ፍለ ጊዜ 1/21
ገጽ 3/5: ርዕስ ሀ፡- የስልጠና ፕሮግራሙ አጠቃቀምርዕስ ሀ፡- የስልጠና ፕሮግራሙ አጠቃቀም
የግምገማ ወረቀቱ የተዘጋጀው እናነተን እና አሰልጣኛችሁን በክፍለ ጊዜዎቹ ውስጥ ለምትሰሩት ሥራ ለማዘጋጀት እና ስለተማራችሁት ነገር እና ሥራችሁን ማዳበር ስለምትችሉበት መንገድ ያላችሁን ሀሳብ እንድትገልጹ ለማስቻል ነው። የግምገማ ወረቀቱ (ከአሰልጣኛችሁ ጋር በመሆን) ህጻናትን በመንከባከብ የዕለት ተዕለት ሥራችሁ ውስጥ ዋናው ጉዳይ ላይ ለማተኮር እንዲረዳችሁ ልትጠቀሙት የምትችሉት ዘዴ ነው። የግምገማ ወረቀቱን በመጠቀም ህጻናትን ስለመንከባከብ ሥራችሁ በርካታ ጥያቄዎችን የምትጠየቁ ሲሆን በግምገማ ወረቀቱ ላይ ያሉትን ጥያቄዎች መመለስ ህጻናቱ ስላሉባቸው ችግሮች እና ስላሏቸው ግብዓቶች ጠቅለል ያለ እይታ የሚሰጣችሁ ከመሆኑም በላይ በእንክብካቤ ሥራችሁ ውስጥ ምን ማሻሻል እንደምትፈልጉ ግንዛቤ ይሰጣችኋል።
የግምገማ ወረቀቱን ጥያቄዎች ከመለሳችሁ በኋላ ስለምትገኙበት ሁኔታ እና በክፍለ ጊዜዎቹ ውሰጥ ምን ላይ መሥራት እንደሚያስፈልግ ጥሩ ግንዛቤ ይኖራችኋል።
አስተውሉ፡- ለግምገማ ወረቀቱ ቃለ መጠይቅ የምትሰጧቸው መልሶች ፈተና አይደሉም፤ የስልጠና ፕሮግራሙን በምትጠቀሙበት ወቅት ልንሰራበት ያስፈልጋል የምትሉትን ጉዳይ መተንተን እና ማቀድ የምትችሉበት መሳሪያችሁ ነው። የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ሥራችሁን ከሄሊኮፕተር ላይ ሆናችሁ እንደመመልከት ነው። ከዚህ እይታ በመነሳት በሥልጠናው ወቅት ምን ላይ መሥራት እንደምትፈልጉ መወሰን ትችላላችሁ።
ስልጠናው ካበቃ በኋላ የተቀሩትን ክፍለ ጊዜዎች በማከናወን እና ራሳችሁን በማስተማር መቀጠል ትችላላችሁ።
በአንድ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ምን ምን አለ?እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ አንድን ርዕስ ጉዳይ በጽሁፍ እና በቪዲዮ በማቅረብ (ለምሳሌ ክፍለ ጊዜ 4 የሚከተለውን ርዕሰ ጉዳይ ያቀርባል፡- “ሰውን የመቅረብ መሠረታዊ ንድፈ ሀሳብን መገንዘብ”) ርዕሰ ጉዳዩን በተመለከተ አስፈላጊ የሆነውን ሞያዊ ተሞክሮ እና ንድፈ ሀሳብ ያሳያችኋል።
በእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ውስጥ የተማራችሁትን ነገር እንዴት ተግባራዊ እንደምታደርጉት እንድትወያዩ፣ እንድታስቡ እና እንድታቅዱ ትጠየቃላችሁ። በንቃት እንድትሳተፉ እና የተማራችሁትን ነገር ተግባራዊ ስለምታደርጉበት መንገድ የራሳችሁን ሀሳብ እንድታመጡ እንጠይቃችኋለን። በፕሮግራሙ ውስጥ የምታገኙትን ዕውቀት እንዴት መጠቀም እንዳለባችሁ ከማንም በለይ የምታውቁት እናንተው ናቸው።
የእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ አለልጣኙ ሀሳቦቻችሁን እና ዕቅዶቻችሁን በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ እስከምትገናኙ ድረስ በምን መልኩ ተግባራዊ እንደምታደርጓቸው እንድትጽፉ ይጠይቃችኋል።
ቢቻል የየዕለት ውሎአችሁን (diary) እንድትጽፉ እንመክራለን (አብዛኛውን ጊዜ መሻሻላችንን ማየት የምንችለው ወደኋላ ስንመለከት ነው እንዲሁም በአደራ የምታሳድጉት ልጅ ሲያድግ የምትሰጡት ጠቃሚ የጽሁፍ ማስታወሻ ይሆናችኋል።የምትጽፏቸውን ወይም የምትመዘግቧቸውን ማናቸውም እይታዎች በስልጠና ፕሮግራሙ ውስጥ የማይሳተፍ ማንኛውም ሰው ሊያያቸው ወይም ሊጠቀማቸው አይገባም።
ጽሁፉ በሚስጥር መያዝ ያለበት ነው።
Here is an example of an instructor educating a group of SOS mothers. Please notice how the instructor involves the participants and gets them to speak.