ክፍለ ጊዜ 8/21
ገጽ 1/3 አፈጻጸማችሁ እንዴት ነው? ግምገማ እና ማስተካከያጻጸማችሁ እንዴት ነው? ግምገማ እና ማስተካከያ
ልምምድ የሚደረግባቸው ችሎታዎች፡-
- በመማር ሂደታችሁን ላይ መወያየት።
- የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ሰጪዎች እንደመሆናችሁ መጠን ያላችሁን ልምድ መጠቀም።
የክፍለ ጊዜው ጭብጥ፡- በዚህ የስልጠና ክፍለ ጊዜ እስከ አሁን ባጠናቀቃችኋቸው ክፍለ ጊዜዎች ውስጥ የሠራችኋቸውን ሥራዎች ዞር ብላችሁ ትመለከታላችሁ።ከመቀጠላችሁ በፊት የሠራችሁትን ሥራ እና ያገኛችኋቸውን ልምዶች በአጭሩ ታስቀምጣላችሁ።
የክፍለ ጊዜው ዓላማዎች፡- ይህ ክፍለ ጊዜ ዓላማው በሥራችሁ ምን እንደተማራችሁ እና ምን ስኬት እንዳስመዘገባችሁ እንዲሁም እንዴት አብራችሁ ይበልጥ በተሻለ መልኩ መሥራት እንደምትችሉ ከአሰልጣኙ እና ከሌሎቹ የአደራ ቤተሰብ ወላጆች ጋር በመሆን መወያየት ነው።
“ይህ ክፍለ ጊዜ የእያንዳንዱን ህጻን ዕድገት እንድንፈትሽ፣ የማህበራዊ ትስስር መረባችንን እንድንፈተሽ፣ እንድንቀበል እና እንድንደግፍ ሥራችንንም እንዴት መቀጠል እንዳለብን እንድንወስን ረድቶናል። አንዳንድ አዳዲስ ሀሳቦችን አግኝተናል እንዲሁም አብረን የምንሰራበት መንገድ ላይ ማስተካከያ አድርገናል።”
የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ሰጪ አስተያየት