ክፍለ ጊዜ 5/21
ገጽ 3/5 አልጋ የህጻን ልጅ አንጎል አንዲሰራ ጥሩ ያልሆነው ለምንድን ነው?አልጋ የህጻን ልጅ አንጎል አንዲሰራ ጥሩ ያልሆነው ለምንድን ነው?
እንዲያውም አንድ ህጻን አልጋ ላይ በሚጋደምበት ወቅት አንጎሉ መስራቱን ይቀንሳል።
ረዘም ላሉ ሠዓታት ሥራ ላይ በምትሆኑበት ወቅት ህጻኑን አልጋ ላይ መተው የለባችሁም ምክንያቱም ልጁ አልጋ ላይ ጋደም ብሎ ሳይንቀሳቀስ ሲቆይ አይነቃቃም። በአንጻሩ ህጻኑን አቅፋችሁት ብትንቀሳቀሱ አንጎሉ ይነቃቃል።
ህጻኑን የተዘጋ የልጅ አልጋ ላይ ከተዋችሁት ህጻኑ የሚኖረው ውስን እይታ ነው እንዲሁም ከሰው ጋር መገናኘት እና በዙሪያው ያለውን የሰው እንቅስቃሴ ማጥናት አይችልም።
የሚንዠዋዠው አልጋ ወይም በተለይም ደግሞ እዚህ ምስል ላይ እንዳለው በጨርቅ የተወጠረ መተኛ ላይ ከሆነ ህጻኑ በቀስታ ይንዠዋዠዋል፣ ጨርቆቹ ያነቃቁታል፣ በዙሪያው ያለውን ነገር ማጥናት ይችላል እንዲሁም ሊወድቅ አይችልም።
አካላዊ ማነቃቀቂያ የአንጎል ሥራን የሚቆጣጠረው እንዴት ነው? የቆዳ ለቆዳ ንክኪ እና የሚዛን ማነቃቂያ
መሠረታዊ የአንጎል ሥራን ለመጨመር በጣም አስፈላጊ የሆኑት የሚከተሉት ሁለት ዓይነት ማነቃቂያዎች እንደሆኑ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡-
ቆዳን ማነቃቃት፡- ምላስ እና አፍ። ለምሳሌ ህጻኑ ሲጠባ፣ ወይም የተንከባካቢው ክንድ ላይ ሲተኛ፣ ወይም ሰውነቷ ላይ በጨርቅ ሲታቀፍ፣ ወይም ከአንሶላ በላይ መነቃቃትን በሚፈጥር ማቀፊያ ጨርቅ ሲጠቀለል። ህጻናት ከተንከባካቢዎቻቸው አካላዊ ንክኪ ለማግኘት ጥረት በማድረግ የቆዳ ለቆዳ ንክኪን ሆነ ብለው ይፈልጋሉ።
የሚዛን ማነቃቃት፡- (ማንዠዠዋዠው፣ ማቆም፣ ማንቀሳቀስ፣ ሰውነቱን ማዞር)። ለምሳሌ እንክብካቤ ሰጪዋ ህጻኑን አቅፋ ስትንቀሳቀስ፣ የሚንዠዋዠው አልጋው ወይም በጨርቅ የተወጠረ መተኛው ግራና ቀኝ ሲንቀሳቀስ፣ እንክብካቤ ሰጪዋ “ህጻኑን አየር ላይ አየወረወረች” ስታስቀው። ህጻናት ራሳቸውን እስኪያዞራቸው ድረስ በማሽከርከር፣ ከፍና ዝቅ በሚያደርጉ ነገሮች፣ በዥዋዥዌ፣ በሚሽከረከሩ ነገሮች እና በሌሎች የሚዛን ማነቀቃቂያ እንቅስቃሴዎች በመደሰት የሚዛን ማነቃቃትን ሆነ ብለው ይፈልጋሉ።
ከጊዜያቸው ቀድመው በተወለዱ እና አነስተኛ ክብደት ኖሯቸው በተወለዱ ህጻናት ላይ ከተሰሩ የተለያዩ ጥናቶች የተገኙ አንዳንድ ምሳሌዎች፡-
-
- የሙቀት ክፍል ውስጥ ምንም እንቅስቃሴ የለም እንዲሁም አነስተኛ የቆዳ ማነቃቂያ ነው ያለው። ህጻናት ከለስላሳ አንሶላ ይልቅ በሙቀት ውስጥ ያለፈ የጠቦት ቆዳ ላይ እንዲተኙ ቢደረጉ ከጠቦት ቆዳው የሚያገኙት መነቃቃት አንጎላቸውን ይበልጥ የሚያሰራው በመሆኑ (ይህም የሰውነታቸውን ምግብ የመፍጨት ሂደት የሚደግፈው በመሆኑ) በቀን 15 ግራም ይበልጥ ክብደታቸውይጨምራል።
- የሙቀት ክፍል ውስጥ ያሉ ህጻናትን የጭንቅላታቸውን የኋላ ክፍል በሠዓት አንድ ጊዜ ለሁለት ደቂቃ ያህል በጣታችሁ ጫፍ በስሱ ከደባበሳችሁት 20 በመቶ ይበልጥ ጋስትሪክ አሲድ ያመነጫሉ፤ይህም የምግብ ፍላጎታቸው እና ክብደታቸው ይበልጥ እንዲጨምር ያደርጋል።
- የሙቀት ክፍል እና ህክምና በሌለባቸው ሀገራት “የካንጋሮ ዘዴ”ን ከተጠቀምን (ህጻኑን እንክብካቤ ሰጪዋ ቀኑን ሙሉ ካቀፈችው) ከጊዜያቸው ቀድመው የተወለዱ ህጻናት በጣም የተሻለ በህይወት የመቆየት ዕድል ይኖራቸዋል። ይህን ዘዴ ከክፍለ ጊዜው በኋላ እዚህ ይበልጥ ልትለማመዱት ትችላላችሁ።
ህጻኑ አብዛኛውን ጊዜ በተንከባካቢዎቹ ከተደባበሰ ወይም ከተንዠዋዠወ የሰውነቱ መሠረታዊ ተግባራት (የልብ ምት፣ ትንፋሽ፣ የምግብ ፍላጎት፣ ምግብ መፍጨት፣ የእንቅልፍ፣ ንቃት፣ ከሰው ጋር አይን ለአየን መተያየት እና ትኩረት) ቀስ በቀስ እየተረጋጉ እንደሚመጡ ሌሎች ጥናቶች ይጠቁማሉ።
ይህችን እናት እንደገና ብታጠኗት ምን ያህል ንክኪ እና ማንዠዋዠውን እንደምትጠቀም እና ይህም ምን ያህል ህጻኑን ምላሽ እንዲሰጥ እና ንቁ እንዲሆን እንደሚያደርገው ማየት ትችላላችሁ።
በቀላሉ ሊጎዱ የሚችሉ ህጻናትን እና በቂ ማነቃቂያ ያላገኙ ህጻናትን ማነቃቃት
በቂ ማነቃቂያ ያላገኙ ህጻናት እና ከጊዜያቸው ቀድመው የተወለዱ ህጻናት ከመደበኛው ይልቅ ማነቃቂያ በቀላሉ ተጽዕኖ የሚያሳድርባቸው በመሆኑ ሆነ ብለው ከሚያነቃቃ ነገር ለመራቅ ጥረት ያደርጋሉ። አንድ ህጻን በይበልጥ ማነቃቂያ በቀላሉ ተጽዕኖ የሚያሳድርበት በሆነ ቁጥር፡-
- የምታነቃቁት በጣም በቀስታ መሆን አለበት (ለምሳሌ በጣም እንቅስቃሴ ሳታደርጉ ወይም በጣም ጮክ ብላችሁ ሳታወሩ ህጻኑን ክንዳችሁ ላይ ማቀፍ። ህጻኑን ለተወሰኑ ሰከንዶች በጣም በቀስታ ማንዠዋዠው፤ ምን ዓይነት ምላሽ እንደሚሰጥ ማየት እና ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ያንኑ ደግሞ ማድረግ)።
- ለአጭር ሠዓት ያህል ወዲያው ወዲያው በማነቃቃት መጀመር እና ቀስ በቀስ ረዘም ላለ ሠዓት ማነቃቃት አለባችሁ (ለምሳሌ ለተወሰኑ ሰከንዶች ህጻኑን በማንዠዋዠው ጀምራችሁ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ መድገም፤ ከዚያም በየቀኑ ትንሽ ረዘም ላለ ጊዜ ማንዠዋዠው እና ትንሽ የበለጠ መደባበስ)።
- ከመጠን በላይ ማነቃቃታችሁን የሚጠቁሙ ምልክቶችን ማስተዋል አለባችሁ። ህጻኑ ሊደነግጥ፣ ዞር ለማለት ሊሞክር ወይም ማልቀስ ሊጀምር ይችላል። አንድ ህጻን እንዲነቃቃ ከተደረገ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ ማረፍ ያስፈልገዋል። ልጁ ምን ያህል ማነቃቂያ እንደሚበቃው እና ለህጻኑ የሚስማማውን የማነቃቂያ አካሄድ ለማወቅ ሞክሩ። ይህ አካሄድ ከህጻን ህጻን በጣም ይለያያል።
እናታቸው በእርግዝና ወቅት አልኮል መጠጣቷ ተጽዕኖ ያሳደረባቸው (በአልኮል የተነሳ በጽንስ ላይ የሚፈጠር ተጽዕኖ/Foetal Alcohol Effects (FAE) ወይም የባሰ ከሆነ ደግሞ በአልኮል የተነሳ በጽንስ ላይ የሚፈጠር በሽታ/Foetal Alcohol Syndrome (FAS) ያለባቸው) ህጻናት ማነቃቂያ በጣም በቀላሉ የሚሰማቸው በመሆኑ ክፍላቸው ጠንካራ ብርሀን ሊኖረው አይገባም እንዲሁም ሰዎች በቀስታ መንቀሳቀስ እና ድምጻቸውን ቀንሰው ማውራት እንዲሁም እነዚህን ህጻናት ጭናቸው ላይ አስቀምጠው ጸጥ ብለው መቀመጥ አለባቸው።
የሚከተለው ድረገጽ ላይ ስለ ማነቃቃት ይበልጥ ማንበብ ትችላላችሁ፡- www.nofas.org/living/strategy.aspx
FAE እና FAS አብዛኛውን ጊዜ ዕድሜ ልክ የሚቆዩ ችግሮችን ያስከትላሉ።
አግባብ ያልሆነ የአልኮል እና የዕፅ አጠቃቀም፡-የዕፅ ተጽዕኖ ያሳደረባቸው ህጻናት ከሚያሳዩአቸው የተለመዱ ምልክቶች ውስጥ ከመጠን በላይ መንቀልቀል፣ ደካማ አመጋገብ፣ ፈጣን የልብ ምት፣ ከመጠን በላይ መወራጨት እና ደካማ እንቅልፍ አተኛኝ ይገኙበታል። ሲወለዱ ክብደት ዝቅተኛ መሆን፣ ዝቅተኛ የApgar ነጥብ (ትንፋሽን፣ የልብ ምትን እና ንጥቀትን ጨምሮ የህጻኑን አጠቃላይ ጤና የሚለካ መለኪያ) ማስመዝገብ እና ከመደበኛው ያነሰ የጭንቅላት ትልቀት ከሌሎች የተለመዱ ምልክቶች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው። ነገር ግን እነዚህ ምልክቶች አብዛኛውን ጊዜ የሚፈጠሩት እናትየው በአጠቃላይ ደስታ ያጣች በመሆኗ ስለሆነ ህጻኑ ከተወለደ በኋላ ጤናማ ተንከባካቢ ከተመደበለት አብዛኛዎቹ እነዚህ ችግሮች ይጠፋሉ።ስለዚህ ህጻኑን እንደተወለደ ወዲያውኑ ተቋም ውስጥ ወይም የአደራ ቤተሰብ ውስጥ ማስገባት በጣም አስፈላጊ ነው።
የሚጥል በሽታ ላለባቸው ህጻናት የሚሰጣቸው ማነቃቂያ መታቀድ ያለበት ከተቻለ ከህክምና ድጋፍ ጋር ነው። የሚጥል በሽታ ያለባቸው ህጻናት በጣም በፍጥነት ወይም በኃይል ማነቃቂያ ከተደረገላቸው በሽታው ሊነሳባቸው ይችላል።
10 ደቂቃ
- ህጻናት ወደ እንክብካቤ ሰጪዎቻቸው ሰውነት ጠጋ ተደርገው መታቀፋቸው አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
- በባህላችሁ መሠረት እናት በሥራ በምትጠበድበት ጊዜ ህጻን ልጅን ለማነቃቃት ጥቅም ላይ የሚውሉት ምን ዓይነት ዘዴዎች ናቸው?
- አልጋ ላይ ተጋድመው የሚያሳልፉት ጊዜ በቀን ወቅት በተፈጥሮ እንቅልፍ ለሚወስዳቸው ሠዓት ያህል ብቻ መሆን ያለበት ለምንድን ነው?
- ህጸናት ጤናማ በሆነ መልኩ አንጎላቸው እንዲሰራ በጣም ተመራጭ የሆኑት ማነቃቂያዎች እንዴት ያሉት ናቸው?
- በጣም ጥንቃቄ ማድረግ ያለባችሁ ምን ዓይነት ህጻናትን ስታነቃቁ ነው?