ክፍለ ጊዜ 16/21

ገጽ 5/6 ጨዋታ ከዕድሜ ጋር እያደገ ይመጣል

ጨዋታ ከዕድሜ ጋር እያደገ ይመጣል

አንድ ህጻን የሚፈልገው እና ለመጫወት ተነሳሽነት ያለው የጨዋታ ዓይነት እንደ ዕድሜው ይወሰናል። አንድ ህጻን ዕድሜው እየጨመረ ሲመጣ የፈጠራ ችሎታውን ይበልጥ ይጠቀማል እንዲሁም አሻንጉሊቶችን፣ ሀሳቦቹን እና ዕቃዎችን በመጠቀም ይበልጥ የተለያዩ ነገሮችን ይሞክራል። በተጨማሪም ረዘም ላለ ጊዜ ትኩረት ማድረግ የሚችል በመሆኑ ለመጫወት ይበልጥ ጊዜ እና ቦታ ሊያስፈልገው ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ ህጻናት ለብቻቸው እንደመጫወት፣ ከሌሎች ሰዎች አጠገብ እንደመጫወት እና ከሌሎች ሰዎች ጋር እንደመጫወት ያሉ የተለያዩ ነገሮችን መሞከራቸው አይቀርም።

የህጻኑን ዕድሜ መሰረት ያደረጉ እንቅስቃሴዎች እና የጨዋታ ሀሳቦች ጠቅላላ ቅኝት ከዚህ በታች ቀርቧል።

ጨቅላ ህጻናት – ከአንድ ዓመት በታች

እንዲህ ያለው ጨቅላ ህጻን የሚያውቀው ምርጥ መጫወቻ እንክብካቤ ሰጪው ነው። የእንክብካቤ ሰጪአቸውን ፊት ማየት እና የእንክብካቤ ሰጪአቸውን ድምጽ መስማት ለአፍላ ህጻናት ከምንም የበለጠ ጨዋታ ነው – በተለይም ደግሞ ፈገግታ ካገኙ።

  • ሙዚቃ፣ መዝሙሮች እና የሙዚቃ መሳሪያዎች የመስማት እና የመንቀሳቀስ ችሎታን ያዳብራሉ።
  • “አየሁህ” የሚለው ጨዋታ ከእንክብካቤ ሰጪአቸው ጋር በሚለያዩበት ወቅት ያለመፍራትን ለህጻናት ያስተምራል። በዕድሜ ተለቅ ካሉ ልጆች ጋር ድብብቆሽ መጫወትም እንደዚያው።
  • እንደ ላባ፣ ጭቃ እና ብረት ያሉ የተለያዩ ዓይነት ዕቃዎች የመዳበስ የስሜት ህዋስን ያዳብራሉ።
  • የተለያዩ ቅርጾች፣ ትልቀቶች እና ቀለሞች ያሏቸው ዕቃዎች ህጻኑ ተንጠራርቶ እንዲያነሳቸው በማበረታታት ምን ትልቅ እና ምን ትንሽ፣ ከባድ ወይም ቀላል፣ ለስላሳ ወይም ሻካራ፣ ወዘተ እንደሆነ እንዲማር ይረዳሉ።
  • የቤት ዕቃዎች፣ ኳሶች፣ አሻንጉሊቶች እና የሳጥን ቅርጽ ያላቸው ዕቃዎች ህጻኑን ዳዴ እንዲል፣ እንዲቆም እና እንዲራመድ ያበረታቱታል። 
  • በደረት መጋደም እና መሬት ላይ መጫወት አካላዊ ጥንካሬን እና ሰውነትን የመቆጣጠር ችሎታን ያዳብራሉ። 

የቅድመ መደበኛ ትምህርት ዕድሜ ላይ ያሉ ህጻናት – 4-6 ዓመት

  • ማስቀመጫ ዕቃዎች፣ የእንጨት ማንኪያዎች፣ ዱላዎች፣ ባልዲዎች፣ ድስቶች፣ ያረጁ ልብሶች፣ ወዘተ ምናብን የመጠቀም ችሎታን ያዳብራሉ እንዲሁም ላልተደራጁ ጨዋታዎች ጥሩ ናቸው።
  • በድስት ወይም በመጥበሻ የታጀበ ሙዚቃ ለመደነስ፣ ለሙዚቃ ትርዒቶች ወይም ሙዚቃ ለመፍጠር ጥሩ ነው።
  • ኳስ ህጻኑ በእግሩ እንዲመታ፣ እንዲወረውር፣  እንዲቀልብ እና እንዲንከባለል ያበረታታዋል።

ድክ ድክ የሚሉ ህጻናት – 1-3 ዓመት

ድክ ድክ የሚሉ ህጻናት በዙሪያቸው ያለውን አካባቢ ማሰስ እንዲሁም የሰውነታቸውን አቅም እና አካላዊ ጥንካሬአቸውን መፈተሸ ይወዳሉ።

  • እንደ ኳስ ወይም ባልዲ ያሉ የተለያየ ክብደት ያላቸው ዕቃዎች ህጻኑን እንዲሮጥ፣ እንዲገፋ፣ እንዲጎትት ወይም እንዲያንሸራትት ያበረታቱታል።
  • ገመድ፣ ሙዚቃ እና ማስቀመጫ ዕቃዎች ህጻኑን እንዲዘል፣ በእግሩ እንዲመታ፣ እንዲረጋግጥ፣ እንዲራመድ እና እንዲሮጥ ያበረታቱታል።
  • የሳጥን ቅርጽ ያላቸው ዕቃዎች፣ ትላልቅ ድንጋዮች እና ትራሶች ህጻኑን እንዲንጠላጠል፣ ሚዛኑን እንዲጠብቅ፣ እንዲጠማዘዝ ወይም እንዲንከባለል ያበረታቱታል።
  • የተለያዩ ልብሶችን የመልበስ ማንኛውም ዓይነት ጨዋታ ምናብን የመጠቀም እና የፈጠራ ችሎታን ያዳብራል።
  • መዝሙሮች፣ ሙዚቃ እና የሙዚቃ መሳሪያዎች ህጻኑን የተለያዩ ድምጾችን እና ምቶችን እንዲሞክር ያበረታቱታል።

የትምህርት ዕድሜ ላይ ያሉ ልጆች – ከሰባት ዓመት ጀምሮ

  • የቤት ዕቃዎች፣ ናይለን፣ የልብስ ቅርጫት እና ሳጥኖች ትናንሽ መደበቂያዎችን ለመስራት ጥሩ ናቸው። 
  • እንደ ጣውላ፣ የዛፍ ግንድ ቁራጭ፣ ማስታጠቢያ፣ ትልቅ ድንጋይ፣ ወዘተ ካሉ የተለያዩ ቁሳቁሶች የሚሰሩ መሰናክሎች ህጻኑን በተለያዩ መንገዶች፣ አቅጣጫዎች እና ፍጥነት እንዲንቀሳቀስ ያበረታቱታል።
  • ምግብ ማብሰል፣ ምግብ ማዘጋጀት እና አትክልትን የመንከባከብ እንቅስቃሴዎች የቁጥር አጠቃቀምን እና የዕለት ተዕለት ክህሎቶችን ለማዳበር ጥሩ ናቸው።
  • እንደ ሀብል መሥራት፣ ሹሩባ መሥራት እና ቀለም መቀባት ያሉ የእጅ ሥራዎች።

“ጨዋታ ለልጆቼ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አላውቅም ነበር። ከዚህ ቀደም ለመጫወት ጊዜ ማግኘት እና ከልጆቹ አጠገብ መገኘት ከባድ ነው ብዬ አስብ ነበር እንዲሁም ለልጆቼ የሚሆኑ ብዙ መጫወቻዎች አልነበሩኝም። አሁን ግን ከእነሱ ጋር ለመጫወት ጊዜ እመድባለሁ ወይም እነሱ እየተጫወቱ እያለ አጠገባቸው ሆኜ የቤት ውስጥ ሥራዎችን እሰራለሁ። ማግኘት የምንችላቸውን ነገሮች በመጠቀም ብዙ ዓይነት ጨዋታዎችን እንጫወታለን፡- የካይት (kite) ጨዋታ፣ ኳስ፣ አሻንጉሊቶች፣ የመቁጠር ጨዋታዎች፣ የቀለም ጨዋታዎች እና የመሳሰሉትን ማለት ነው። ከልጆቼ ጋር መጫወት በጣም ነው የሚያስደስተኝ።” – እንክብካቤ ሰጪ

እንክብካቤ ሰጪዎች ከልጆቻቸው ጋር መጫወት የሚችሉት እንዴት ነው?
እንክብካቤ ሰጪዎች በህጻናት የሚመሩ ጨዋታዎች ላይ መሳተፍ ይችላሉ። ይህም ዓለምን በልጆቻቸው አይን ለማየት የሚያስችላቸው ድንቅ ዕድል ነው። እንክብካቤ ሰጪዎች በጨዋታ አማካኝነት ከልጆቻቸው ጋር መስተጋብር በሚያደርጉበት ወቅት ህጻናት ሙሉ ትኩረት እየሰጧቸው እንደሆነ እና ግንኙነቶችን እንዲገነቡ እያገዟቸው እንደሆነ ያውቃሉ። ከልጆቻቸው ጋር የሚጫወቱ እንክብካቤ ሰጪዎች ከልጆቻቸው ጋር ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መልኩ እንደሚግባቡ ጥናቶች ያሳያሉ።

ከልጆች ጋር መጫወት በተለይም ደግሞ ድክ ድክ የሚሉበት እና የቅድመ መደበኛ ትምህርት ዕድሜ ላይ እያሉ አስፈላጊ ነው። ህጻኑ ከዋና እንክብካቤ ሰጪው ጋር እንዲሁም ከህጻኑ ጋር ልዩ ግንኙነት ካላቸው ሌሎች አዋቂዎች ጋር መጫወቱ አስፈላጊ ነው።

መፍትሄ የሚያስፈልጓቸው በርካታ ተግባራት ያሉበት እና ሥራ የበዛበት የዕለት ተዕለት ህይወት ያለን ከሆንን ከልጆቻችን ጋር ለመጫወት ጊዜውን እና ጉልበቱን ማግኘት አስቸጋሪ ሊመስለን ይችላል። ነገር ግን ጨዋታ አስቀድሞ የተወሰነ ጊዜ ወይም ደግሞ የተወሰኑ ዕቃዎች ወይም መጫቻዎች አያስፈልጉትም። ጨዋታ እንደ ሁኔታው ሊሆን ይችላል እንዲሁም ህጻናት ምናባቸውን መጠቀም እና መሯሯጥ የሚችሉበት ማንኛውም ቦታ ላይ ሊከናወን ይችላል።

እንክብካቤ ሰጪዎች ልጆቻቸው በሚጫወቱት ጨዋታ ውስጥ እንዲሳተፉ በተለይ ተስማሚ የሆኑ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎችን የተመለከቱ ሀሳቦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

 

  • ተረት ማንበብ እና የህጻናት ማቆያ መዝሙሮችን መዘመር
  • ድብብቆሽ
  • የእግር ጉዞ ማድረግ
  • አትክልትን መንከባከብ
  • ምግብ ማብሰል
  • መዝሙሮችን መዘመር
  • ዳንስ
  • የተለያዩ ልብሶችን የመልበስ ጨዋታ
  • ኳስ በእግር መምታት እና መወርወር
  • የቤት ውስጥ ሥራ

አንዳንድ የዕለት ተዕለት የቤት ውስጥ ሥራዎች በቀላሉ ወደ ጨዋታ ሊቀየሩ ይችላሉ። አስቤዛ ለመግዛት ስትሄዱ ህጻኑን ይዛችሁት ሂዱ እና የተለያዩ እንስሳትን ተመልከቱ፣ መንገድ ላይ ያሉትን ድምጾች አዳምጡ፣ መራመድ የምትችሉባቸው የተለያዩ ዓይነት መሬቶችን ፈልጋችሁ አግኙ፣ ወዘተ። በተጨማሪም አትክልትን በምትንከባከቡበት ወቅት ህጻኑን እንዲቆፍር፣ ውሀ እንዲያጠጣ ወይም በጭቃ ወይም በአሸዋ እንዲጫወት በማድረግ ልታሳትፉት ትችላላችሁ።

ጨዋታ መጫወት ቀላል እና አዝናኝ ሊሆን ይገባል። በዚህ ረገድ ማስታወስ የሚያስፈልጉ አንዳንድ መመሪያዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

  • ህጻኑ ስህተቶችን እንዲሰራ ፍቀዱ። ፍጹም ክህሎትን ለማዳበር የሚቻለው ደጋግመው በመሞከር እና በመሳሳት ብቻ ነው። ይህን ለህጻኑ ንገሩት።
  • ህጻኑ እያደረገ ስላለው ነገር አውሩ፤ ለሚያደርገው ጥረት አድንቁት እንዲሁም አበረታቱት።
  • ህጻኑን አዳምጡት፣ የሚያደርገውን ነገር ተከትላችሁ አድርጉ እንዲሁም ጨዋታውን እንዲለውጥ እና “ሕጎቹን” እንዲወስን ፍቀዱለት።
  • ጨዋታው ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን እና አደገኛ ያለመሆኑን አረጋግጡ።
  • ነገሮችን ከእሱ በተሻለ እንደምታደርጉ ለህጻኑ አታሳዩት። የራሳችሁን ቀላል ስህተት እየሰራችሁ በዚያ ሳቁ።
እንዲደረግ የሚመከር እንቅስቃሴ

ለአንዳንድ እንክብካቤ ሰጪዎች ከልጆቻቸው ጋር የሚጫወቱበት ጊዜ ማግኘት ከባድ ነው። የተለያዩ ቤተሰቦች እና ልጆቻቸው ተገናኝተው የተለያዩ ጨዋታዎችን አብረው የሚጫወቱበት ቀን ማዘጋጀት ትችላላችሁ?