ክፍለ ጊዜ 4/21
ገጽ 5/5: የሥራ ዕቅድ፡- ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት የሚሠሩ ሥራዎችየሥራ ዕቅድ፡- ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት የሚሠሩ ሥራዎች
- ሀ. እንክብካቤ ሰጪያቸው ስትሄድ በጣም የመቅረብ ባህሪ በማሳየት ምላሽ የሚሰጡ ህጻናትን ወይም ልጆችን አስተውላችሁ በአእምሮአችሁ መዝግቡ ወይም አጠር ያሉ ቪዲዮዎችን ቅረጹ።
- ለ. አስተማማኝ መሰረት የመሆን ባህሪ የምታሳይ አንዲት እንክብካቤ ሰጪን የሚያሳይ አጠር ያለ ቪዲዮ ቀርጻችሁ አዘጋጁ።
- ሐ. የተለያዩ ህጻናት እንክብካቤ ሰጪያቸው ስትሄድ የሚሰጡትን ምላሽ ቅረጹ (እንክብካቤ ሰጪያቸውን ይዘው አልለቅም እንደሚሉ ወይም ማሰስ፣ ዳዴ ብለው መሄድ፣ ወዘተ እንደሚጀምሩ)።
1.የሞባይል ስልካችሁን ከተጠቀማችሁ፡- ቪዲዮዎቹን የምታዩአቸው እናንተ፣ ሌሎቹ የአደራ ቤተሰብ ተንከባካቢዎች እና አሰልጣኙ ብቻ እንደምትሆኑ ማረጋገጥ የምትችሉት እንዴት ነው?
2.የቀረጻችኋቸውን ነገሮች በኋላ እንድታዩአቸው ደህንነቱ አስተማማኝ በሆነ መልኩ ማስቀመጥ የምትችሉት እንዴት ነው (ለምሳሌ የይለፍ ኮድ ያለው ኮምፒዩተር ላይ)?
3.የቀረጻችኋቸውን ነገሮች በሙሉ አንድ ኮምፒዩተር ላይ ካስቀመጣችሁ በኋላ ለመቅረጽ ከተጠቀማችኋቸው ሞባይል ስልኮች ወይም ካሜራዎች ላይ መሰረዛቸውን አረጋግጡ።
ፍላጎትስላሳያችሁእያመሰገንንእስከሚቀጥለውክፍለጊዜድረስለምትሰሩትሥራመልካምዕድልእንመኝላችኋለን!