ክፍለ ጊዜ 11/21
ገጽ 1/4 እኔ ማን ነኝ? ከተከፋፋለ የጀርባ ታሪክ በመነሳት አዎንታዊ ማንነትን መገንባትእኔ ማን ነኝ? ከተከፋፋለ የጀርባ ታሪክ በመነሳት አዎንታዊ ማንነትን መገንባት
ልምምድ የሚደረግባቸው ችሎታዎች፡-
- የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ውስጥ ስለ መሆን ግልጽ ውይይቶችን የማቀድ እና የማድረግ ክህሎት።
- የራሳችሁን የህይወት ተሞክሮዎች እንዴት አርአያ የሆኑ ትርክቶችን ለማዘጋጀት እንደ ግብዓት መጠቀም እንደምትችሉ።
- የሚያሳዩት ባህሪ ሰውን ለማጣት የሚሰጡ ተፈጥሮአዊ ምላሾች መሆናቸውን እንዲገነዘቡ ህጻናት እና ወጣቶችን እንዴት ማገዝ እንደሚቻል።
- ህጻናት በህይወታቸው ውስጥ ትልቅ ቦታ ከሚሰጧቸው ሰዎች ጋር ያጋጠሟቸውን ከባድ መለያየቶች መፍታት የሚችሉባቸው ተጨባጭ እንቅስቃሴዎችን እንዴት ማዘጋጀት እንደሚቻል።
የክፍለ ጊዜው ጭብጥ፡- በዚህ የስልጠና ክፍለ ጊዜ ህጻናት ስለማንነታቸው እና ስለራሳቸው ከፍተኛ ግምት ስለመስጠት አዎንታዊ ሀሳቦችን እንዲያዳብሩ ከመርዳት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ትሠራላችሁ። በዚህ አጋጣሚ ህጻኑ የተለያዩ መነሻዎች ያሉት መሆኑን ተቀብሎ መኖር የሚችልባቸው ዘዴዎች ይቀርባሉ።
የክፍለ ጊዜው ዓላማዎች፡- ይህ ክፍለ ጊዜ ዋና ዓላማው የጀርባ ታሪካቸውን እንዲገነዘቡ ህጻናትን በመርዳት ስለማንነታቸው አዎንታዊ ሀሳብን እንዲያዳብሩ መርዳት ነው።