ ወላጆች እና በዕለት ተዕለት ማህበራዊ መረቡ መካከል ያሉ ግንኙነቶች።
- በአካባቢው ካለው ምህዳር እና ውሳኔ ሰጪዎች ጋር ያለው ግንኙነት።
የክፍለ ጊዜው ዓላማዎች፡-
ዓላማዎቹ የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤያችሁን ዕድገት ማጤን እና ስለዚያ መወያየት እና ከላይ በተጠቀሱት አራት ዘርፎች የስልጠናው መጀመሪያ ላይ የነበራችሁን የእንክብካቤ አሰጣጥ ሁኔታ አሁን ካላችሁ ሁኔታ ጋር ማነጻጸር ነው። በዚህ የፌርስታርት ስልጠና መጀመሪያ ላይ የተነሳችሁበትን ቦታ አሁን ከምትገኙበት ሁኔታ ጋር በምታነጻጽሩበት ወቅት የሚከተሉትን ጉዳዮች ከግምት ውስጥ አስገቡ፡-
-
- የአደራ ህጻናትን በመንከባከብ ችሎታችሁ ላይ ስልጠናው ምን ዓይነት ተጽዕኖ አሳድሯል?
- ይበልጥ ማህበራዊ፣ ይበልጥ ሞያን የተላበሰ ለህጻናት ይበልጥ ሞያዊ የሆነ አስተማማኝ መሰረትን መስጠት የሚችል የአደራ ቤተሰብ ፈጥራችኋል?
- እንደ ቤተሰብ ስልጠናው ያሳደረባችሁ እና የአደራ እንክብካቤአችሁ የሚያሳድርባችሁ ተጽዕኖ ምን ዓይነት ነው?
- ባል/ሚስት የሌላችሁ የአደራ ወላጅ ከሆናችሁ እባካችሁ የሚከተለውን ጉዳይ በራሳችሁ አጢኑ፡- የግል ዕድገታችሁን እና ችሎታዎቻችሁን።