ክፍለ ጊዜ 3/21
ገጽ 5/6፡- ርዕስ ሐ፡- የመለያየት ፍርሀትርዕስ ሐ፡- የመለያየት ፍርሀት – “ከመጀመሪያ ጀምሮ ወዳናለች (ወይስ አልወደደችንም ነበር?)””
አንዳንድ ልጆች እንደገና የማይፈለጉ መሆንን ለመከላከል የራሳቸውን ፍላጎቶች እና ዕምነቶች ሊረሱ እና ከአዲስ እንክብካቤ ሰጪዎቻቸው ጋር ለመለማመድ ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ዝግጁ ይሆናሉ። አንዳንድ ሰዎች አንዳንድ ልጆችን ሲያዩ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ የአደራ ወላጆቻቸውን የወደዱ እና ፍጹም ጥሩ በሆነ መልኩ በመላመድ ላይ ያሉ ሊመስላቸው ይችላል። እነዚህ ልጆች ሲያዩአቸው ከሚያገኙት ማንኛውም ሰው ጋር በጣም ደስ በሚል መልኩ መግባባት የሚችሉ ይመስላሉ። ነገር ግን ስሜት ለስሜት የእውነት ለመቀራረብ ጊዜ ይወስዳል። ስለሆነም እንዲህ ያለውን ባህሪ ማየት ያለባችሁ ልጁ እንደገና የማይፈለግ መሆንን ለመከላከል የሚያደርገው ነገር እንደሆነ አድርጋችሁ ነው። እንዲህ ያለው ከመጠን በላይ የመላመድ ባህሪ መንስኤው የመለያየት ፍርሀት ነው። ከተወሰኑ ወራት በኋላ ህጻኑ የመተማመን ስሜት ውስጥ መግባት ይጀምር እና በውስጡ የያዛቸውን ችግሮች እና ግጭቶች ማስተዋል ትጀምራላችሁ። አንድ ህጻን እንዲህ ዓይነቱን ባህሪ ማሳየቱ ህጻኑ የመተማመን ስሜት ውስጥ መግባት መጀመሩን እና በዚህም የተነሳ ችግሮቹን ቢገልጽላችሁም እንኳን ጥላችሁት እንደማትሄዱ በእናንተ ላይ እምነት ያለው መሆኑን የእውነት የሚያሳይ ምልክት ነው።
ሌሎች ልጆች ደግሞ የሚያሳዩት ባህሪ ከዚህ ተቃራኒ ነው። ከመጠን በላይ የመላመድ ችሎታ እንዳላቸው ከማንጸባረቅ ይልቅ የማይፈለጉ የመሆን ፍርሀት ስለሚኖርባቸው ከአዲሶቹ እንክብካቤ ሰጪዎቻቸው ጋር ከነጭራሹ ግንኙነት ላመመስረት ጥረት ያደርጋሉ። እነዚህ ህጻናት አብዛኛውን ጊዜ ትንሽ እያሉ በህይወታቸው ውስጥ የማይፈለጉ መሆን የደረሰባቸው እና በዚህም የተነሳ ላለማዘን እና የማይፈለጉ ላለመሆን በአዋቂ ሰው መመካት የለብንም የሚል ትምህርት የወሰዱ ናቸው። መጀመሪያ ላይ ህጻኑ በጣም ራሱን የቻለ እና የእናንተን ድጋፍ የማይፈልግ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ይህ ህይወትን የመቋቋሚያ ዘዴ ብቻ እንደሆነ እና ሁሉም ህጻን ቀጣይነት ያለው እንክብካቤ፣ ድጋፍ እና ፍቅር እንደሚያስፈልገው አስታውሱ። ከጊዜ በኋላ ህጻኑ ይበልጥ የመተማመን ስሜት ሲሰማው እና ጥላችሁት እንደማትሄዱ ሲያውቅ እናንተን ማመን እና ከእናንተ ጋር የእውነት ስሜት ለስሜት መቀራረብ ይጀምራል። የአንድን ህጻን ሰውን የማመን ችሎታ መልሶ ለመገንባት ረጅም ጊዜ ሊወስድ የሚችል ቢሆንም ህጻኑ ከአዲስ ተንከባካቢው ጋር የሚያሳልፈው እያንዳንዱ አዎንታዊ ነገር በትክክለኛው አቅጣጫ አንድ እርምጃ እንደመራመድ ነው።
ህጻኑ ትንሽ እያለ ችላ መባል የደረሰበት ከሆነ እና በዚያ የተነሳ ከአዋቂዎች ጋር ጥልቅ የሆነ ግንኙነት መመስረት ያልቻለ ከሆነ ብዙም ሳይቆይ አብዛኛውን ጊዜ ምንም የቅርብ ግንኙነት ሳይመሰርት ካገኘው ሰው ሁሉ ጋር ያለምንም መስፈርት እና ገደብ ይቀራረባል። እንዲህ ካለው ህጻን ጋር ቅርርብ ለመፍጠር ዓመታት ሊወስድ ይችላል።
ትንሽ እያሉ እንክብካቤ ያላገኙ ህጻናት ሊያሳዩት የሚችሉት ሌላኛው ባህሪ በጣም ቁጥብ የሆኑ፣ ከማንኛውንም ዓይነት ግንኙነት የሚርቁ እና ግንኙነቶችን የመመስረት ምንም ፍላጎት የማያሳዩ (ለምሳሌ አንድ ህጻን ወይም ታዳጊ የስሜት ለውጥ ቢነበብበት ጤናማ በሚሆንባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ከሰው ጋር በሚለያዩበት እና አንድን ሰው በሚያጡበት ወቅት የስሜት ለውጥ ያለማሳየት) ህጻናት ላይ የሚታይ ነው።

• ሁኔታውን በመቆጣጠር እና ትዕግስተኛ በመሆን ህጻኑን ልንረዳው እንችላለን ብላችሁ ታስባላችሁ?
• ህጻኑ ከእናንተ ጋር የመለያየት ከፍተኛ ፍርሀት ይታይበታል? ይህ በሚከሰትበት ወቅት በተረጋጋ እና ርህራሄ በተሞላበት መልኩ ማስተናገድ የምትችሉት እንዴት ነው?
• ህጻኑ ቀልባችሁን ለመግዛት እና እንደምትፈልጉት ለመሆን እየሞከረ ነው -ለዚህ ምላሽ መስጠት የምትችሉት በምን መልኩ ነው?