ክፍለ ጊዜ 1/19

ገጽ 5/5፡- የሥራ ዕቅድ፡- ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት የሚሰሩ ሥራዎች
የሥራ ዕቅድ፡- ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት የሚሰሩ ሥራዎች

የእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ የሥራ ዕቅድ ትወስናላችሁ። የመጀመሪያውን የሥራ ዕቅድ በተመለከተ የሚከተሉትን እንድታድርጉ እንመክራለን፡-

 

  •  የሞባይል ስልካችሁን በመጠቀም በየቀኑ ከልጁ/ልጅቷ ጋር የሚፈጠሩ ሁኔታዎችን የሚያሳዩ አጭር ቪዲዮዎችን ቅረጹ። ስልክ ከሌላችሁ በየቀኑ የሚፈጠር አንድ ሁኔታ ፈልጋችሁ የሚቀጥለው የስልጠና ክፍለ ጊዜ ላይ መናገር እንድትችሉ አስተውሉት እንዲሁም በአእምሮአችሁ መዝግቡት። ለምሳሌ አብራችሁ ቁርስ መብላት፣ የሚያዝናና ነገር ማድረግ፣ መሥራት፣ ወዘተ። በምታስተውሉት ሁኔታ ወይም በምትቀርጹት ነገር ውስጥ ከህጻኑ/ህጻኗ ጋር መስተጋብር የሚያደርጉትን ሰዎች ማካተታችሁን አረጋግጡ።
  • እነዚህ ቪዲዮዎች ወይም ምልከታዎች የሆነ ቀን ልጁ/ልጅቷ ከአደራ ቤተሰብ እንክብካቤያችሁ በሚወጣበበት/በምትወጣበት ወቅት በጣም የሚጠቅሙ ይሆናሉ። 
  • በእንክብካቤያችሁ ስር ያሉ ህጻናት ላይ ምን እንደሚሠራ እና ምን እንደማይሰራ ለመረዳት ስላስተዋላችሁት ነገር እና እንክብካቤ ስለምትሰጡበት መንገድ በጋራ መወያየት እና አስተያየት መስጠት ትችላላችሁ።

 

የአደራ ቤተሰብ ወላጅ በአደራ ከምታሳድጋቸው ልጆች ጋር የሚከሰቱ የዕለት ተዕለት ሁኔታዎችን ቪዲዮ ስትቀርጽ
ፍላጎት ስላሳያችሁ እያመሰገንን እስከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ድረስ ለምትሰሩት ሥራ መልካም ዕድል እንመኝላችኋለን!