ክፍለ ጊዜ 5/19

ገጽ 5/5 የሥራ ዕቅድ፡- ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት የሚሠሩ ሥራዎች

የሥራ ዕቅድ፡- ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት የሚሠሩ ሥራዎች

  • እባካችሁ ከሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ በፊት ከዕለት ተዕለት አሠራራችሁ ውስጥ ማሻሻል የምትፈልጓቸው ሁለት አሠራሮችን ምረጡ።
  • የህጻናትን አካባቢ በተመለከተ ልትሠሩባቸው የወሰናችኋቸውን ሁለት ማሻሻያዎች ጻፏቸው።
  • ሥራ በምትሠሩበት ጊዜ በተለየ መልኩ ማድረግ ያለባችሁ እና ይበልጥ ማስተዋል ያለባችሁ ምንድን ነው?
  • ምን ዓይነት ተጨባጭ ችግሮች ይኖራሉ (እንደ የቀለም ማስቀቢያ ገንዘብ፣ አልጋዎችን ማስተካከል ወይም መሸጥ፣ ልሙጥ አንሶላዎችን በሌሎች ማቴሪያሎች መቀየር፣ ሬዲዮ ወይም ቴሌቪዥን ጥቅም ላይ የሚውሉሉባቸውን ጊዜዎች የተመለከቱ ዕቅዶች፣ ለህጻናት በጨርቅ የተወጠሩ መተኛዎችን መግዛት ወይም መስፋት ወይም የሚንዠወዋዠዉ አልጋዎችን መግዛት፣ ወዘተ ያሉ)።
  • ማነቃቃትን እና አካላዊ ንክኪን በተመለከተ ከእሴቶቻችሁ እና ከአሠራሮቻችሁ ጋር በተያያዘ በተለየ መልኩ ማድረግ ያለባችሁ ምንድን ነው?
  • እንደተሳካላችሁ የምታውቁት በምንድን ነው?
  • አዲሶቹን አሠራሮች በአእምሮአችሁ መዝግቡ ወይም በቪዲዮ ቅረጹ ወይም በተለየ መልኩ ያደረጋችሁትን ነገር እና ለለውጦቹ ህጻናቱ ምላሽ የሰጡበትን መንገድ በተመከተ ያስተወላችሁትን ነገር በጽሁፍ አስፍሩ።
ፍላጎትስላሳያችሁእያመሰገንንእስከሚቀጥለውክፍለጊዜድረስለምትሰሩትሥራመልካምዕድልእንመኝላችኋለን!