ክፍለ ጊዜ 7/19

ገጽ 1/5 ስቃይን ወደ ጽናት መቀየር፡- ሰውን ማጣት እና መለያየት የሚፈጥሯቸውን ስሜቶች እንዲቋቋሙ ለህጻናት እገዛ ማድረግ

ስቃይን ወደ ጽናት መቀየር፡- ሰውን ማጣት እና መለያየት የሚፈጥሯቸውን ስሜቶች እንዲቋቋሙ ለህጻናት እገዛ ማድረግ

ልምምድ የሚደረግባቸው ችሎታዎች፡-

  • ሰውን ስለማጣት እና ከሰው ጋር ስለመለያየት ግልጽ ውይይቶችን የማቀድ እና ተግባራዊ የማድረግ ክህሎት።
  • የራሳችሁን የህይወት ተሞክሮዎች ምሳሌ የሚሆኑ ትርክቶች አድርጋችሁ መጠቀም የምትችሉበት መንገድ።
  • ሰውን በሚያጡበት ወቅት የሚያሳዩት ባህሪ ጤናማ ምላሽ መሆኑን እንዲገነዘቡ ለህጻናት እና ለታዳጊዎች እገዛ ማድረግ።
  • ሰውን የማጣት ተሞክሮዎች ሊፈቱ የሚችሉባቸው ተጨባጭ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የሚቻልበት መንገድ።

የክፍለ ጊዜው ጭብጥ፡- በዚህ የስልጠና ክፍለ ጊዜ ህጻናት ወላጆቻቸውን ማጣትን፣ ከወላጆቻቸው ርቀው መኖርን ወይም ከባድ ሰውን የማጣት ወይም ድንገት ከሰው ጋር የመለያየት ክስተቶችን መቋቋም እንዲችሉ መርዳት የምትችሉባቸውን መንገዶች ታጠናላችሁ።    

የክፍለ ጊዜው ዓላማዎች፡- ይህ ክፍለ ጊዜ ዋና ዓላማው ሰውን በሚያጡበት ጊዜ ስለሚኖረው የስሜት ለውጥ ከህጻናት እና ከታዳጊዎች ጋር ግልጽ እና መረጃ ሰጪ ውይይቶችን ማድረግን ለማመድ ነው። በተጨማሪም ያለወላጆቻቸው በሚኖሩበት ወቅት በህይወታቸው ውስጥ የሚኖሩትን ሁኔታዎች መቀበል እንዲችሉ የሚረዱ እንቅስቃሴዎችን መፍጠር የሚቻልባቸውን መንገዶችን መለማመድ ነው።

ማስታወሻ፡- ይህን ክፍለ ጊዜ መጀመር ያለባችሁ ክፍለ ጊዜ 2፣ 3 እና 5ን ያከናወናችሁ ከሆነ ብቻ ነው። የዚህን ክፍለ ጊዜ ይዘቶች ለመረዳት አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎች ናቸው።