ክፍለ ጊዜ 16/19

ገጽ 1/6 ለህጻን ልጅ ጤናማ ዕድገት የጨዋታ አስፈላጊነት

ለህጻን ልጅ ጤናማ ዕድገት የጨዋታ አስፈላጊነት

ልምምድ የሚደረግባቸው ችሎታዎች፡-

  • በህጻናት ጨዋታ እና አንኳር የህይወት ክህሎቶችን በማዳበር መካከል ያለውን ትስስር መገንዘብ
  • ልጆች በኋላ ላይ በህይወታቸው ውስጥ ስኬታማ እንዲሆኑ ጨዋታ ወሳኝ መሆኑን ማወቅ
  • በተደራጀ እና ባልተደራጀ ጨዋታቸው ውስጥ ህጻናትን መደገፍ
  • ጨዋታን የዕለት ተዕለት ተግባራት አንድ መደበኛ አካል አድርጎ ማካተት

 

የክፍለ ጊዜው ጭብጥ፡-

ይህ ክፍለ ጊዜ ለህጻናት ዕድገት፣ ደህንነት እና በት/ቤት እና በአዋቂነት ህይወታቸው ውስጥ ለሚያስፈልጓቸው ክህሎቶች ጨዋታ ወሳኝ መሆኑን የሚመለከት ነው።

 

የክፍለ ጊዜው ዓላማዎች፡-

ይህ ክፍለ ጊዜ ዓላማው ለህጻናት ዕድገት ወሳኝ እንደመሆኑ መጠን ጨዋታን ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዱ ሀሳቦችን ለእንክብካቤ ሰጪዎች ማቅረብ እና ማነሳሳት እንዲሁም የጨዋታ እንቅስቃሴዎችን የቤተሰብ ህይወት መደበኛ አካል አድርገው እንዲያቅዱ እና እንዲጠቀሙ የሚያስችሉ ጥልቅ ግንዛቤዎችን እና መገልገያዎችን ለእንክብካቤ ሰጪዎች መስጠት ነው። የአደራ ቤተሰቦች፣ የመልሶ ማገገሚያ ሠራተኞች፣ የኤስ ኦ ኤስ እናቶች እና የት/ቤት መምህራን ይህን ክፍለ ጊዜ ሊጠቀሙ ይችላሉ። ጨዋታ በዓለም አቀፍ ደረጃ የህጻን ልጅ ዕድገት አንድ አካል ነው!