ክፍለ ጊዜ 7/19
ገጽ 3/5 ርዕስ ሀ፡- 0-3 ዕድሜርዕስ ሀ፡- 0-3 ዕድሜ
ሰውን ማጣትን እንዲቋቋሙ ለህጻናት እገዛ ማድረግ፡- ለመለየት የሚሰጡ ምላሾችን ክብደት መቀነስ
ሥራችሁ ግቡ “ህጻኑ ሁል ጊዜ ደስተኛ እንዲሆን ማድረግ” አይደለም። ህጻኑ ለመለያየት የሚሰጠውን ምላሽ ቀስ በቀስ ለመቀነስ ከቻላችሁ መደበኛ በሆነ መልኩ ምላሽ እንዲሰጥ ህጻኑን ረድታችሁታል ማለት ነው። ሙሉ በሙሉ መደንዘዝ ጠቃሚ አይይለም፤ ነገር ግን ትንሽ አይን አፋር እና ለስሜት ቅርብ መሆን ጤናማ ነው። ብቸኛው ልዩነት ምላሹ ምን ያህል ከባድ ነው የሚለው ነው። ከክፍሉ ስትወጡ ከፍተኛ የመረበሽ ስሜት ውስጥ መግባት ጤናማ አይደለም፤ ነገር ግን ስትሄዱ ማልቀስ እና ትንሽ ማዘን ፍጹም ጤናማ ነው።
የሚከተሉት ልትጠቀሟቸው የምትችሏቸው ምክሮች ናቸው። ምንድን ነው የሚጠቅመው የሚለውን በብዛት የሚወስነው እንክብካቤ በሚሰጡት የአደራ ቤተሰብ ወላጆች እና በህጻኑ መካከል ያለው የግል ግንኙነት ነው። ስለዚህ “ትክክለኛውን ነገር” ለማድረግ አትሞክሩ። ስሜትን ለማገናዘብ ሞክሩ፣ መፍትሄዎቹን በራሳችሁ መንገድ አቀናጅታችሁ ተጠቀሙ እንዲሁም ህጻኑ ለምታደርጉት ጥረት የሚሰጠው ምላሽ ምን እንደሚመስል በየቀኑ ማስታወሻዎችን ያዙ።
የሚመከሩ መልመጃዎች
- “የአስተማማኝ እንክብካቤ ሰጪ ባህሪ” የሚያካትታቸውን አምስት ነገሮች ተለማመዱ (ክፍለ ጊዜ 6፣ የርዕስ መግቢያ ለ፡- የአስተማማኝ እንክብካቤ ሰጪ ባህሪ የሚያካትታቸው ነገሮችን ተመልከቱ)። በጣም ከደነዘዘ ወይም ካለማቋረጥ ይዞ አልለቅም ከሚል ህጻን አጠገብ ሆነው አሉታዊ ተጽዕኖ ውስጥ ያለመውደቅ ከባድ ነው። ምንም እንኳን ህጻኑ መደበኛ በሆነ መልኩ ምላሽ የማይሰጥ ቢሆንም ራሳችሁን ደስተኛ ለማድረግ ራሳችሁ ስለሚሰማችሁ ስሜት ሌሎች ሰዎችን (ባላችሁን፣ ጓደኞቻችሁን) መደበኛ በሆነ መልኩ በየጊዜው ማነጋገር አለባችሁ።
- አካላዊ ንክኪን መጠቀም – እንደ የህጻን ልጅ ማሳጅ ወይም ህጻኑን ሰውነታችሁ ላይ ማቀፍ ያለ አካላዊ ንክኪ ሰውን በጣም የመቅረብ ሥርዓቱን ጤናማ በሆነ መልኩ እንዲሰራ ያነቃቃዋል። ህጻኑ መታቀፍን፣ መሳምን፣ ጭናችሁ ላይ መቀመጥን ወይም እሹሩሩ መባልን እንደመውደድ ያሉ ይበልጥ ጤናማ የሆኑ ሰውን በጣም የመቅረብ ባህሪያት እስኪያሳይ ድረስ ወራት ሊወስድበት ስለሚችል በጣም ትዕግስተኛ ሁኑ (ማበረታቻ እንዲሆናችሁ ክፍለ ጊዜ 5ን ተመልከቱ)።
- ከህጻኑ ጋር በምትገናኙበት ወቅት ስሜትን የምታንጸባርቁ እና ስሜታችሁ የሚነበብ እንዲሁም ምላሽ ሰጪነታችሁ የተጋነነ መሆኑን በጣም አስተውሉ። ስሜት የማይነበብበት ፊት የሚለው ሙከራ የመጀመሪያው ክፍል ላይ ያለችውን እናት እንደገና በመመልከት እንዴት ድምጿን እና ሰውነቷን በመጠቀም ህጻኑን መስተጋብር እንዲያደርግ እንደምትጋብዘው ማስተዋል ትችላላችሁ።
“ሁል ጊዜም ከጎኑ” እንደምትሆኑ ለህጻኑ አሳዩት እንዲሁም ህጻናት በመደበኛው ከሚፈልጉት በላይ ለረጅም ጊዜ የደህንነት ስሜት እንዲሰማቸው እና ከጎናቸው እንድትሆኑ እንደሚፈልጉ አስቀድማችሁ ጠብቁ። - ከህጻኑ ጋር በየጊዜው “ድብብቆሽ” ተጫወቱ። እንዲህ ያለው ጨዋታ ህጻኑ መለያየትን እንደ አስደሳች እና አዝናኝ ነገር አድርጎ በማየት እንዲቋቋመው ይረዳዋል። በተጨማሪም ይህ እንቅስቃሴ ሁል ጊዜም በውስጡ የሚኖር እናንተን የሚገልጽ “የውስጥ ምስል” እንዲፈጥር ይረዳዋል፤ ይህም በአካል መኖራችሁን የመፈለጉን ሁኔታ ይቀንሰዋል። በተጨማሪም ዕቃዎችን ደብቃችሁ ህጻኑ እንዲፈልጋቸው ልታደርጉ ትችላላችሁ፤ ይህን ማድረግም እንዲሁ ህጻኑ ሰዎች እና ዕቃዎች ምንም እንኳን ልናያቸው ወይም ልንሰማቸው ባንችልም እንደሚኖሩ እንዲገነዘብ ይረዳል።
- ህጻኑ ይህን ለመገንዘብ የሚያስችል ዕድሜ ላይ ያለ ከሆነ፡- የእንቅልፍ ሠዓት ላይ ከህጻኑ ክፍል ከመውጣት ይልቅ የሚከተለውን ጨዋታ ልትጫወቱ ትችላላችሁ፡- ህጻኑ እራሱ ከመኝታ ክፍሉ “ውጡ” እንዲላችሁ እና ከፈራ ተመልሳችሁ እንድትመጡ እንዲጠራችሁ ማድረግ። ይህን በምታደርጉበት ወቅት ከእሱ ቁጥጥር ውጭ በሆነ መልኩ “ተትቶ ከመኬድ” ይልቅ መለያየቱን መቆጣጠር የመቻል ስሜት ሊሰማው ይችላል። ከዚያ በኋላ ረዘም ላለ ጊዜ ከመኝታ ክፍሉ “ውጡ” ብሏችሁ ስለቆየ ጀግና ብላችሁ ልታደንቁት ትችላላችሁ። ህጻኑ ወደ አልጋው መልሶ ሊስባችሁ እንዲችል ቀሚሳችሁ ላይ ገመድ ማሰር ትችላላችሁ። ይህ ጨዋታ በጣም የሚያዝናና ነው!
ከላይ የተገለጹትን ዘዴዎች በምን መልኩ አቀናጅታችሁ ለመጠቀም እንደምትሞክሩ ከወሰናችሁ በኋላ ጻፏቸው እንዲሁም ህጻኑ በጣም አዎንታዊ ምላሽ የሚሰጠው ምን ስታደርጉ እንደሆነ ጻፉ። የሞባይል ስልካችሁን በመጠቀም እንቅስቃሴዎቻችሁን የሚያሳዩ አጭር ቪዲዮዎችን ቅረጹ እና ህጻኑ የሚሰጠውን ምላሽ ለመረዳት ተመልከቷቸው። የህጻኑን ፊት እና የሚነበቡበትን ስሜቶች ለማየት በሚያስችላችሁ መልኩ አስጠግታችሁ መቅረጻችሁን አረጋግጡ።
እዚህ ጋር አፍቃሪ ልብ ያላት እንክብካቤ ሰጪ ያለችበት ቪዲዮ ቀርቦላችኋል። እባካችሁ እንክብካቤ ሰጪዋ ህጻኑን የመረጋጋት እና የመተማመን ስሜት እንዲሰማው ድምጿን እንዴት እንደምትጠቀም እና ህጻኑን እሹሩሩ እንደምትለው አስተውሉ። በተጨማሪም እንክብካቤ ሰጪዋ ህጻኑን አይን ለአይን ማየቷ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህን ማድረጓ ሀጻኑ መስተጋብር እንዲሰማው እና ማድረግ እንዲችል ይረዳዋል።
ህጻኑ ዕድሜው 3 ዓመት ከመሆኑ በፊት ከእኛ ጋር በሚመደብበት ጊዜ ምን መጠበቅ አለብን?
በአጠቃላይ 3 ዓመት ሳይሞላቸው የአደራ ቤተሰብ ውስጥ የሚመደቡ ህጻናት ሰውን እንደሁኔታው የመቅረብ አዝማሚያ አላቸው። አብዛኛዎቹ ህጻናት የራሳቸው ወላጅ የሆኑ ያህል ከአንደኛው ወይም ከሁለቱም የአደራ ቤተሰብ ወላጆች ጋር ይበልጥ መቀራራብ ሊችሉ ይችላሉ። ህጻናት አብዛኛውን ጊዜ ከተፈጥሮ ወላጆቻቸው የተማሯቸውን ሰውን የመቅረብ ባህሪያት አስወግደው የአዲሱ አንደኛ ደረጃ እንክብካቤ ሰጪያቸውን ባህሪያት ይከተላሉ። በተጨማሪም ዕድሜያቸው ከፍ ካለ በኋላ ከሚመደቡ ህጻናት ጋር ሲነጻጸሩ በሰብዕና እና በማህበራዊ ዕድገት ይበልጥ የአደራ ቤተሰብ ወላጆቻቸውን የመምሰል አዝማሚያ አላቸው። ነገር ግን ህጻኑ የአደራ ቤተሰብ ወላጆቹ እንደመሆናችሁ መጠን ከእናንተ ጋር ትስስር መፍጠር እስከሚችል ድረስ የተፈጠሮ ወላጆቹን ማጣቱን እንዲለምደው ረጅም ጊዜ ልትሰጡት ይገባል።