ክፍለ ጊዜ 6/21
ገጽ 4/4 የሥራ ዕቅድ፡- ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት የሚሠሩ ሥራዎች
የሥራ ዕቅድ፡- ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት የሚሠሩ ሥራዎች
የሚከተለውን አስተውላችሁ ጻፉ ወይም ሞባይል ስልካችሁን ወይም ካሜራችሁን በመጠቀም ቅረጹ፡- የዕለት ተዕለት ተጨባጭ ተግባራትን የምታከናውኑበትን መንገድ። ቪዲዮውን ተመልከቱ እና ተጨባጭ ሥራዎችን በምትሰሩበት ወቅት ከህጻናቱ ጋር መስተጋብር ማድረግ በምትችሉበት መንገድ ላይ ተወያዩ። በቀን ውስጥ የተለያዩ ሁኔታዎች ላይ አንዳንድ ጊዜ ተጨባጭ ሥራዎችን እንዴት በጣም አስፈላጊ ሆነው ልታገኟቸው እንደምትችሉ እና አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እንዴት ከግንኙነት ጋር በተያያዘ የሚሠሩ ስራዎችን በጣም አስፈላጊ ሆነው ልታገኟቸው እንደምትችሉ ተወያዩ።
የሚከተለው ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት ልታደርጉት የምትችሉት ነገር ምሳሌ ነው፡-
-
- አንደኛውን ችሎታ ምረጡ እና እስከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ድረስ እንዴት እንደምታሻሽሉት ተወያዩ።
- የትኞቹን አሠራሮች ለማሻሻል እንደምትሞክሩ እና በምን እንቅስቃሴዎች/ የቀን ሠዓት ላይ እንደምታደርጉት ወስኑ።
- የምታሳዩትን መሻሻል እንዴት እንደምትመለከቱ ወይም በቪዲዮ እንደምትቀርጹ አቅዱ። መደበኛ አሠራራችሁን እና ህጻናቱ የሚሰጡትን ምላሽ በማስተዋል ጀምሩ እና ወደ አዲሱ አሰራራችሁ እና ህጻናቱ ወደሚሰጡት ምላሽ ሂዱ።
- አሁን የተወያያችሁትን ነገር እና ለማድረግ የወሰናችሁትን ነገር እንዲሁም ማን እንደሆነ የሚያደርገው ጻፉ።
ፍላጎት ስላሳያችሁ እያመሰገንን እስከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ድረስ ለምትሰሩት ሥራ መልካም ዕድል እንመኝላችኋለን!