ክፍለ ጊዜ 13/21

ገጽ 2/5 ከተፈጥሮ ወላጆቹ ጋር ለመገናኘት እና በወላጆቹ እና በአደራ ቤተሰቡ መካከል መስማማት እንዲኖር ህጻኑ ያለው ፍላጎት

Tከተፈጥሮ ወላጆቹ ጋር ለመገናኘት እና በወላጆቹ እና በአደራ ቤተሰቡ መካከል መስማማት እንዲኖር ህጻኑ ያለው ፍላጎት

የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ላይ ያሉ ህጻናት ሁለት ቤተሰቦች አሏቸው፡- የትውልድ ቤተሰባቸው እና የአደራ ቤተሰባቸው።
በዚህ ረገድ እንዲሳኩ ልትሰሩባቸው የሚገቡ ሁለት ግቦች እንዳሉ በአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ላይ የተሰሩ ጥናቶች የሚያሳዩ ሲሆን እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡-

 

  • በአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ላይ ያሉ ህጻናት የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ላይ እያሉ ከተፈጥሮ ቤተሰባቸው ጋር ሙሉ በሙሉ ግንኙነት ካቋረጡ በህይወት ውስጥ ደካማ የመሆን ሁኔታ ይታይባቸዋል። በተለይም ደግሞ፡- የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ መጨረሻ ላይ የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ላይ ያሉ ልጆች ከትውልድ ቤተሰባቸው ውጭ የሚሄዱበት ሌላ ማንም ሰው አይኖራቸውም። በአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ላይ በነበሩበት ወቅት ከወላጆቻቸው ጋር ምንም ግንኙነት ካልነበራቸው ይህንንም ግንኙነት ጭምር ሊያጡት ይችላሉ።
  • በአደራ ቤተሰባችሁ እና በልጁ የተፈጥሮ ወላጆች መካከል ይበልጥ መስማማት እና መከባበርን መፍጠር በቻላችሁ ቁጥር ህጻኑ ይበልጥ የመተማመን ስሜት ይሰማዋል፡- ይጫወታል፣ ያስሳል እንዲሁም ይማራል። ከተፈጥሮ ወላጆቹ ጋር ግጭት ውስጥ ከሆናችሁ (ወይም ንቀት የምታሳዩአቸው ከሆነ) የህጻኑ ኃይል የሚውለው የመተማመን ስሜት ማጣት ላይ ይሆናል እንዲሁም አስተማማኝ መሠረት አይኖረውም።

ለአደራ ቤተሰብ ወላጆች በጣም ከባድ ከሆኑት ነገሮች ውስጥ አንዱ ይህ ነው፡- የራሳቸውን ልጅ መንከባከብ ካልቻሉ ሰዎች ጋር አንድን ህጻን መጋራት። ይህ ለምንድን ነው በጣም የሚከብደው? ህጻናት የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ እንዲያገኙ የሚመደቡት ለምን እንደሆነ እና የተፈጥሮ ወላጆቻቸው የሚገኙበትን ሁኔታ በተመለከተ የተለመደው ነገር ምን እንደሆነ እንመልከት እና ከዚያ ደግሞ  ከወላጆች ጋር የሚኖር ግንኙነትን ማስኬጃ ዘዴዎችን እንመልከት።