ክፍለ ጊዜ 19/21
ገጽ 3/5 ርዕስ ሀ፡- ከሥራችሁ እና ከስልጠናው ያገኛችኋቸውን ብቃቶች መገምገምርዕስ ሀ፡- ከሥራችሁ እና ከስልጠናው ያገኛችኋቸውን ብቃቶች መገምገም
ለእያንዳንዱ ጥያቄ፡-
- በቀደመው ገጽ ላይ ያለውን ቅጽ ስላዳበራችኋቸው ችሎታዎች ለመወያየት እንደ መሰረት ተጠቀሙ።
- እባካችሁ አምስት ደቂቃ ወስዳችሁ ከዚህ በታች ያለውን እያንዳንዱን ጥያቄ አጢኑ እንዲሁም ተወያዩበት።
- ማስታወሻዎችን ያዙ።
- ከዚያም እንደገና አምስት ደቂቃ ወስዳችሁ የአደራ ቤተሰብ ወላጆች እንደመሆናችሁ መጠን ይህ በአጠቃላይ ምን ችሎታዎችን እንዳስጨበጣችሁ ተወያዩ።
በተጨባጭ ክህሎቶች እና በግንኙነት ክህሎቶች ዙሪያ የአደራ ልጁ ብቃቶች መዳበር
የሚከተሉትን ጥያቄዎች በምትመልሱበት ወቅት እባካችሁ የሚከተሉትን ነገሮች ከግምት ውስጥ አስገቡ፡-
- የህጻኑን ዕድሜ
- ህጻኑ እናንተ ጋር ከመመደቡ በፊት የኖረባቸውን ሁኔታዎች
- እናንተ ልትንከባከቡት ስትረከቡት ህጻኑ የነበረበትን አካላዊ እና አእምሮአዊ ሁኔታ
- እናንተ ጋር ሲመደብ ህጻኑ የነበሩበትን ችግሮች
የአደራ ወላጆች እንደመሆናችሁ መጠን እባካችሁ የህጻናትን ተጨባጭ ክህሎቶች ዕድገት ከመደገፍ ጋር በተያያዘ ከዕለት ተዕለት ተሞክሮዎቻችሁ እና ከፌርስታርት ስልጠና ያገኛችኋቸውን ችሎታዎች ግለጹ፡-
ለምሳሌ፡- “የአደራ ልጆች አስተማማኝ መሰረት እንዲሁም ለውጦች እና እንቅስቃሴዎች ያልበዙበት የዕለት ተዕለት ፕሮግራም እንደሚያስፈልጋቸው ተምሬአለሁ” ስለ ህጻኑ ተጨባጭ ክህሎቶች ዕድገት ምን ታስባላችሁ?
ህጻኑ ለምሳሌ ልብስ መልበስን፣ የተረጋጋ የዕለት ተዕለት ፕሮግራምን፣ የቤት ሥራውን መስራትን፣ ብስክሌት መንዳትን፣ ወዘተ መማር ላይ መሻሻል አሳይቷል? በአጭሩ ተጨባጭ ነገሮችን በራሱ ማድረግን ለምዷል፤ ተመሳሳይ ዕድሜ ላይ ያሉ ልጆች ማድረግ ከሚችሉት ነገር ጋርስ አብሮ ይሄዳል?
የአደራ ወላጆች እንደመሆናችሁ መጠን እባካችሁ የህጻናት የግንኙነት ክህሎቶች እንዲዳብሩ ከመደገፍ ጋር በተያያዘ ከዕለት ተዕለት ተሞክሮዎቻችሁ እና ከፌርስታርት ስልጠና ያገኛችኋቸውን ችሎታዎች ግለጹ፡-
ለምሳሌ፡- “የህጻኑን ስሜት መጋራት ነገር ግን እንደ ህጻኑ ያለመሆን አስፈላጊ እንደሆነ ተምሬአለሁ። ጤናማ ያልሆኑ ግንኙነቶች የነበሯቸው ህጻናት ለእንክብካቤ የሚሰጡት ምላሽ የተዘበራረቀ ሊሆን ስለሚችል በዚህ መበሳጨት አቁመናል”
ስለ ህጻኑ የግንኙነት ክህሎቶች ምን ታስባላችሁ? ህጻኑ ከእናንተ ጋር መስተጋብር የሚያደርግበት እና የሚቀራረብበት መንገድ ተሻሽሏል? መጀመሪያ ላይ ሲመደብ ህጻኑ የመሸሽ ወይም የመጠራጠር ባህሪ የነበረው ከሆነ ይህ ባህሪ ጠፍቷል ወይም ቀንሷል? ህጻኑ እገዛ፣ ጥበቃ እና ማባበልን ፍለጋ እናንተ ጋር ይመጣል? ህጻኑ ከእኩዮቹ ጋር ስላለው የማህበራዊ ችሎታ ዕድገት ምን ታስባላችሁ? ህጻኑ ከራሳችሁ ልጆች እና ከሌሎች ልጆች ጋር መግባባት ይችላል? ጓደኝነቶችን እና የት/ቤት ግንኙነቶችን የሚይዘው እንዴት ነው?
የአደራ ወላጆች እንደመሆናችሁ መጠን እባካችሁ ህጻናት ከመለያየት ጋር ተያይዞ የሚፈጠር ጭንቀትን ማስተናገድ እንዲችሉ ከማገዝ አንጻር ከዕለት ተዕለት ተሞክሮዎቻችሁ እና ከፌርስታርት ስልጠና ያገኛችኋቸውን ችሎታዎች ግለጹ፡-
የአደራ ልጁ መለያየትን የማስተናገድ ችሎታ እንዴት ነው? ህጻኑ ሰውን ማጣት እና መለያየት በምን መልኩ ተጽዕኖ እንዳሳደረበት ይገነዘባል? ህጻኑ መለያየትን መርሳት ስለሚችልበት መንገድ ግንዛቤ አዳብሯል? ህጻኑ አሁንም ድረስ ለመያየት የሚሰጠው አካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ምላሽ ጠንካራ ነው (እንደ መደንገጥ ያለ) ወይስ ከእናንተ ወይም ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው ሌሎች ሰዎች ጋር በሚለያይበት ወቅት መረጋጋት ይችላል? ህጻኑ መለያየትን እንዴት ለማስተናገድ እንደሚሞክር ማስረዳት ይችላል?
የአደራ ወላጆች እንደመሆናችሁ መጠን እባካችሁ ህጻናት ምንም እንኳን የተለያዩ የጀርባ ታሪኮች ቢኖሯቸውም ግልጽ ማንነትን እንዲፈጥሩ ከማገዝ አንጻር ከዕለት ተዕለት ተሞክሮዎቻችሁ እና ከፌርስታርት ስልጠና ያገኛችኋቸውን ችሎታዎች ግለጹ፡- ህጻኑ ስለ ማንነቱ ግልጽ የሆነ ሀሳብ አለው? ህጻኑ የተለያዩ እንክብካቤ ሰጪዎቹ፣ ጓደኞቹ፣ መምህራኑ እና ሌሎች ሰዎች ለማንነቱ በምን መልኩ አስተዋጽዖ እንዳደረጉ ያውቃል? ህጻኑ ይህንን መግለጽ ይችላል?
ከማህበራዊ እና ከሞያዊ ትስስሮች ጋር ያላችሁ ቅንጅታዊ አሠራር ዕድገት
1. የአደራ ወላጆች እንደመሆናችሁ መጠን እባካችሁ ለህጻኑ ጠቃሚ የሆነ አቃፊ እና ለአዳዲስ ሀሳቦች ክፍት የሆነ ማህበራዊ ትስስርን ከመፍጠር አንጻር ከዕለት ተዕለት ተሞክሮዎቻችሁ እና ከፌርስታርት ስልጠና ያገኛችኋቸውን ችሎታዎች ግለጹ፡-የህጻኑን ማህበራዊ ትስስር ማዳበር፡- እባካችሁ ከማህበራዊ ትስስራችሁ (ዘመዶቻችሁ፣ ጎረቤቶቻችሁ፣ የት/ቤት መምህራን፣ ወዘተ) ጋር ያላችሁን ግንኙነት ተመልከቱ እና ከእነሱ ጋር ባላችሁ ቅንጅታዊ አሰራር ውስጥ ለህጻኑ ጠቃሚ የነበሩ ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮችን ጥቀሱ።
2. የአደራ ወላጆች እንደመሆናችሁ መጠን እባካችሁ ከባለሥልጣን አካላት ጋር ተቀናጅታችሁ ከመሥራት አንጻር ከዕለት ተዕለት ተሞክሮዎቻችሁ እና ከፌርስታርት ስልጠና ያገኛችኋቸውን ችሎታዎች ግለጹ፡-እባካችሁ በምደባው ዙሪያ ከባለሥልጣን አካላት ጋር ተቀናጅቶ ከመሥራት ጋር በተያያዘ የነበሯችሁን ተሞክሮዎች ተመልከቱ እና ከእነሱ ጋር ባላችሁ ቅንጅታዊ አሰራር ውስጥ ለህጻኑ ጠቃሚ የነበሩ ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮችን ጥቀሱ።
3. የአደራ ወላጆች እንደመሆናችሁ መጠን እባካችሁ ከአደራ ቤተሰብ ልጆች የተፈጥሮ ወላጆች ጋር ተቀናጅታችሁ ከመሥራት አንጻር ከዕለት ተዕለት ተሞክሮዎቻችሁ እና ከፌርስታርት ስልጠና ያገኛችኋቸውን ችሎታዎች ግለጹ፡- ለምሳሌ፡- “ምንም እንኳን ችግሮች ቢኖሩም የእሱን ወላጆች እንደምናከብራቸው ለህጻኑ ማሳየትን እና ይህም ራስን እንዲያከብር ህጻኑን እንደሚረዳው ተምሬአለሁ” እባካችሁ ከህጻኑ የተፈጥሮ ወላጆች ጋር ያላችሁን ቅንጅታዊ አሠራር በተመለከተ ከእነሱ ጋር ባላችሁ ቅንጅታዊ አሰራር ውስጥ ለህጻኑ ጠቃሚ የነበሩ ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮችን ጥቀሱ። (ለእናንተ አግባብነት ካለው)፡- እባካችሁ ህጻኑ ከልጅነት ወደ ወጣትነት ባደረገው ሽግግር እና ከእንክብካቤአችሁ ከመውጣቱ ጋር በተያያዘ የሠራችሁትን ሥራ ተመልከቱ እና በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላለው ልጅ ጠቃሚ የነበሩ ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮችን ጥቀሱ።