ክፍለ ጊዜ 1/21

ገጽ 2/5፡- በአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ሥራችሁ ውስጥ ባለሞያዎቹ እናንተ ናችሁ

በአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ሥራችሁ ውስጥ ባለሞያዎቹ እናንተ ናችሁ

ይህን ፕሮግራም ያዘጋጁት ባለሞያዎች እና የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ሰጪዎች ሁሉንም ነገር ያውቃሉ ማለት አይደለም በተለይም ደግሞ እናንተን፣ የየአንዳንዳችሁን የአደራ ቤተሰብ ወይም በእናንተ እንክብካቤ ስር ያለውን እያንዳንዱን ህጻን አያውቁም።

እያንዳንዱ የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ እና ህጻን የተለየ ነው። ሆኖም ግን ስልጠናው ስለ የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ሥራዎች በጥቅሉ ብዙ ዕውቀትን ሊሰጣችሁ ይችላል፤ ነገር ግን የአደራ ቤተሰብ እንክበብካቤ ሥራችሁን እና ልጃችሁን የምታውቁት እናንተ ብቻ ናችሁ:: ስለመሆነም ይህን ራሱን የቻለ እና የተለየ የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ በተመለከተ ባለሞያዎቹ እናንተ ናችሁ።

ፕሮግራሙ ዝም ብላችሁ የምትማሩት እና የምታደርጉት ነገር አይደለም። እኛ ጠቅላላ ዕውቀቱን እናቀርባለን፤ ከዚያ በኋላ እንዴት እንድትጠቀሙት በንቃት የምትወስኑት እና በሂደት ተግባራዊ የምታደርጉበትን አሠራር የምትፈልጉት ግን እናንተ ናችሁ። ይህን ኃላፊነት መውሰዳችሁ ሥራችሁ አስደናቂ እንደሆነ ይበልጥ እንዲሰማችሁ እንደሚያደርጋችሁ ተስፋ እናደርጋለን።

የአደራ ቤተሰብ ወላጅ ስለመሆን ልታናግሩት የምትችሉት ሰው አላችሁ
በርካታ የአደራ ቤተሰብ ወላጆች የሚኖሩት ከከተማ ርቀው ነው የሚሠሩትም ብቻቸውን በመሆኑ ችግሮች እና ጭንቀቶች አሉባቸው። በዚህ ስልጠና ላይ ከአሰልጣኛችሁ እና ከስልጠናው ድጋፍ ታገኛላችሁ እንዲሁም በዚህ የስልጠና ፕሮግራም ውስጥ ካሉ ሌሎች የአደራ ቤተሰብ ወላጆች ጋር ስልጠናው ካበቃ በኋላም እንኳን ድጋፍ ለማግኘት ልትጠቀሙት የምትችሉበት ማህበራዊ ትስስር ለመፍጠር በጣም ጥሩ ዕድል ታገኛላችሁ። ስለሆነም እባካችሁ ከሌሎቹ የአደራ ቤተሰብ ወላጆች ጋር ተነጋገሩ ማናቸውንም ችግሮች ከእነሱ እና ከአሰልጣኙ ጋር በግልጽ ተወያዩ።