ክፍለ ጊዜ 4/21

ገጽ 3/5፡- የርዕስ መግቢያ ለ፡- በልጁ አስተማማኝ መሠረትን የሚያጠናክር የማሰስ ባህሪ ላይ መሥራት

የርዕስ መግቢያ ለ፡- በልጁ አስተማማኝ መሠረትን የሚያጠናክር የማሰስ ባህሪ ላይ መሥራት r

ሰውን የመቅረብ ሥርዓቱ በሥራ ላይ እስካለ ድረስ ህጻኑ ሙሉ ኃይሉን የሚያጠፋው መለያየትን ለመከላከል እንክብካቤ ሰጪውን በመፈለግ ሲሆን ይህም ለህጻኑ በጣም አድካሚ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ሁሉም ህጻን ስለ መለያየት መማር አለበት (እንክብካቤ ሰጪዎች እና ወላጆች ሌሎች ኃላፊነቶች አሉባቸው)። በሚለያዩበት ጊዜ በጣም እንዳይፈሩ ህጻናትን ማስተማር የምትችሉት እንዴት ነው?

እንክብካቤ ሰጪው የሚከተሉትን ሁለት ነገሮችን በማድረግ ህጻኑን ፍርሀት ሳይሰማው እንዴት መለያየት እንደሚችል ማስተማር ይችላል/ትችላለች፡-

  • ህጻኑ እንዳይረበሽ እንክብካቤ ሰጪው መለያየትን ለህጻኑ ቀስ በቀስ ያስተምራል።

ለምሳሌ እንክብካቤ ሰጪው ህጻኑን ያስተኛ እና ይሄዳል፤ ከዚያ ህጻኑ ሲያለቅስ እንክብካቤ ሰጪው ተመልሶ መጥቶ ያባብለዋል። ቀጥሎ ያለው ጊዜ ላይ ተለያይቶ የሚቆይበት ጊዜ ትንሽ ረዘም ይላል፤ እንደዚያ እንደዚያ እያለ ይቀጥላል። መጨረሻ ላይ እናቱ ስትሄድ ህጻኑ አይፈራም። ድንገት ተነስታ ከሄደች ወይም ህጻኑን ተቆጥታው ከሄደች ህጻኑ ዝም ብሎ ያለቅሳል እንዲሁም መልሶ መላልሶ ይረበሻል።

  • በተጨማሪም እንክብካቤ ሲጪዋ ከእይታው ስትርቅ እንዲያስታውሳት ህጻኑን ታስተምራለች።

ለምሳሌ እንክብካቤ ሰጪዋ “አየሁህ!” ወይም ድብብቆሽ ከህጻኑ ጋር ልትጫወት ትችላለች። እንክብካቤ ሰጪዋ በጨዋታ መልኩ ከበር ጀርባ ለአጭር ሠዓት ከተደበቀች በኋላ ህጻኑ በጣም ሳይፈራ በፊት ተመልሳ ትመጣለች። በዚህ መንገድ ህጻኑ “እኔ ላያት በማልችልበት ጊዜም አለች” የሚለውን ይማራል። ይህም እንክብካቤ ሰጪዋ በማትኖርበት ጊዜም እንኳን ህጸኑን የደህንነት ስሜት እንዲሰማው ይረዳዋል።
የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ሰጪ እንደመሆናችሁ መጠን ከህጻኑ ጋር በመሆን እነዚህን ተረጋግቶ ከሰው ጋር መለያየትን ማስተማሪያ ሁለት መንገዶች መለማመድ ትችላላችሁ።

Here is a caregiver trying to teach her child to play ”peek a booh”