ክፍለ ጊዜ 5/21

ገጽ 2/5 ርዕስ ሀ፡- አካላዊ ማነቃቂያ ለጤናማ የአንጎል ዕድገት እና ሰውን በጣም ለመቅረብ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ርዕስ ሀ፡- አካላዊ ማነቃቂያ ለጤናማ የአንጎል ዕድገት እና ሰውን በጣም ለመቅረብ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ዓመታት አጥቢ እንስሳት በእናት እና በልጅ መካከል የሚደረግ አካላዊ ንክኪን ሲያዳብሩ ቆይተዋል። አብዛኛውን ጊዜ ውሾች፣ ድመቶች፣ ላሞች ወይም ሌሎች ማናቸውም አጥቢ እንስሳት ልጆቻቸውን ከተወለዱ በኋላ ሲልሷቸው እና ከጎናቸው ጋደም በማለት የቅርበት አካላዊ ንክኪ ሲሰጧቸው ታያላችሁ። ይህንንም የሚያደርጉት ሊያጸዷቸው ብቻ ሳይሆን መላስ የእንስሳው ቡችላ አንጎሉ መሥራት እንዲጀምር እና ንቁ እንዲሆን ስለሚያደርግ እና አካላዊ ንክኪም በቡችላው እና “በእናቱ” መካከል በጣም መቀራረብ እና የስነ ልቦና ትስስር መፈጠር እንዲጀምር የሚያደርግ ወሳኝ ነገር በመሆኑም ጭምር ነው።   ከተወለደ በኋላ ያልተላሰ ቡችላ አንጎሉ የማይሰራ በመሆኑ ብዙም ሳይቆይ የመሞት ዕድሉ ሰፊ ነው። “ድባቴ” ትክክለኛ ትርጉሙ “ዝቅተኛ እንቅስቃሴ” ነው፤ ስለዚህ በህጻናት ላይ የሚከሰት ድባቴ መንስኤው የአካላዊ ማነቃቂያ ማነስ ሲሆን ይህም የአንጎል እንቅስቃሴ መጠን ዝቅተኛ መሆንን ያስከትላል። በተለይ በተቋም የታቀፉ እና ቸል የተባሉ ህጻናት የመጀመሪያ ተንከባካቢያቸውን ያጡ ወይም በቂ የሠው ኃይል በሌላቸው ተቋማት ውስጥ በመሆናቸው የተነሳ እንዲህ ላለው ማነቃቂያ ማነስ ተጋላጭ ናቸው። በርካታ ሥራቸውን በአግባቡ መወጣት የማይችሉ ወላጆች ልጆቻቸውን በአካል ማነቃቃት የማይችሉ በመሆኑ በርካታ ህጻናት ተቋማት ወይም የአደራ ቤተሰብ ጋር ከመድረሳቸው በፊት በበቂ ሁኔታ ማነቃቂያ አይደረግላቸውም። 

 

የሰው ልጆች የሚወለዱት በጣም ያልጠነከረ እና ያልረጋ አንጎል ይዘው በመሆኑ የህይወታችን መጀመሪያ ላይ የአንጎል እንቅስቃሴ ሊጨምር እና ሊረጋ የሚችለው ህጻኑ አብዛኛውን ጊዜ በአካላዊ ንክኪ አማካኝነት ከተነቃቃ ብቻ ነው።

በተጨማሪም ከወሊድ በኋላ መነካካት (ቆዳ ለቆዳ የሚደረግ ንክኪ) በጣም ሰውን የመቅረብ ሥርዓቱን “ሥራ ለማስጀመር” በጣም አስፈላጊ ነው። ገና የተወለዱ ህጻናት እናቶች በፈለጉ ጊዜ ሁሉ ልጃቸውን እንዳይነኩ እና እንዳያቅፉ ከተደረጉ ትንሽ ዕድሜ ላይ የሚከሰቱ ሰውን በጣም የመቅረብ ችግሮች ይስተዋላሉ።

ለምሳሌ ከወሊድ አሠራሮች ጋር በተያያዘ በሆስፒታሎች በተሰሩ ጥናቶች፡- ገና የተወለዱ ህጻናት በቀን ውስጥ በተወሰነ ፕሮግራም መሠረት ከእናታቸው ተነጥለው ሲወሰዱ እናቶቹ አብዛኛውን ጊዜ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማቸዋል፣ ህጻኑ ምን እንደሚሰማው እና ምን እንደሚፈልግ ከመረዳት እና የሚሰጣቸውን ምልክቶች ከመተርጎም አንጻር ይበልጥ የመተማመን ስሜት ያንሳቸዋል እንዲሁም ህጻኑን ከመንከባከብ ጋር የተያያዙ ውሳኔዎችን ከመወሰን አንጻር የመተማመን ስሜት ይበልጥ ያንሳቸዋል።

በአካል ተነጣጥለው የሚቆዩበት ጊዜ በጣም ረጅም ከሆነ እናትየው ለልጁ የሚሰማትን የስሜት ቅርበት ልታጣው እና እንደ ባዕድ/ባዳ ልታየው ትችላለች። የቅርበት ስሜት እንዲኖር ከወሊድ በኋላ ለረጅም ጊዜ እናት እና ልጅ በነጻነት አካል ለአካል መነካካት መቻል አለባቸው። ከዜው ቀድሞ የሚወለድ ልጅ እና በወሊድ ወቅት የሚፈጠሩ መወሳሰቦች አስቸጋሪ የሚሆኑት ከህጻኑ አካላዊ ሁኔታ አንጻር ብቻ ሳይሆን ገና የተወለደው እና በቀላሉ ሊጎዳ የሚችለው ህጻን በህክምና ምከንያቶች የተነሳ አብዛኛውን ጊዜ ከእናቱ የሚለይ መሆኑ (ሙቀት ክፍል፣ ወዘተ) እና ይህም በህጻኑ የአንጎል እንቅስቃሴ እንዲሁም እናትየው ለህጻኑ በሚኖራት የቅርበት ስሜት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር መሆኑ ነው። በርካታ የማዋለጃ ሆስፒታል ክፍሎች ውስጥ በዚህ ምክንያት የተነሳ እናቶችን ገና ከተወለደ ልጃቸው እንዲነጠሉ ማድረግ ቀርቷል። 

 

ለምሳሌ ዩቲዩብ ላይ ህጻናትን ማሳጅ የማድረጊያ ዘዴዎችን የሚያሳዩ በርካታ ቪዲዮዎችን ማግኘት
ትችላላችሁ።

ህጻናትን ማሳጅ የማድረጊያ ዘዴዎች ምሳሌ።

እናቶች በሥራ ላይ እያሉም እንኳን ህጻናትን ለማነቃቃት የሚረዱን መገልገያዎች – “ለረጅም ጊዜ ደረት ላይ ማቆየት”

የሰው ልጅ ጎሳዎች ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ሲጀምሩ ህጻናትን ማነቃቂያ እና መመገቢያ ሌሎች መንገዶችን ማግኘት ነበረብን።

ስለዚህ ሴቶች (የሰው ልጆች ሴቶች) ሁለት ጡቶች ብቻ ፊትለፊት ላይ የላይኛው የአካላቸው ክፍል ላይ ብቻ የኖራቸው እና ጥንታዊ የሰው ልጆች ልጃቸውን የሚሸከሙት በክንዳቸው የሆነው። የሰው ልጆች በመላው ዓለም መንሰራፋት የቻሉትም በዚህ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡- ገና የተወለደ ልጅ ያላት እናትም እንኳን ረጅም ርቀት በእግሯ መጓዝ በመቻሏ እና በዚህም የተነሳ የሰው ልጆች በቡድን ተሰባስበው ከቦታ ቦታ መዘዋወር በመቻላቸው። በተጨማሪም የሰው ልጅ ህጻናት በወሊድ ወቅት ጭንቅላታቸው ትልቅ ነው፤ ስለዚህ ልክ እንደ ካንጋሮ የህጻኑ አንጎል ሥራውን ለመሥራት ከመቻሉ ረጅም ጊዜ አስቀድመን መውለድ ይኖርብናል።

ከወሊድ በኋላ ያሉት የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት ላይ “እርግዝናን ከማህጸን ውጭ የምንጨርስበት” ጊዜ ነው ማለት ይቻላል (ህጻኑ በረጋ ሁኔታ አንጎሉ መሥራት የሚጀምረው ከተወለደ በኋላ ከጠኝ እስከ አሥራ ሁለት ወራት ቆይቶ ነው)።


የቡድን ውይይት

10 ደቂቃ

እባካችሁ ምስሎቹን እና ቪዲዮዎቹን ተመልከቱ እና በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡-

  • ወላጆቻችሁ እና አያቶቻችሁ ልጆችን የሚያነቃቁት እንዴት ነበር? ሰውነታቸው ላይ ይሸከሟቸው ነበር?
  • ከምታዩአቸው ውስጥ የሚጠቀሟቸው የማነቃቂያ መገልገያዎች ነበሩ (የልጅ አልጋ፣ በጨርቅ የተወጠረ መተኛ፣ ወዘተ)?
  • ህጻን ልጆች ካሏችሁ ወይም ከነበሯችሁ ከእነዚህ መገልገያዎች ውስጥ የተጠቀማችሁት አለ?
  • በሞያዊ እንክብካቤአችሁ ስር ያሉ ከአንድ ዓመት በታች ዕድሜ ያላቸው ህጻናትን ተመልከቱ፡-
    • አብዛኛውን ጊዜ ሰውነታችሁ ላይ ትሸከሟቸዋላችሁ?
    • ምን ላይ ነው የሚተኙት?
    • እንቅልፍ ላይ ከማይሆኑበት ጊዜ ውስጥ አልጋ ወይም ሌላ የማይንዠዋዠው ወይም የማይንቀሳቀስ ነገር ላይ የሚያሳልፉት ምን ያህሉን ጊዜ ነው? (እንደ አልጋ፣ የታጠረ የህጻን መጫወቻ አልጋ ወይም የቆመ የህጻን ማንሸራሸሪያ ጋሪ ያለ)