ክፍለ ጊዜ 18/21
ገጽ 1/4 ህጻናትን እና ወጣቶችን በመንከባከብ ውስጥ አባቶችን ማሳተፍ - በአካባቢያችሁ ማህበረሰብ ውስጥ መሥራትህጻናትን እና ወጣቶችን በመንከባከብ ውስጥ አባቶችን ማሳተፍ – በአካባቢያችሁ ማህበረሰብ ውስጥ መሥራት
ልምምድ የሚደረግባቸው ችሎታዎች፡-
ርዕስ ሀ፡- መነሻ ዕውቀት
በቤተሰብ እና ህጻናትን በመንከከባከብ ውስጥ እንዳይሳተፉ አባቶችን የሚከለክላቸው ምን እንደሆነ መገንዘብ።
የአዎንታዊ የአባት ተሳትፎን ሦስት ክፍሎች መገንዘብ።
የአባት ተሳትፎ ለህጻናት እና በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ለሚገኙ ልጆች ዕድገት አስፈላጊ መሆኑን መገንዘብ።
ርዕስ ለ፡- ለአባቶች የማህበረሰብ ስብሰባዎችን ማቀድ
አባቶችን ለማጠናከር በማህበረሰባችሁ ውስጥ የቡድን ውይይቶችን ማቀድ እና ማከናወን የሚቻልበት መንገድ።
አባቶችን በቤተሰብ ውስጥ ለማሳተፍ የሚያስችሉ አዳዲስ አዎንታዊ መንገዶችን እንዲያገኙ ተሳታፊዎችን ማበረታታት።
በዕቅድ ዝግጅታችሁ እና በአፈጻጸማችሁ ውስጥ ቅደም ተከተሉን እንድትከተሉ የሚረዳ ዝርዝር መጠቀም።
የክፍለ ጊዜው ጭብጥ፡- በዚህ የስልጠና ክፍለ ጊዜ የአፍሪካ አባቶች ስለሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች፣ አባቶች በህጻናት ዕድገት ውስጥ መሳተፋቸው አስፈላጊ ስለመሆኑ እና የአባቶችን ተሳትፎ እንዲደግፉ ማህበረሰቦችን ማነሳሳት ስለምትችሉበት መንገድ መሰረታዊ ግንዛቤ ትጨብጣላችሁ።
የክፍለ ጊዜው ዓላማዎች፡- ይህ ክፍለ ጊዜ መንፈስን የምታነሳሱ አስተባባሪዎች እንድትሆኑ የሚያስፈልጓችሁን መገልገያዎች የሚሰጣችሁ ይሆናል። አባቶችን በቤተሰባቸው ውስጥ ማሳተፍ እንዲችሉ ማህበረሰቦችን ለማገዝ እና በአባቶች እና በህጻናት መካከል ጠንካራ ትስስርን ለመፍጠር ትሰራላችሁ።
የእናንተ የሥራ ድርሻ አባቶችን ለማሳተፍ በአካባቢያችሁ ማህበረሰብ ውስጥ የቡድን ስብሰባዎችን ማድረግ መጀመር ነው። ይህን ክፍለ ጊዜ ተግባራዊ ካደረጋችሁ በኋላ የማህበረሰብ ስብሰባዎችን እና አባቶችን የሚያጠናክሩ እንቅስቃሴዎችን እንዲያደርጉ ሌሎች ሰዎችን ማሰልጠን ትችላላችሁ።