ክፍለ ጊዜ 3/21

ገጽ 3/6፡- የርዕስ መግቢያ፡- ርዕስ ሀ እና ርዕስ ለ

ርዕስ ሀ፡- በሽግግር ወቅት ሁኔታውን መቆጣጠር እና መታገስ

እንክብካቤ ሰጪዎች አንድ ህጻን በአዲስ ከባቢ ሁኔታ ውስጥ እስኪላመድ እና ከአደራ ወላጀቹ ጋር እስኪቀራረብ ድረስ የሚወስደውን ጊዜ አሳንሰው የመገመት አዝማሚያ አላቸው። የመጀመሪያውን ዓመት ማሰብ ያለባችሁ ህጻኑ አብዛኛውን ኃይሉን ካለበት አዲስ ሁኔታ ጋር ራሱን ማላመድ ላይ የሚያጠፋበት የሽግግር ጊዜ አድርጋችሁ ነው። ህጻኑ በዕድሜ ከፍ ያለ ከሆነ ይበልጥ ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። ህጻኑ ስሜቶቹን እና ሀሳቦቹን በሙሉ እንደገና ማስተካከል ይኖርበታል፤ ይህም በጣም አድካሚ ነው።
የአደራ ወላጆች ጎበዝ ወላጆች አይደለንም የሚል ጭንቀት ካለባቸው እና ይህን ማረጋገጥ የሚፈልጉ ከሆነ ህጻኑ ላይ በሚታየው መሻሻል ላይ ብቻ ሊያተኩሩ እና ጥሩ ባህሪ እንዲያሳይ ህጻኑ ላይ ከመጠን በላይ ጫና በማሳደር የፍቅር እንዲሁም የፈጣን ዕድገት እና መሻሻል ምልክት ለማየት ሊጠብቁ ይችላሉ። የመጀመሪያውን ወቅት የማገገሚያ ወቅት አድርጎ ማሰብ ጥሩ ነው፡- ህጻኑ እረፍት፣ ማባበል፣ ምቾት እና ትዕግስት ያስፈልገዋል። በቀውስ ውስጥ በማለፍ ላይ ነው።

የአደራ ወላጆች እንደመሆናችሁ መጠን የሚያሳያቸውን ባህሪዎች በመቆጣጠር ህጻኑን ልታግዙት ትችላላችሁ -ህጻኑ ካለማቋረጥ በጣም ሊጨነቅ ወይም ደግሞ በጣም ሊናደድ ወይም ሊያዝን ይችላል። ለዚህ የምትሰጡት ምላሽ የተረጋጋ እና ርህራሄ የተሞላበት ሊሆን ይገባል እንዲሁም እነዚህን ባህሪያት በእናንተ ላይ ያነጣጠሩ አድርጋችሁ ማሰብ የለባችሁም ። አዲስ እና ከባድ ሁኔታ ውስጥ በሚሆኑበት ወቅት የሚታዩ ጤናማ ባህሪያት ናቸው። በተጨማሪም በጣም ትዕግስተኛ መሆን አለባችሁ እንዲሁም ከህጻኑ ብዙ ነገሮችን መፈለግ እና መጠበቅ የለባችሁም። ዋናው ነገር አዲስ እንክብካቤ ሰጪዎቹን እና አዲሱን ከባቢ ሁኔታ እንዲለምድ ህጻኑን ማገዝ ነው እንዲሁም በዚህ የሽግግር ወቅት ለህጻኑ ብዙ ክህሎቶችን ማስተማር ላይ ብዙ ማተኮር የለባችሁም።

ርዕስ ለ፡- ከህጻኑ ላለመለየት ሞክሩ እንዲሁም አስተማማኝ የዕለት ተዕለት ፕሮግራሞችን ፍ

የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ወራት ላይ በአካል ከህጻኑ ጋር ያለመለያየት ጥሩ ነው -ከአደራ ወላጆቹ ውስጥ አንዳቸው ሁልጊዜም መኖር አለባቸው እንዲሁም ህጻኑን ማሰብ ያለባችሁ እንደ ማንኛውም ታዳጊ ህጻን ተንከባካቢዎቹ ምቾት እንዲሰጡት እና ከጎኑ እንዲኖሩ የሚያስፈልገው ህጻን አድርጋችሁ ነው። አብዛኛዎቹ የአደራ ወላጆች የአደራ ልጃቸው ለደቂቃዎች ብቻውን ስለተተወ ሲረበሽ ማስተዋላቸውን ይናገራሉ። ይህ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ይጠፋል -አንዳንድ ጊዜ መጀመሪያ ላይ ካሰባችሁት በላይ በጣም ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ይችላል፤ ስለዚህ በጣም ትዕግስተኛ መሆን አለባችሁ።

መጀመሪያ ላይ ብዙ እንቅስቃሴዎችን እና የእረፍት ሽርሽሮችን ማድረግ እና ጓደኞችን እና ቤተሰቦችን መጋበዝ ጥሩ አይደለም -ይህ ህጻኑ ለመላመድ ይበልጥ እንዲከብደው ያደርጋል። ሌሎች ሰዎችን ከማሳተፋችሁ በፊት አብዛኛውን ሠዓት ብቻችሁን አብራችሁ የምትሆኑባቸው ብዙ ቀናት እንዲኖሯችሁ እና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችን አብራችሁ ለማከናወን ጥረት አድርጉ።

በሽግግር ጊዜው ወቅት ህጻኑ የቤተሰቡን የዕለት ተዕለት ፕሮግራም መማር አለበት። ይህም ህጻኑን ከሚገኝበት የተረበሸ ሁኔታ ማውጣት የምንችልበት በጣም ጠቃሚ መንገድ ነው ሁል ጊዜም ተመሳሳይ ነገሮችን ተመሳሳይ ሠዓት ላይ ደጋግማችሁ አድርጉ!።

ለምሳሌ አንድን የእንቅልፍ ሠዓት ተረት ተረት በርካታ ጊዜ ደጋግሞ ማንበብ ቤታችሁ የተረጋጋ መኖሪያ እንደሆነ ማሳያ ጥሩ መንገድ ነው። በዕድሜ ተለቅ ላሉ ልጆች በየቀኑ ተመሳሳይ ተግባራትን እና እንቅስቃሴዎችን ማከናወን መንፈስን የሚያረጋጋ ሊሆንላቸው ይችላል።

ለህጻኑ ተገማች የሆነ ዓለምን ለመፍጠር እንዲረዳ በዕለት ተዕለት ህይወታችሁ ውስጥ መፍጠር የምትችሏቸውን ልማዶች እና ትናንሽ እንቅስቃሴዎች አስቡ።