ክፍለ ጊዜ 19/21
ገጽ 5/5 የሥራ ዕቅድ፡- ለወደፊቱ የምናደርጋቸው ነገሮችየሥራ ዕቅድ፡- ለወደፊቱ የምናደርጋቸው ነገሮች
የዚህን ክፍለ ጊዜ ማስታወሻዎች መሠረት በማድረግ በአደራ ቤተሰብ እንክብካቤያችሁ ውስጥ ስለተመዘገቡት ስኬቶች እና ሞያዊ አሠራሮች አጭር የጽሁፍ ገለጻ ሪፖርት እንድታዘጋጁ እንመክራለን። ይህም የስራ መሪዎቻችሁን፣ የውሳኔ ሰጪዎችን እና በሞያ የምታውቋቸው ሰዎችን ዕውቅና በማግኘት ረገድ አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይችላል።
እባካችሁ ሪፖርቱን ስለምትሰሩት ሥራ ዕውቀቱ የሌላቸው ሰዎች ሊያነቡት እንደሚችሉ አስታውሱ።
ምን እንደምትሰሩ፣ ከማን ጋር እንደምትሰሩ፣ በምን መልኩ ሥራችሁን እንደምትሰሩ እና ለሥራችሁ መሠረት የሆኑት ሰብዓዊ እሴቶች ምን እንደሆኑ በቀላል ቋንቋ የሚገልጽ መሆን አለበት። ከ3-5 ገጽ መብለጥ የለበትም እንዲሁም ለማስረዳት እንዲጠቅሟችሁ ከዕለት ተዕለት ሥራችሁ የተወሰዱ ፎቶዎችን ማስገባት ትችላላችሁ። የብቃቶች ቅጹን የሞላችሁ ከሆነ ለሪፖርታችሁ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።
እባካችሁ ሪፖርቱን ማን እንደሚጽፈው ወስኑ (ለምሳሌ የስራ መሪ፣ አሰልጣኝ እና የአደራ ቤተሰብ ወላጆች)።
ለአደራ ቤተሰብ እንክብካቤያችሁ የቪዲዮ መግለጫ ልታዘጋጁ ትችላላችሁ። ምን እንደምትሰሩ፣ ከማን ጋር እንደምትሰሩ፣ በምን መልኩ ሥራችሁን እንደምትሰሩ እና ለሥራችሁ መሠረት የሆኑት ሰብዓዊ እሴቶች ምን እንደሆኑ በቀላል ትዕይንቶች/ቃለ መጠይቆች የሚያሳይ መሆን አለበት። ከአሥር ደቂቃ የሚረዝም መሆን የለበትም።
የሚቻል ከሆነ ከአደራ ቤተሰብ ልጃችሁ ጋር የተደረገ አንድ ቃለ መጠይቅ (ለምሳሌ፡- “የአንድሬ የአደራ እንክብካቤ ቤተሰብ”) ማካተት እንዲሁም ከዚህ በተጨማሪ ምን አልባት በማህበራዊ ትስስሩ ውስጥ ያሉ ሰዎችን እና የተፈጥሮ ወላጆችን ማካተት ትችላላችሁ።
ላሳያችሁን ፍላጎት እናመሰግናለን እንዲሁም ለወደፊቱ በምትሰሩት ሥራ መልካም ዕድልን እንመኝላችኋለን!