ክፍለ ጊዜ 8/19
ገጽ 2/3 የርዕስ መግቢያ፡- በሞያዊ ዕድገታችሁ ላይ መወያየትየርዕስ መግቢያ፡- በሞያዊ ዕድገታችሁ ላይ መወያየት
ይህን ግምገማ ለማድረግ በጣም ተመራጩ መንገድ በቡድን ከዚህ በታች በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ መወያየት እና አስተያየት መስጠት ነው።
(የግምገማ ወረቀት ቃለ መጠይቁን የመለሳችሁበትን የስልጠናው መጀመሪያ ላይ የነበረውን ጊዜ መለስ ብላችሁ ማሰብ ትችላላችሁ)
አሰልጣኙ ጥያቄዎቹን ሊጠይቃችሁ እና መልሶቻችሁን ሊጽፍ ይችላል። በአንድ ጊዜ አንድ ህጻንን በተመለከተ ብቻ መልስ ስጡ።
እባካችሁ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ በጋራ ተወያዩ፡-
የህጻኑ ዕድገት (የግምገማ ወረቀቱ ላይ “ሥራው ምን ያህል አድካሚ ነው” ከሚለው አንስቶ “የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ላይ ስላለው ህጻን ያሏችሁ ሀሳቦች እና የምትጠብቋቸው ነገሮች” እስከሚለው ድረስ ያሉት የመጀመሪያ ጥያቄዎች)፡-
2.ህጻኑን ሲያስስ እና ሲማር ታዩታላችሁ ወይስ በጣም ያለመተማመን ስለሚሰማው ደህንነቱን ነው የሚፈልገው?
3.ህጻኑ ላይ እንደጠበቃችሁት ዕድገት እየታየበት ነው?
4.የህጻኑ ባህሪ ላይ ያያችሁት በጣም ጥሩ መሻሻል ምንድን ነው?
5.ህጻኑን አሁንም ድረስ በማህበራዊ ግንኙነቶች ውስጥ የሚከብደው ምንድን ነው?
6.ከህጻኑ የተፈጥሮ ቤተሰብ (ካለ) ጋር ያላችሁ ትብብር ምን ይመስላል?
7.ከተፈጥሮ ወላጆቹ ጋር መተባበር የምትችሉበትን መንገድ አግኝታችኋል?
8.ከዚህ ህጻን ጋር በተያያዘ የነበራችሁ በጣም ትልቅ ቦታ የምትሰጡት ተሞክሮ ምንድን ነው (የምታሳዩትን ባህሪ ስትመለከቱት በጣም ስኬታማ የሆነው ምንድን ነው እንዲሁም የማይሰራ የሚመስላችሁስ ምንድን ነው)?
ከባለሥልጣን አካላት እና ከባለሞያዎች ጋር ያሏችሁ ግንኙነቶች (የግምገማ ወረቀቱ ላይ ጥያቄ 1-4)፡-
2.ከተቆጣጣሪው/ስራ መሪው/ ወይም የአደራ ቤተሰብ ሥራ አስኪያጁ ጋር ያላችሁ ግንኙነት በምን መልኩ ጎልብቷል?
3.በጣም የረካችሁባቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?
4.ያላችሁን ቅንጅታዊ አሠራር መሠረት በማድረግ ምን ላይ ድጋፍ እንዲያደርጉላችሁ ትጠይቋቸዋላችሁ (ህጻኑን ለመንከባከብ በጣም የሚያስፈልጋችሁ ነገር ምንድን ነው)?
የቤተሰብ ግንኙነቶቻችሁ (የግምገማ ወረቀቱ ላይ ጥያቄ 5-11)፡-
2.ግንኙነታችሁ ተሻሽሏል ወይስ ብሶበታል?
3.የአደራ ቤተሰብ መሆናችሁ ከራሳችሁ ልጅ ወይም ልጆች ጋር (ካሏቸሁ) ባሏችሁ ግንኙነቶች ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ አሳድሯል?
4.የራሳችሁ ልጆች (ካሏችሁ) ከዚህ ምን ተምረዋል (ይበልጥ ኃላፊነት የሚሰማቸው እና የሚገነዘቡ ሆነዋል ወይስ የአደራ ቤተሰብ መሆናችሁን የሚያዩት እንደ ሸክም ነው)?
5.ጓደኞቻችሁ፣ ዘመዶቻችሁ እና ጎረቤቶቻችሁ የምትሰጡትን የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ በተመለከተ ይበልጥ የሚገነዘቧችሁ እና የሚደግፏችሁ ሆነዋል?
6.ህጻኑ ከእናንተ ጋር መኖሩን የተፈጥሮ ወላጆቹ ተቀብለውታል?
7.የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ላይ ያለ ህጻን ስለመሆንን ህጻኑ የተሻለ ግንቤዛን አዳብሯል?
8.ከእነዚህ ጉዳዮች ውስጥ የትኞቹ ላይ መሻሻል ታይቷል እንዲሁም የትኞቹ አሁንም የእናንተን ትኩረት ይሻሉ ብላችሁ ታስባላችሁ?
አስተማማኝ ቅርበት ያለው ወላጅነት ባህሪያችሁ (የግምገማ ወረቀቱ ላይ ጥያቄ 12-19)፡-
2.ስሜትን የምታገናዝቡ ሰዎች ለመሆን ችላችኋል?
3.ህጻኑ ማጽናናት ባስፈለገው ጊዜ ተደራሽ ለመሆን ችላችኋል?
4.እንደ ህጻኑ ሳትሆኑ የህጻኑን ስሜት ለመጋራት ችላችኋል?
5.ስለሚሰማው ስሜት እና ስለሚያስበው ነገር እንዲሁም ሌሎች ሰዎችን ስለሚያይበት መንገድ ከህጻኑ ጋር ለመወያየት ችላችኋል?
6.የአስተማማኝ ወላጅ ባህሪን ተግባራዊ ስለማድረግ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
7.ከአደራ ልጃችሁ ጋር በተያያዘ ከእነዚህ ባህሪዎች ውስጥ በጣም ፈታኝ ሆኖ ያገኛችሁት የትኛውን ነው?
ህጻኑ ከእኩዮቹ ጋር ባሉት ግንኙነቶች ላይ የምትሰሩት ሥራ (የግምገማ ወረቀቱ ላይ ጥያቄ 20-23)፡-
2.ህጻኑ ጓደኞች አግኝቷል፤ እናንተስ በዚህ ረገድ በምን መልኩ ነው የደገፋችሁት?
3.ጓደኞችን ከማፍራት እና ከእነሱ ጋር ከመቀራረብ ጋር በተያያዘ ህጻኑ አሁንም ድረስ የሚከብደው ምንድን ነው?
4.ከሌሎች እንክብካቤ ሰጪዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት መስርታችኋል (መምህራን፣ የህጻናት ማቆያ፣ የትርፍ ጊዜ እንቅስቃሴ አሰልጣኞች)?
5.ምን ላይ ስኬት አስመዝግበናል ብላችሁ ታስባላችሁ እንዲሁም አሁንም ድረስ የእናንተን ትኩረት የሚሻው ምንድን ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?