ክፍለ ጊዜ 5/21
ገጽ 4/5 ርዕስ ለ፡- የአስተማማኝ መሠረት ሞዴልን ተከትላችሁ ለህጻናት አነቃቂ የሆነ አካባቢን ለመፍጠር ዕቅድ ማዘጋጀትርዕስ ለ፡- የአስተማማኝ መሠረት ሞዴልን ተከትላችሁ ለህጻናት አነቃቂ የሆነ አካባቢን ለመፍጠር ዕቅድ ማዘጋጀት
”ህጻን ልጅ ነበረኝ። ሁል ጊዜ ራሱን ይነቀንቅ እና የእጁን ጀርባ ይልስ ነበር። ከዚህ ቀደም እንደዚያ ዓይነት ህጻናት አይቼ ስለማውቅ የአእምሮ ዝግመት አለበት የሚል ሀሳብ አቅርቤ ነበር። በዚህ ክፍለ ጊዜ ውስጥ የተማርኳቸውን ዘዴዎች በዚህ ልጅ ላይ ይበልጥ አዘውትሬ እንዲሁም አብዝቼ ተጠቀምኩኝ። አሁን በሥነ ሥርዓት የሚቀመጥ ከመሆኑም በተጨማሪ እጁን አይልስም እንዲሁም አይወዛወዝም። አንዳንድ ጊዜ ግን ጥፍሩን ይበላል። ነገር ግን ይህንንም ችግር እወጣዋለሁ።”
ከተንከባካቢ የተሰጠ አስተያየት
አብዛኛውን ጊዜ የአደራ ቤተሰብ ወላጆች በቂ ማነቃቂያ ያላገኙ ህጻናት ማነቃቂያ ምን ያህል እንደሚያስፈልጋቸው ግንዛቤው የላቸውም።በዚህም የተነሳ የሚከተሉት ሁለት ነገሮች በጣም አስፈላጊ ናቸው፡-
1.በአጠቃላይ አነቃቂ የሆነ አካባቢን በተለይም ደግሞ በቀን ወቅት መፍጠር የምትችሉት እንዴት ነው?
2.ለህጻናት መደበኛ እናቶች በተፈጥሮ የሚሰጡትን ያህል አካላዊ ንክኪ መስጠት በማትችሉበት ጊዜ ህጻናትን ለማነቃቃት “የእናት መገልገያዎችን” መጠቀም የምትችሉት በምን መልኩ ነው?
በተቀረው የዚህ ክፍለ ጊዜ ክፍል ውስጥ ስለ አሠራሮች እና ለሥራ ቦታችሁ ተስማሚ በሆነ መልኩ ለውጥ ልታደርጉባቸው ስለምትችሉባቸው መንገዶች በርካታ የተለያዩ ምክሮችን ታገኛላችሁ። |
ምን አልባትም ብዙ የተለያዩ አዳዲስ አሠራሮችን እስከምታዘጋጁ ድረስ ይህን በርካታ ጊዜ መደጋገም ሊያስፈልጋችሁ ይችላል። እነዚህን ለውጦች በምታደርጉበት ጊዜ የዕለት ተዕለት ህይወታችሁ በተወሰነ መልኩ ይበልጥ እንደተቃወሰ እና ለማስተካከል አስቸጋሪ እንደሆነ ሊሰማችሁ ይችላል። |
የአካባቢዎችን አነቃቂነት ለማሻሻል የሚረዱ ምክሮች
- ህጻናትን አብዛኛውን ጊዜ የምናቅፍበትን፣ መልካም ስሜትን በሚገልጽ መልኩ ትከሻቸውን መታ መታ የምናደርግበትን፣ ወዲያና ወዲህ የምናወዛውዝበትን፣ አብረናቸው ስንራመድ እጃቸውን የምንይዝበትን ባህል ለመፍጠር የምንችለው እና በአጠቃላይ አካላዊ ቅርበትን የሚደግፉ በርካታ ልማዶች ሊኖሩን የሚችለው እንዴት ነው?
- ልጆችን አብዛኛውን ጊዜ ማቀፍን ወይም ጭናችሁ ላይ አስቀምጣችኋቸው መቀመጥን የተለመደ አሠራር ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው? እንክብካቤ ሰጪው ላይ ሊደረጉ የሚችሉ እንደ ማንጠልጠያ ጨርቅ ወይም ማዘያ ቦርሳ ያሉ ምን መገልገያዎችን ብትጠቀሙ ይበልጥ ይቀልላችኋል?
አልጋዎችን ለማሻሻል ወይም በጨርቅ በተወጠረ መተኛ ወይም በሚንዠዋዠው አልጋ ለመተካት ዕቅድ አዘጋጁ
- አንድ አልጋ በበርካታ መንገዶች ሊሻሻል ይችላል፡- በአንሶላ ፋንታ የቆዳ መነቃቃትን የሚፈጥሩ ጨርቆችን እና የመጠቅለያ ጨርቆችን በመጠቀም (አልጋው ከመጠን በላይ የማይሞቅ መሆኑን አረጋግጡ)። በተጨማሪም ልክ ከፍራሹ በላይ እንዲውል እና በነጻነት እንዲወዛወዝ አድርጋችሁ ጨርቅ ሰፍታችሁ በሁለቱ የአልጋው መደገፊያዎች ላይ ልትወጥሩ ትችላላችሁ። ወይም ደግሞ አልጋውን ሙሉ በሙሉ ትታችሁ መሬት ላይ ከተቀመጠ ለስላሳ ፍራሽ በላይ ጨርቅ መወጠር ትችላላችሁ። በተጨማሪም ህጻኑ እንቅልፍ ላይ በማይሆንበት ሠዓት በዙሪያው የሚደረገውን ነገር ማየት እንዲችል አልጋዎች ላይ ለውጦችን ማድረግ ይቻላል።
ድክ ድክ ለሚሉ ህጻናት ክፍል ውስጥ ወይም ግቢ ውስጥ ፍራሽ አድርጋችሁ ከላዩ ጨርቅ ወይም መንዠዋዠዊያ ልትወጥሩላቸው ትችላላችሁ እንዲሁም የህጻናቱን ሚዛን የሚያነቃቁ የዕለት ተዕለት ተግባራትን ልታቅዱ ትችላላችሁ።
ይህን በምታቅዱበት ጊዜ፡- እነዚህ መገልገያዎች የተለዩ ክፍሎች ውስጥ መቀመጥ እንደሌለባቸው አስታውሱ። እንደዚያ ካደረጋችሁ ህጻናቱ ብዙም አይጠቀሟቸውም። በተቻለ መጠን መቀመጥ ያለባቸው እንክብካቤ ሰጪዎቹ ጊዜያቸውን ወደሚያሳልፉበት ቦታ ተጠግተው ነው። ለመጫወቻ ስፍራው እንደ ዥዋዥዌ፣ መሽከርከሪያ እና ሌሎች ሚዛንን የሚያነቃቁ መሳሪያዎች ያሉ ነገሮችን መሥራት ወይም ማግኘት የምትችሉት እንዴት ነው?
- ከአልጋው በላይ (እንደ ሞባይል ያሉ) መሳጭ ነገሮችን ማንጠልጠል ወይም ደግሞ ህጻናቱ አልጋቸው ላይ ሆነው ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ማየት የሚችሏቸው ነገሮችን ማግኘት የምትችሉት እንዴት ነው?
- ግድግዳዎችን ብሩህ እና የተለያዩ ቀለሞች ልትቀቧቸው እና ዕቃዎችን እና ስዕሎችን ልትሰቅሉባቸው የምትችሉት እንዴት ነው?
- ራሳችሁ የምታዘጋጇቸውን መዝሙሮች እና ሙዚቃ መጠቀም የምትችሉት እንዴት ነው? ለህጻናት መዝሙር መዘመር እና ከልጆች ጋር አብሮ መዘመር ለቋንቋ ዕድገት አስፈላጊ ነው። ህጻናትን ለማስተኛት የሚዘመሩ መዝሙሮች የህጻናትን አንጎል በጣም ዘና ያደርጋሉ። እንደ ማንኪያ፣ ማስታጠቢያ፣ ወዘተ ያሉ ከሞላ ጎደል ማናቸውንም ነገሮች እንደ ከበሮ መጠቀም ይቻላል።
በአጠቃላይ ከሬዲዮ እና ከቴሌቪዥን የሚወጡ ድምጾች የህጻናትን አንጎል አያነቃቁም። ነገር ግን እናታቸው ወይም እንክብካቤ ሰጪያቸው ስትዘምር አንጎላቸው በጣም እንደሚነቃቃ ጥናቶች ያሳያሉ። ስለዚህ አብዛኛውን ጊዜ ስታዩአቸው ዘምሩላቸው እንዲሁም አናግሯቸው። በተጨማሪም ይህን ማድረግ በጣም በተሻለ ሁኔታ ቋንቋ እንዲማሩ ይረደቸዋል። ከወላጆቻችሁ እና ከአያቶቻችሁ የተማራችኋቸውን የራሳችሁ ሰዎች ህጻንን ለማስተኛት የሚጠቀሟቸውን መዝሙሮች አስቧቸው (እና ዘምሯቸው)!