ክፍለ ጊዜ 4/21

ገጽ 2/5፡- ርዕስ ሀ፡- መሠረታዊ ሰውን የመቅረብ ንድፈ ሀሳብ እና ሰውን የመቅረብ ሥርዓት

የርዕስ ሀ መግቢያ፡- መሠረታዊ ሰውን የመቅረብ ንድፈ ሀሳብ እና ሰውን የመቅረብ ሥርዓት

ጆን ቦውልቢ
ጆን ቦውልቢ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወላጆቻቸው የተዋቸው ልጆች እና ህጻናት ላይ የነበረውን ከጥልቅ ሀዘን ጋር የተያያዘ ባህሪ ያጠና እንግሊዛዊ የህጻናት አእምሮ ጤና ባለሞያ ነው። ከእነዚህ ተሞክሮዎች በመነሳት የሰው ልጆች በህጻንነት ዕድሜያቸው ያላቸውን ዕድገት የተመለከተ ከሰው ጋር የመቀራረብ ንድፈ ሀሳብ ለመቅረጽ ችሏል። የመጀመሪያ ጥያቄው የሚከተለው ነበር፡-
አጥቢ እንስሳት በሙሉ በጣም የመቀራረብ ባህሪን የሚለማመዱት ለምንድን ነው?
• ዝቅተኛ እንስሳትን (ተሳቢ እንስሳትን፣ አሳን፣ ነፍሳትን) ስንመለከት “እናትየው” በአንድ ጊዜ ብዙ ልጆችን ትወልዳለች። አንድ ወርቃማ አሳ (gold fish) በአንድ ሠዓት ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ እንቁላሎችን ልትጥል ትችላለች። ነገር ግን “እናትየው” አንድ ጊዜ ከእንቁላሉ ከወጡ በኋላ ልጆቿን ብዙም አትንከባከባቸውም። ለዚህም ምክንያቱ የልጁ የአንጎል ዕድገት ገና ሽሉ በእንቁላል ውስጥ እያለ ስለሚጠናቀቅ ነው። ስለዚህ “ልጁ” ከእንቁላሉ ሲወጣ ወዲያውኑ ራሱን ችሎ መንቀሳቀስ ይችላል (ወዲያውኑ እየተሳበ መሄድ ወይም መዋኘት ወይም ማደን ወይም መመገብ ይችላል)። “የእናት እንክብካቤ” አያስፈልገውም (የአንጎሉ ዕድገት የሚጠናቀቀው ገና እንቁላሉ ሳይፈለፈል በፊት ነው)።

• አጥቢ እንስሳት (እንደ ድመት፣ ውሻ፣ አሳ ነባሪ፣ ጉሬላ እና የሰው ልጅ ያሉ ልጆቻቸውን ጡት የሚያጠቡ እንስሳት) ያላቸው ስትራቴጂ በጣም የተለየ ነው እንዲሁም አንጎላቸው በአንጻሩ በጣም ውስብስብ ነው። በሚያረግዙበት ወቅት የሚወልዷቸው ልጆች በቁጥር በጣም ያንሳሉ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ልጅ የበለጠ እንክብካቤ ይሰጣሉ። የሰው ልጆች የሚወልዷቸው ልጆች የሚወለዱት በጣም ያልበሰለ አንጎል ይዘው ነው፤ እንዲሁም ለበርካታ ዓመታት ሳይበስል ስለሚቆይ ወላጆቹ አንጎሉን ሊቀርጹት እና እንደሚፈልጉት ሊሞሉት ይችላሉ። ህጻናት ማንበብን፣ ማሰብን፣ ማህበራዊ ህይወትን እና ችግሮችን መፍታትን፣ ወዘተ ከአዋቂዎች መማር ይችላሉ። “አንጎላችሁን የምታዳብሩት” በአስተዳደግ እና ከእንክብካቤ ሰጪዎቻችሁ በምታገኙት እንክብካቤ ነው።

• የሰው ልጅ አንጎል ሙሉ በሙሉ እስኪዳብር ድረስ ከ16-17 ዓመታት ይፈጃል፤ በእነዚህ ሁሉ ዓመታት ወቅትም የእንክብካቤ ሰጪዎቻቸው እንክብካቤ እና ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

ጥያቄዎች
• የቤት እንስሳት አሏችሁ ወይም የቤት እንስሳት ያሉት ሰው ታውቃላችሁ? እንስሳቱ ከወለዱ በኋላ ልጆቻቸውን የሚንከባከቡት እንዴት ነው?
• ልጆቻቸውን በሚንከባከቡበት ወቅት ምን ያደርጋሉ? በራሳቸው መንቀሳቀስ እስከሚችሉ ድረስ ለምን ያህል ጊዜ ነው ከራሳቸው ጋር የሚያቆዩአቸው?
በጣም የመቅረብ ባህሪ ምንድን ነው?
• አጥቢ እንስሳት በህይወት ለመቆየት የሚጠቀሙት ይህ ዘዴ አንድ ትልቅ ችግር አለበት፡- አዲስ የተወለደው እንስሳ አንጎል ብዙም አይሠራም፤ ስለዚህ ኣአዲስ የተወለደው እንስሳ ራሱን መጠበቅ አይችልም (ህይወቱ በተለይም ደግሞ የህይወቱ የመጀመሪያ ዓመታት ላይ ሙሉ በሙሉ በውጫዊ አዋቂ እንክብካቤ ሰጪዎች ላይ ጥገኛ ነው)።

• ለዚህ ነው የሰው ልጆች በጣም የመቀራረብ ሥርዓት ያላቸው፡- በጣም የቅርበት ስሜት የሚሰማው መሆኑ ለህጻኑ መተማመንን፣ ጥበቃን እና እንክብካቤን ይሰጠዋል። ስለዚህ በጣም የመቀራረብ ባህሪ፡-
o ህጻኑ ከወላጆቹ ጥበቃ እና እንክብካቤ ለማግኘት እና ጡት ለመጥባትን ጥረት የሚያደርግበት መንገድ ነው።

• እንክብካቤ ሰጪዎቹ ህጻኑን ቢተውት ይሞታል። ስለዚህ ህጻናት በአካል መለያየትን ለመከላከል ጥረት ያደርጋሉ

እንዲሁም በጣም የመቀራረብ ባህሪ በማሳየት ምላሽ ይሰጣሉ። በጣም የመቀራረብ ሥርዓቱ ሥራ የሚጀምረው፡-

o መለያየት ወይም የመለያየት ፍርሀት ብቻም እንኳን ሲኖር በጣም የመቀራረብ ሥርዓቱ መሥራት ይጀምራል።
o ህጻኑ በህይወት ለመቆየት ያለው ዕድል በአካል መለያየትን መከላከል ነው።
o ህጻኑ መለያየትን የሚከላከለው ይዞ አልለቅም በማለት፣ በማልቀስ፣ እንክብካቤ ሰጪውን በመፈለግ፣ ድባቴ እና ሀዘን ውስጥ በመግባት፣ እና እንክብካቤ ሰጪው ሲሄድ በመቃወም ነው።

• ይህ የተለመደ እና ጤናማ በጣም የመቀራረብ ባህሪ ነው። እንክብካቤ ሰጪዎቻቸው ሲሄዱ የስሜት ለውጥ የማያሳዩ ህጻናት እንክብካቤ መፈለግ ላይ ተስፋ የቆረጡ (አሜን ብለው የተቀበሉ) ሊሆኑ ይችላሉ። “በጣም የተረጋጉ” ተብለው ሊገለጹ ይችላሉ፤ ነገር ግን ይህ ባህሪ ጤናማ አይደለም። እንክብካቤ ሰጪዎቻቸው ሲሄዱ በጣም የሚረበሹ ህጻናት ደግሞ በጣም ከባድ እና አስጨናቂ መለያየት የደረሰባቸው ሊሆኑ ይችላሉ። እንዲህ ያሉት የስሜት ለውጦች ጤናማ አይደሉም፤ እንዲሁም እንዲህ ያሉትን የስሜት ለውጦች ብዙ ጊዜ የምታዩት የተፈጥሮ ወላጆቻቸው ሊንከባከቧቸው ያልቻሉ ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት ላይ ነው።

ጥያቄዎች
• የራሳችሁን ልጆች ጤናማ ሰውን የመቅረብ ባህሪዎችን ሲያሳዩ በዓይነ ህሊናችሁ ልታዩአቸው ትችላላችሁ (ስትሄዱ ሲያለቅሱ ወይም ይዘው አልለቅም ሲሉ፣ ሲጮኹ፣ ሲያዝኑ፣ ወዘተ)?

• ከሥራችሁ ጋር በተያያዘ የምታውቋቸው ህጻናት ላይ እንዲህ ያለውን ባህሪ የምታዩባቸው መቼ ነው? እንክብካቤ ሰጪዎቻቸው ሲሄዱ ምንም የስሜት ለውጥ የማያሳዩ ህጻናት አሉ? እንክብካቤ ሰጪአቸው ሲሄድ ለረጅም ሠዓት የመረበሽ ስሜት ውስጥ የሚገቡ ህጻናትስ አሉ?

• ህጻናት ጤናማ ሰውን የመቅረብ ባህሪ ሲያሳዩ የምንከተለው አሠራር ምን ዓይነት ነው?

• በምን ምልኩ ነው ምላሽ የምንሰጠው (እናባብላቸዋለን፣ እንቆጣቸዋለን፣ “ረባሽ” እንደሆኑ እናስባለን፣ ሲያለቅሱ እንጨነቃለን? ወይስ…?)።

• ህጻናት በጣም ሰውን የመቅረብ ባህሪ ሲያሳዩ በባህላችን ውስጥ ወላጆች ምን ያደርጋሉ?

• ይዘው አልለቅም ስለሚሉ ልጆች አያያዝ እናታችሁ ምን ትል ነበር? አባታችሁስ?

የግንዛቤ መገምገሚያ ጥያቄዎች
• ሰውን የመቅረብ ንድፈ ሀሳብን የቀረጸው ማን ነው?

• አጥቢ እንስሳት (በተለይም ደግሞ የሰው ልጆች) ብቻ የመቀራረብ ሥርዓት ያላቸው ለምንድን ነው?

• ከሥራችሁ የተወሰደ የዕለት ተዕለት ምሳሌን በመጠቀም ጤናማ ሰውን የመቅረብ ባህሪን ግለጹ።
• ሥራችሁ ላይ የምታውቋቸው በጣም አነስተኛ ወይም በጣም መረበሽ የሚታይበት ሰውን የመቅረብ ባህሪ ያላቸው ልጆችን ግለጹ።

የሚመከሩ መልመጃዎች
በዕለት ተዕለት ህጻናትን የመንከባከብ ሞያችሁ ውስጥ የምታዩአቸውን ጤናማ ሰውን የመቅረብ ባህሪዎችን የማስታወስ ችሎታችሁን በመጠቀም አስታውሱ ወይም ሞባይል ስልካችሁን ወይም ካሜራችሁን ተጠቅማችሁ ቅረጹ። እንክብካቤ ሰጪው ሲሄድ ህጻናት የሚሰጡትየተለያዩ ምላሽ በምን መልኩ ነው?