ክፍለ ጊዜ 12/21
ገጽ 2/3 ከአሠሪያችሁ ጋር አብሮ ከመሥራት ጋር በተያያዘ ያሉት የሥራ ድርሻዎች እና ግንኙነቶችከአሠሪያችሁ ጋር አብሮ ከመሥራት ጋር በተያያዘ ያሉት የሥራ ድርሻዎች እና ግንኙነቶች
ከዚህ ፕሮግራም መጀመሪያ ጀምሮ የግምገማ ወረቀቱ ላይ እንደተገለጸው የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ የሚያስገኘው ውጤት በአብዛኛው ማህበራዊ መረባችሁን መሠረት በማድረግ የሚወሰን ሲሆን ከዚህ ውስጥም በጣም ትልቁን ቦታ የሚይዘው እንደ የአደራ ቤተሰብ ከቀጠሯችሁ ባለሥልጣን አካላት ጋር ያላችሁ ግንኙነት ነው።
ርዕስ ሀ፡- ከማህበራዊ ሠራተኛው ጋር ተቀናጅቶ መሥራት
ማህበራዊ ሠራተኞች እና የአደራ ቤተሰቦች ምደባውን የሚያዩት በጣም ከተለያዩ አቅጣጫዎች ነው። ማህበራዊ ሠራተኛው የተፈጥሮ ቤተሰቡን ጠቅለል አድርጎ የመመልከት ግዴታ አለበት እንዲሁም አብዛኛውን ጊዜ በተፈጥሮ ወላጆቹ መብቶች እና ፍላጎቶች ላይ ያተኩራል። ከዚህም በተጨማሪ ማህበራዊ ሠራተኛው ህጉን እና የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን (ህጻኑ ወደ ስጋ ቤተሰቡ መመለስ አለበት በማለት እንደተሰጠ የፍርድ ቤት ውሳኔ ያሉትን) የመፈጸም ግዴታ አለበት።
እናንተ የምትሰጡት የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ማህበራዊ ሠራተኛው/ዋ ማስተዳደር ካሉበት/ባት በርካታ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ በመሆኑ አንዳንድ ጊዜ በጣም ብዛት ያላቸው ጉዳዮች ከመኖራቸው የተነሳ እናንተን በማግኘት የሚያሳልፈው/የምታሳልፈው ጊዜ በጣም ውስን ሊሆን ይችላል። ሌላኛው ፈታኝ ሊሆን የሚችል ነገር የሥራ ቦታው አብዛኛውን ጊዜ መልሶ መደራጀቱ እና ማህበራዊ ሠራተኛው ሥራ ወይም የሥራ መደብ ሊቀይር መቻሉ ነው። ይህም ባለሥልጣን አካላት ከአደራ ቤተሰብ ወላጆቹ ጋር ዘላቂ እና በቂ የሆነ ግንኙነት እንዳይመሰርቱ ሊያከብድባቸው ይችላል።
የአደራ ቤተሰብ ወላጆቹ ምደባውን የሚያዩት በጣም ከተለየ አቅጣጫ ነው (እርግጥ ነው ለህጻኑ በአንጻሩ በጣም ይቀርባሉ፣ የህጻኑን ስሜቶች እና ችግሮች ያውቃሉ እንዲሁም ክጻኑ ጋር የመሰረቱት የስሜት ቁርኝት ይኖራል)።
ይህን ስንመለከት ሁለቱ ወገኖች ምን ይቻላል እንዲሁም “የህጻኑ ጥቅምና ፍላጎት ምንድን ነው” በሚሉት ጉዳዮች ላይ በጣም የተለያዩ ሀሳቦች እንደሚኖሯቸው ግልጽ ነው። የአደራ ቤተሰብ ወላጆቹ ሞያዊ ሥራ በእነዚህ ሁለት አቋሞች መካከል ያለውን ልዩነት መገንዘብ እና በእነሱ ላይ ያነጣጠረ አድርገው ያለመመልከት ነው።
ይህ በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ በጣም ፈታኝ ሊሆን የሚችል ቢሆንም ህጻኑ ከምንም በላይ በጥሩ ሁኔታ ዕድገት የሚያሳየው በማህበራዊ ሠራተኛው እና በአደራ ቤተሰብ ወላጆቹ መካከል ጥሩ ግንኙነት እና መግባባት ሲኖር እንደሆነ ጥናቶች ይጠቁማሉ።
2. የግምገማ ወረቀቱን እና በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ማስታወሻዎቻችሁን ቅጂ ለማህበራዊ ሠራተኛው ስጡት። ይህን ማድረጋችሁ ከምደባው ጋር በተያያዘ እናንተ ትልቅ ቦታ የምትሰጡት ነገር ምን እንደሆነ እንዲገነዘብ ማህበራዊ ሠራተኛውን ይረዳዋል።
3. ህጻኑ በእናንተ እንክብካቤ ስር እያለ በምን መልኩ (እና በየስንት ጊዜው) እንገናኛለን ብላችሁ መጠበቅ እንደምትችሉ ማህበራዊ ሠራተኛውን ጠይቁት።
የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮች
- ስለ ውሏችሁ፣ ስለ ሥራው ባህሪ ባለሥልጣናት ሥራችሁ ጥሩ ውጤት አስገኝቷል የሚሉት መቼ እንደሆነ ጥሩ ግንዛቤ ያስጨበጣችሁ የመጀመሪያ ስብሰባ ከማህበራዊ ሠራተኛው ጋር አድርጋችሁ ነበር?
- ማህበራዊ ሠራተኛውን የምታነጋግሩት በየስንት ጊዜው ነው፤ ውይይቶቻችሁስ ወደ ስምምነት እና ተጋግዘዞ ወደ መሥራት ያመራሉ?
- ህጻኑ በየስንት ጊዜው ከተፈጥሮ ወላጆቹ ጋር መገናኘት እንዳለበት እና ይህም በምን መልኩ መከናወን እንዳለበት ማህበራዊ ሠራተኛው በግልጽ አስቀምጧል?
ርዕስ ለ፡- ከአደራ ቤተሰብ ድርጅቱ አሰልጣኞች እና/ወይም ሥራ አስኪያጅ ጋር ተቀናጅቶ መሥራት
ሥራቸው የእናንተን ሥራ መደገፍ በመሆኑ እና ከአደራ ቤተሰብ ወላጆች ጋር በቅርበት አብረው የሚሰሩ በመሆኑ የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤውን እንዴት እንደምታዩት ይበልጥ የማወቅ ዕድላቸው ሰፊ ነው። ይህም ማለት በተቻለ መጠን አእምሮአችሁን ለአዳዲስ ሀሳቦች ክፍት ማድረግ እንዲሁም የአደራ ቤተሰብ ወላጆች እንደመሆናችሁ መጠን በምትሰሩት ሥራ ውስጥ የሚያጋጥሟችሁን በጣም ግላዊ የሆኑ ችግሮች መግለጽ አለባችሁ ማለት ነው።
- ከህጻኑ ወይም ከወላጆቹ ጋር ካላችሁ ግንኙነት ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሟችሁን ከባድ ችግሮች ለግለሰቡ ስለመንገር ምን ታስባላችሁ?
- በሚኖረው የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ስለሚችሉ ከህጻኑ ጋር በተያያዘ በምትሰሩት ሥራ ውስጥ የሚያጋጥሟችሁ የግል ችግሮች ወይም በአደራ ቤተሰቡ ውስጥ ያሉ የትዳር ችግሮች ስለ ማውራት ምን ታስባላችሁ?
1. ግለሰቡ ሊጎበኛችሁ ከመምጣቱ አስቀድማችሁ መወያየት ስለሚያስፈልጓችሁ በጣም አስፈላጊ ነገሮች አስቡ ወይም አጭር ዝርዝር አዘጋጁ። ቢቻል ከመገናኘታችሁ አስቀድማችሁ ለግለሰቡ ላኩለት።
2. በጥየቃዎች ላይ ስላስተዋላችኋቸው ነገሮች ውይይቶችን ለማድረግ በጥየቃዎች ወቅት የግምገማ ወረቀቱን ተጠቀሙ። ይህ ጥሩ ውይይት ለማድረግ እንደ መሰረት ሊያገለግል ይችላል። ግለሰቡ በተሻለ ድጋፍ እንዲያደርግላችሁ ይረዳል እንዲሁም እናንተ የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ሥራን ስለምታዩበት መንገድ ለግለሰቡ ጠቅለል ያለ ጥሩ እይታ ሊሰጠው ይችላል።
3. ተጽዕኖ ስለሚያሳድሩባችሁ የግል ጉዳዮች ለማውራት የምትቸገሩ ከሆነ ይህን ለግለሰቡ ንገሩት። የአደራ ቤተሰብ ወላጆች በምትሆኑበት ጊዜ የምታሳዩአቸው የግል ባህሪዎች የሞያዊ ሥራችሁ አካል ጭምርም ስለሚሆኑ የግል ስለሆኑ ስሜቶች ማውራት በጣም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ እናንተ እና የስራ መሪው/ተቆጣጣሪው ተጋግዛችሁ በመሥራት የግል የሚባለው ምንድን ነው እንዲሁም ሞያዊ እንክብካቤ በምትሰጡበት መንገድ ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር የግድ ውይይት ሊደረግበት የሚገባ የሚባለው ምንድን ነው የሚለው ገደብ የቱ ጋር እንዳለ መወሰን አለባችሁ።
4. ለአንድ ህጻን የአደራ ቤተሰብ የመሆን ሥራ በጣም ከባድ ሊሆን ይችላል እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ እንዲረዳችሁ በተዘረጋው ሥርዓት በጣም ቅር ልትሰኙ ወይም በተወሰኑ ውሳኔዎች ላትስማሙ ትችላላችሁ። ይህ የተፈጠረ እንደሆነ ለስራ መሪው እንድትነግሩት እንመክራለን፤ ነገር ግን በሂደት የሚፈጠሩ ችግሮች ቢኖሩም ተጨባጭ ሁኔታውን ያገናዘበ እና ለአዲስ ሀሳቦች ክፍት የሆነ አስተሳሳብ እንዲኖራችሁ እንመክራለን። በአደራ ቤተሰብ ወላጆች እና በባለስልጣን አካላት ወይም በስራ መሪዎች መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶች ከረጅም ጊዜ አንጻር ለአደራ ቤተሰቡ ልጅ ፈጽሞ አይጠቅሙትም። ነገር ግን ሁል ጊዜም ትህትና በተሞላበት መልኩ ሥራችሁን ለመሥራት የሚያስፈልጋችሁን ድጋፍ ለማግኘት ካለማቋረጥ መጠየቅ አለባችሁ።