ክፍለ ጊዜ 1/21

ገጽ 1/5፡- የመማር እና የዕድገት ሂደታችሁን የተመለከተ መሠረታዊ ግንዛቤ ማስጨበጫ

የመማር እና የዕድገት ሂደታችሁን የተመለከተ መሠረታዊ ግንዛቤ ማስጨበጫ

የዚህ ማቴሪያል አጠቃቀም፡-

 ይህ የስልጠና ፕሮግራም እንደናንተ ባሉ ሰዎች የተዘጋጀ እና በዕለት ተዕለት አሠራሮች የተፈተሸ ነው፡- ከህጻናት ማሳደጊያ ውጭ ከተመደቡ ታዳጊ ህጻናት ጋር የተያያዘ ሥራ በሚሠሩ በአሥር ሀገራት የሚገኙ የአደራ ቤተሰብ ወላጆች ማለት ነው። 

በህጻናት ዕድገት ዙሪያ የሚሠሩ በርካታ ተመራማሪዎች እና ባለሞያዎች በእንክብካቤ ላይ ያሉ ህጻናት ያሏቸው ፍላጎቶች ምንድን ናቸው በሚለው ጉዳይ ላይ ዕውቀታቸውን አጋርተዋል። ጥራት ያለው እንክብካቤን በተመለከተ በቪዲዮ በሚቀርቡ ማሳያዎች፣ በአስተያየቶች እና በቡድን ውይይቶች አማካኝነት እንደ እንክብካቤ ሰጪ የሚጠቅሟችሁ ብዙ ክህሎቶችን ትማራላችሁ። ህጻናቱም ይበልጥ ያድጋሉ እንዲሁም ይበልጥ ይማራሉ።

የእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ በክፍለ ጊዜው የተማራችሁትን ነገር እንዴት ተግባር ላይ እንደምታውሉት ትወስናላችሁ። ይህ ሁሉ ትምህርት ጥቅም የሚኖረው የዕለት ተዕለት ሥራችሁ ላይ ከተጠቀማችሁት እና በፕሮግራሙ ውስጥ በምታልፉበት ወቅት የአደራ ቤተሰብ ወላጅ እንደመሆናችሁ መጠን አሠራራችሁን እንዴት እንደምትቀይሩ የምታቅዱ ከሆነ ብቻ ነው።

 

የክፍለ ጊዜው ጭብጥ፡-

በዚህ የመጀመሪያ የስልጠና ክፍለ ጊዜ ስለ የግምገማ ወረቀት፣ ስለዚህ የስልጠና ፕሮግራም መሠረታዊ ሀሳቦች እና ይዘት እና ክፍለ ጊዜዎቹን መከታተል ስለምትችሉበት መንገድ መሠረታዊ ግንዛቤ ታገኛላችሁ። በተጨማሪም እንደ የአደራ ቤተሰብ ወላጅ በምትሰሩት ሞያዊ ሥራ ከራሳችሁ የህይወት ተሞክሮ ያገኛችሁት ምን ያህል ጠቃሚ ዕውቀት  እንዳላችሁ እንድትገነዘቡ ከሌላ የአደራ ቤተሰብ ወላጅ ጋር ሁለት ሁለት በመሆን የሚደረግ ቃለ መጠይቅ ይቀርብላችኋል። በፕሮግራሙ ውስጥ ስለ የህጻናት እንክብካቤ ሞያ ንድፈ ሀሳብ በምትማሩበት ወቅት ምን እንደሚጠበቅባችሁ እንዲሁም እናንተ እና አሰልጣኛችሁ ፕሮግራሙን በምትጠቀሙበት ወቅት እንዴት መደጋገፍ እንደምትችሉ ግንዛቤ ታገኛላችሁ።

 

የክፍለ ጊዜው ዓላማዎች፡-

  •  የስልጠና ፕሮግራሙን እንዴት መከታተል እንዳለባችሁ፣ ለክፍለ ጊዜዎቹ በምንሰበሰብበት ወቅት እንዴት አብራችሁ መሥራት እንዳለባችሁ እና በክፍለ ጊዜዎች መካከል በየቤታችሁ እንዴት መሥራት እንዳለባችሁ ግንዛቤ ማግኘት።
  •  የራሳችሁ የህይወት ተሞክሮ ለአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ሥራ እንዴት የሚጠቅም ሞያዊ ዕውቀት እንደሚያስገኝ መገንዘብ።

•  ስለ የግምገማ ወረቀት መሠረታዊ ግንዛቤ መጨበጥ።