ክፍለ ጊዜ 2/19

ገጽ 3/4፡- የርዕስ መግቢያ፡- ርዕስ ሀ እና ርዕስ ለ
ርዕስ ሀ፡- በቤተሰባችን ህይወት ውስጥ ያሉት ዕሴቶች የአደራ ቤተሰብ እንደመሆናችን መጠን መሠረት ሊሆኑን የሚችሉት እንዴት ነው?

ይህ መልመጃ ዓላማው ሁሉም የቤተሰቡ አባላት የአደራ ቤተሰብ በመሆን ሂደት ውስጥ እንዲሳተፉ ማድረግ ነው።

የአደራ ቤተሰብ እንደመሆናችሁ መጠን የሚጠበቅባችሁ ባለሞያዎች መሆን ሳይሆን በአደራ ለሚያድግ ልጅ ለረጅም ጊዜ እንክብካቤ ከማድረግ አንጻር ምን ጥሩ ነገር መስጠት እንደምትችሉ ማወቅ ነው፤ እሱም በየቀኑ ከቤተሰብ ጋር የመኖር ዕድል እና እንክብካቤ እንዲያገኝ ማድረግ ነው።

ይህ መልመጃ ሁሉም የቤተሰብ አባላት በአደራ ቤተሰብ እንክብካቤ ውስጥ ላለ ልጅ ማቅረብ የሚችሏቸውን አሴቶች እንዲያጋሩ እና እንዲያውቋቸው የሚረዳ ነው። 

የእናንተን ቤተሰብ ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? የአደራ ቤተሰብ ወላጆች እንደመሆናችሁ መጠን እናንተ እና የራሳችሁ ልጆች (ልጅ ያላችሁ ከሆነ) የሚረብሻችሁ ነገር ሳይኖር ለተወሰኑ ሠዓታት መወያየት የምትችሉበት ከሠዓት በኋላ ያለ ጊዜ ወይም ምሽት ፈልጋችሁ አዘጋጁ። ሞባይል ስልካችሁን አጥፉ። ቤተሰባችሁ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውበጣም ጥሩ የቤተሰቡ ጓደኛ የሆነ ሰው ወይም ወንድ ወይም ሴት አያት ካሏችሁ እነሱንም ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። የመጀመሪያዎቹ ጥያቄዎች ብዙ ጊዜ ከወሰዱ ምን አልባት ሁለት ከሠዓት በኋላዎችን ወይም ምሽቶችን መጠቀም ሊኖርባችሁ ይችላል።

ወረቀት ላይ ማስታወሻዎችን ያዙ (የራሳችሁ ልጆች ካሏችሁ ስዕሎችን መሳል ይችላሉ)።

1. በቤተሰባችሁ ህይወት ውስጥ ሁላችሁም ካሳለፋችኋቸው ቀናት ሁሉ ምርጥ ቀን -እርስ በእርስ ምስጋና ወይም ፍቅር የተገላለጻችሁበት፣ በጣም የሳቃችሁበት እና የተዝናናችሁበት ቀን የምትሉትን አንድ ቀን በመተጋገዝ ግለጹ። ወይም ደግሞ ሁላችሁም አንድን ችግር በጋራ መጋፈጥ የቻላችሁበትን እና ምንም እንኳን የሚያስጨንቅ ነገር ቢኖርም እርስ በእርስ የተደጋገፋችሁበትን አንድ ቀን ልትመርጡ ትችላላችሁ። እባካችሁ ይህን ቀን አንዳችሁ ለአንዳችሁ ግለጹ -ይህን ቀን በጣም ጥሩ ያደረገው ምን ማድረጋችሁ ነበር?

2. ስለ ቤተሰብ ህይወታችሁ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸውን ሦስት ነገሮች ለዩ። ለምሳሌ፡- እራት እየበላን በጣም ጥሩ ወሬዎችን  እናወራለን፣ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ አብረን መሥራት እንችላለን፣ ወይም በማንነታችን እንኮራለን። መሠረታዊ እሴቶቻችሁን አስተውሉ/ማስታወሻ ያዙ።

3.ያወራችሁትን ነገር መሠረት በማድረግ ዝርዝር አዘጋጁ -እንደ ቤተሰብ እና እንደ የአደራ ቤተሰብ ብቃቶቻችን እነዚህ ናቸው የምትሏቸውን ነገሮች።

4.እያንዳንዱን የቤተሰብ አባል የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቁ፡- በአደራ ለማሳደግ ለምንቀበለው ወይም አስቀድመን ለተቀበልነው ልጅ ጥሩ አንክብካቤ ለማድረግ የአንተን/የአንቺን ጠንካራ ጎኖች እና ብቃቶች በምን መልኩ መጠቀም እንችላለን?

 

ርዕስ ለ፡- የአካባቢ የግንኙነት መረባችሁን ማዘጋጀት፡- ድጋፍ ሊያደርጉ የሚችሉ ሰዎችን ለዩ

በማህበራዊ ትስስራችሁ ውስጥ ያሉ ከልጁ/ልጅቷ ጋር የመገናኘት ሰፊ ዕድል ያላቸው እና በህይወቱ/ቷ ውስጥ ትልቅ ቦታ ሊይዙ የሚችሉ ሰዎችን ዝርዝር ጻፉ። ይህም በቤታችሁ አቅራቢያ ያለ ባለሰሱቅ፣ ጎረቤቶቻችሁ እና ልጆቻቸው፣ ጓደኞቻችሁ ወይም ዘመዶቻችሁ፣ ወይም (ልጁ/ልጅቷ እነዚህን ተቋማት እንዲጠቀም/እንድትጠቀም የምታቅዱ ከሆነ) በአካባቢው ያለው አጸደ ህጻናት ወይም ት/ቤት ሊሆን ይችላል።

በዚህ የግንኙነት መረብ ውስጥ ያሉ ሰዎችን በምታናግሩበት ወቅት በአደራ ቤተሰብነት ለመሥራት የወሰናችሁትን ውሳኔ አንስታችሁ ለመወያየት ማንኛውንም ማህበራዊ አጋጣሚ ልትጠቀሙ ትችላላችሁ። ለምሳሌ የምታውቋቸውን ሰዎች መንገድ ላይ አግኝታችሁ ስለ ዕለት ተዕለት ህይወታችሁ በምታወሩበት ወቅት።

ይህን ውሳኔ ስለመወሰናችሁ፣ ለቤተሰባችሁ ዕድገት ጥሩ ነገር ነው ብላችሁ እንደምታስቡ እና በአደራ የምታሳድጉትን ልጅ ለመንከባከብ በጉጉት እንደምትጠብቁ ከመጀመሪያው ጀምሮ በጣም ግልጽ ማድረግ ጥሩ ነው። የአደራ ቤተሰብ ውስጥ የሚያድግ ልጅ የሚያሳፍር ነገር እንዳልሆነ እና ይልቁንም  ወላጅ ለሌላቸው ልጆች እንክብካቤ ማድረግ የተፈጥሮ ግዴታ ነው ብላችሁ እንደምታስቡ በተግባር ማሳየት አለባችሁ።

የምታናግሯቸው ሰዎች በአደራ ቤተሰብ ስለሚያድጉ ልጆች ጥርጣሬዎች ወይም የተሳሳቱ አመለካከቶች ካሏቸው ጸብ አትጀምሩ፤ ዝም ብላችሁ አዳምጧቸው ወይም ስሜታቸው እንደሚገባችሁ እና ከልጁ/ልጅቷ ጋር ሲገናኙ ሀሳባቸውን ሊቀይሩ እንደሚችሉ ንገሯቸው።

በግንኙነት መረቡ ውስጥ ያሉ ጠቃሚ ሰዎች ዝርዝር

 

 ጎረቤቶቻችሁን፣ ጓደኞቻችሁን እና ቤተሰባችሁን ካነጋገራችሁ በኋላ ስለ የአደራ ቤተሰብ ሁኔታችሁ አዎንታዊ አመለካከቶች አሏቸው ብላችሁ የምታስቧቸውን ሦስት ሰዎችን ለዩ።

እነዚህ ጠቃሚ ሰዎች ለወደፊቱ ሥራችሁ ላይ በምን መልኩ ሊረዷችሁ እንደሚችሉ ራሳችሁን ጠይቁ።

 

ስለአደራ እንክብካቤ አሉታዊ አመለካከቶች ያሏቸው ወይም ስለአደራ ቤተሰብ ልጆች የተሳሳቱ አመለካከቶች ያሏቸው ሰዎች ካሉ
(“
ስጋ የማይዛመዳችሁን ልጅ እንዴት ታሳድጋላችሁ?”)።