ክፍለ ጊዜ 19/21
ገጽ 2/5 ዕድገታችሁን መገምገምዕድገታችሁን መገምገም
በዚህ ክፍለ ጊዜ ውስጥ በአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ስልጠናችሁ ወቅት ያዳበራችኋቸውን ችሎታዎች በአጭሩ እንድትገልጹ እንጠይቃችኋለን። ምን አልባት በሥራችሁ ውስጥ አዳዲስ እሴቶችን አግኝታችሁ ይሆናል። ምን አልባት ደግሞ ህጻናትን ከመንከባከብ ጋር በተያያዘ ትልቅ ቦታ ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ምንድን ነው የሚለውን በተመለከተ ያላችሁ አስተሳሰብ ተቀይሮ ይሆናል። ምን አልባት የአደራ ወላጅ እንደመሆናችሁ መጠን ከህጻኑ ጋር እና ከማህበራዊ ትስስራችሁ ጋር መስተጋብር የምታደርጉበትን መንገድ አስተውላችሁ ይሆናል። ወይም ደግሞ ምንም እንኳን መጀመሪያ ላይ ያስቀመጣችኋቸውን ግቦች በሙሉ ባታሳኩም ጥራት ያለው እንክብካቤ መስጠት የምትችሉባቸው በርካታ ሁነኛ መንገዶችን አግኝታችሁ ይሆናል። አንዳንድ ሀሳቦቻችሁ ፕሮግራሙ ሊያቀርባቸው ከሚችላቸው ማናቸውም ሀሳቦች በጣም የተሻሉ ሊሆኑ ይችላሉ።
በተጨማሪም ይህን ክፍለ ጊዜ ስታጠናቅቁ የአደራ ቤተሰብ ወላጆች እንደመሆናችሁ ያሏችሁን ችሎታዎች በትክክል መግለጽ የምትችሉበት ሁኔታ ውስጥ ትሆናላችሁ። አዲስ የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ግንኙነት ለመጀመር ፍላጎት ካላችሁ ይህንን ለባለሥልጣን አካላት ልታቀርቡ ትችላላችሁ።
የስራ መሪ ያላችሁ ከሆነ ወይም ከማህበራዊ ሠራተኛ ጋር ተቀናጅታችሁ የምትሰሩ ከሆነ እባካችሁ በውይይቶቹ ውስጥ እንዲሳተፍ ይህን ሰው ጋብዙት። ካልሆነም ከባለቤታችሁ ጋር ልትወያዩ ትችላላችሁ። በተጨማሪም ልትጋብዟቸው የምትፈልጓቸው ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡- የህጻኑ የት/ቤት መምህር፣ አያት፣ ወዘተ።
ማውራት ያለባችሁ በመጀመሪያ ስለ ህጻኑ ዕድገት ከዚያ ደግሞ በአጠቃላይ ከሞያዊ የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ሥራ ጋር በተያያዘዘ ከሥራችሁ እና ከስልጠናው ስላገኛችኋቸው ችሎታዎች ነው። በዚህ ክፍለ ጊዜ ውስጥ በተጠየቁት ጥያቄዎች ዙሪያ የምታደርጉትን ውይይት ለማጠናከር “የመወያያ ሰነድ” የተባለውን ይህን የወርድ ዶክመንት (word document) መጠቀም ወይም እዚህ ጋር ያሉትን ጥያቄዎች ተመልክታችሁ ወረቀት ላይ ልትጽፏቸው ትችላላችሁ። ጥያቄዎቹ በቀጣዩ ገጽ ላይ ተብራርተዋል።
አዲስ ዕውቀት፡- (ከአስተማማኝ መሰረት አንጻር በህጻናት ዕድገት ዙሪያ ያለኝን ዕውቀት አዳብሬአለሁ የሚሉ ምሳሌዎችን ስጡ። ምን አልባት ክፍለ ጊዜዎቹን እንደገና ተመልሳችሁ አየት ልታደርጓቸው እና ከየትኞቹ የንድፈ ሀሳብ ክፍሎች ትምህርት እንዳገኛችሁ ልትመለከቱ ትችላላችሁ)
ተግባራዊ ማድረግ፡- (ያገኘሁትን አዲስ ዕውቀት በሥራዬ ውስጥ ይህን ሳደርግ እጠቀመዋለሁ የሚሉ ምሳሌዎችን ስጡ)
እሴቶች፡- ይህን (ለምሳሌ “አዲስ ዕውቀት እና ተግባራዊ ማድረግ” የሚሉት አምዶች ላይ የተገለጸውን) ሳደርግ (ለምሳሌ ህጸኑ የተለየ መሆኑን ማክበር እና ክብር መስጠት) የሚለውን እሴት መሰረት በማድረግ ነው።