ክፍለ ጊዜ 13/21
ገጽ 1/5 ከህጻኑ የተፈጥሮ ወላጆች ወይም ዘመዶች ጋር ተቀናጅቶ መሥራትከህጻኑ የተፈጥሮ ወላጆች ጋር ተቀናጅቶ መሥራት
አስታውሱ፡- ይህ ክፍለ ጊዜ የስጋ ዘመዶች እንክብካቤ እንዲያገኙ የሚመደቡ ህጻናትን አይመለከትም (የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ እንዲያገኙ የሚመደቡ ህጻናትን ብቻ የሚመለከት ነው)።
ልምምድ የሚደረግባቸው ችሎታዎች፡–
- ተቀናጅቶ መሥራት በአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ውስጥ ላሉ ህጻናት ዕድገት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ መገንዘብ።
- የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ውስጥ ያለን ልጅ ወላጆች ያሉበትን ሁኔታ መገንዘብ።
- በአደራ ቤተሰብ ወላጆች እና በተፈጥሮ ወላጅ(ጆች) መካከል የሚደረጉ ጥየቃዎችን የማቀድ እና ተግባራዊ የማድረግ ክህሎት።
- ከባድ ሁኔታዎችን ተቀናጅቶ በመሥራት ማስተናገድ።
የክፍለ ጊዜው ጭብጥ፡–
በዚህ የስልጠና ክፍለ ጊዜ በአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ውስጥ ካለ ህጻን የተፈጥሮ ወላጆች ወይም ዘመዶች ጋር እንዴት ተቀናጅታችሁ መሥራት እንዳለባችሁ ታጠናላችሁ።
የክፍለ ጊዜው ዓላማዎች፡-
ይህ ክፍለ ጊዜ ዓላማው በሂደቱ ውስጥ በሚሳተፉ ሰዎች መካከል በተቻለ መጠን በጣም ጥሩ ቅንጅትን ለመፍጠር ከአደራ ቤተሰብ ልጁ ወላጅ(ጆች) ወይም ሌሎች ዘመዶች ጋር በሚኖራችሁ መስተጋብር ውስጥ የምትጠቀሟቸውን ዘዴዎች መማር እና መለማመድ ነው። በአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ስር ያለው ልጅ በአደራ ቤተሰቡ እና በወላጆቹ መካከል ስምምነትን እና መከባበርን ማየት አለበት እንዲሁም ህጻኑ ከሁለቱ ቤተሰቦች ለማን ነው ታማኝ መሆን ያለብኝ የሚል ግጭት ውስጥ መግባት የለበትም።