ክፍለ ጊዜ 20/21
ገጽ 4/7: ርዕስ ለ፡- በስራችሁ ካሉ ህጻናት እና ታዳጊዎች ጋር ግልጽ ውይይቶቸን ለማድረግ መዘጋጀትርዕስ ለ፡- በስራችሁ ካሉ ህጻናት እና ታዳጊዎች ጋር ግልጽ ውይይቶቸን ለማድረግ መዘጋጀት
“ርዕስ ለ”ን ከመጀመራችሁ በፊት
እባካችሁ ከሥራ ዕቅድ ሀ ውስጥ ተሳታፊዎች ሊወያዩባቸው ስለሚገቡ ርዕሰ-ጉዳዮች አጠር ያለ ክለሳ አድርጉ። የስ-ልቦና ባለሞያ ማነጋገር ያስፈልገኛል ብለው የሚያስቡ ማናቸውም ተሳታፊዎች አሉ? በቡድናችን ውስጥ ያሉ አሳዳጊዎች በሙሉ ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ለመውጣት በደንብ ዝግጁ እንደሆኑ እንደሚሰማቸው እና ለህጻናቱ የሚያሳውቁበትን መንገድ ለማቀድ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጡ።
ህጻናት የአእምሮ ጠባሳቸው እንደገና እንዳይቀሰቀስባቸው መከላከል
በኤስ ኦ ኤስ መንደር እንክብካቤ ውስጥ የሚኖሩ ህጻናት ወደ ኤስ ኦ ኤስ መንደር ከመግባታቸው በፊት ከወላጆቻቸው እና ከእኩዮቻቸው ጋር የመለያየት ሰቆቃ የደረሰባቸው ናቸው። አንድ ህጻን በለመደው የኤስ ኦ ኤስ መንደር ውስጥ ያለውን አስተማማኝ መሰረት እና ከጓደኞቹ እና ከመንደሩ ሰራተኞች ጋር ያሉትን አስተማማኝ ግንኙነቶች ለቆ መሄድ እንዳለበት ሲነገረው በለጋ ዕድሜ ከወላጆቹ እና ከጓደኞቹ ጋር በተለያየበት ወቅት የነበሩ የቆዩ ፍርሀቶች እና ምናባዊ ሀሳቦች ሊቀሰቀሱ እና ከመጠን በላይ የሆነ የመለያየት ፍርሀትን፣ ጭንቀትን እና ሌሎች አሉታዊ ስሜቶችን ሊፈጥሩበት ይችላሉ። ይህ ምላሽ የአእምሮ ጠባሳ እንደገና መቀስቀስ ይባላል። የሚከተሉት ሀሳቦች እና ውይይቶች ህጻናት እና ታዳጊዎች የአእምሮ ጠባሳቸው መልሶ እንዳይቀሰቀስባቸው ለመከላከል እና ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ስለመውጣት አዎንታዊ ተሞክሮ እንዲኖራቸው ለማድረግ ይረዷችኋል።
አንዲት ሴት ልጅ ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ስለመውጣት እና ለወደፊቱ ስላላት ህልም ለኤስ ኦ ኤስ እናቷ የተናገረችው እንደሚከተለው ቀርቧል።
በስራችሁ ያሉት ህጻናት እና ወጣቶች ምን ዓይነት ምላሽ የሰጣሉ?
እንደ እድሜአቸው እና ታሪካቸው ሁኔታ ህጻናት ለዜናው የሚሰጡት ምላሽ በጣም የተለያየ ሊሆን ይችላል። ድክ ድክ የሚሉ ህጻናት እና በዕድሜ አነስ ያሉ ህጻናት የሚያዩት የአሁኑን ብቻ ነው፤ አሁን ያላቸው ቆይታም “ለዘለአለም” እንዲዘልቅ ይጠብቃሉ። ነገሩ እንዲገባቸው አይዞህ መባል እና አዲሱ ከባቢ ሁኔታቸው ውስጥ በአካል መገኘት ያስፈልጋቸዋል።
በዕድሜ ተለቅ ያሉ ህጻናት እና በአስራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ህጻናት ከኤስ ኦ ኤስ መንደሩ ወጥተው ማህበረሰቡን ለመቀላቀል ቀድሞውንም ጉጉት ሊኖራቸው ይችላል፤ እንደዚያም ሆኖ ግን ስለ ሽግግሩ ያለመተማመን እና የፍርሀት ስሜት ሊሰማቸው ይችላል።
ለ10 ደቂቃ ማሰላሰል፡- በስሬ ካሉት ህጻናት ወይም ታዳጊዎች ውስጥ አንደኛው ምን ዓይነት ምላሽ ሊሰጥ ይችላል?
እያንዳንዷ እናት በቤቷ ውስጥ ስላለ አንድ ህጸን ወይም ወጣት ታሰላስላለች፡-
- ይህ ህጻን ወይም ወጣት ወደ ኤስ ኦ ኤስ መንደር ከመግባቱ በፊት ባሳለፋቸው አሰቃቂ ተሞክሮዎች የተነሳ አሁንም ፍርሀቶች እና ጠንካራ የመለያየት ፍርሀት አለበት? ወይስ ያልተጠበቀ ነገር በሚከሰትበት ጊዜም እንኳን በአብዛኛው ደስተኛ እና ተጫዋች ነው?
- ይህ ህጻን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ላይ ለውጦች በሚኖሩበት ወቅት በተለምዶ የሚሰጠው ምላሽ ምን ይመስላል? ለምሳሌ ትምህርት ለመጀመር የሰጠው ምላሽ ምላሽ ወይም አዲስ ሰዎችን ለመተዋወቅ እና አዳዲስ ቦታዎች ለመሄድ የሚሰጠው ምላሽ ምን ይመስል ነበር?
- ህጻኑ በማህበረሰቡ ውስጥ ሊሟሉለት የሚችሉ ምን ተስፋዎች ወይም ፍላጎቶች አሉት?
- ስለ ህጻኑ ካለዎት ዕውቀት በመነሳት በምን መልኩ ሲያናግሩት ወይም ሲያናግሯት ነው በጣም ውጤታማ የሚሆንልዎት?
የ30 ደቂቃ የቡድን ውይይት፡-
አንደኛዋ የቡድን አባል በስሯ ካሉት ድክ ድክ የሚሉ ህጻናት ወይም አነስተኛ ዕድሜ ላይ ያሉ ህጻናት ውስጥ ለአንደኛው ስለምታሳውቅበት መንገድ ያላትን ሀሳብ ስታቀርብ ቡድኑ ያዳምጣል። ከዚያም ለዚህ ህጻን በምን መልኩ ቢነገረው የተሻለ ይሆናል በለሚለው ጉዳይ ዙሪያ የቡድኑ አባላት ያላቸውን አስተያየት እና ሀሳብ ያጋራሉ። ሌላ የቡድኑ አባል ደግሞ በስሯ ላለ አንድ በዕድሜ ተለቅ ያለ ህጻን ወይም በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለ ህጻን ስለማሳወቅ ያላትን ሀሳብ ታቀርባለች። ቡድኑም አድምጦ ሀሳቦችን ይሰጣታል። ከዚያም እባካችሁ በሚከተለው ጉዳይ ዙሪያ ውይይት አድርጉ፡-
- የግል ጥንካሬዎቹን እና ፍላጎቶቹን መሰረት በማድረግ ለአንድ በዕድሜ አነስ ያለ ህጻን ወይም ወጣት ማሳወቅ የምንችለው እንዴት ነው?
የሥራ ዕቅድ ርእስ ለ፡- ለህጻናት እና ወጣቶች ማሳወቅ
ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ለሚወጡ ህጻናት አንዲት የ11 ዓመት ልጅ የሰጠችው ምክር፡- “እንደ እኔ ተሞክሮ ከሆነ በተቻላቸው መጠን የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊአቸው የሚላቸውን ነገር ለማድረግ ጥረት ማድረግ አለባቸው። ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ለመውጣት መፍራት የለባቸውም፤ እንዲህ ብለው ማሰብ አለባቸው፡- “አዳዲስ ጓደኞችን አፈራለሁ፣ ፈተናዎቼን አልፋለሁ፣ ሁሉንም ነገር በትክክል ለማድረግ ብቻ እሞክራለሁ፣ ከዚያ ደስተኛ እሆናለሁ”
ከኤስ ኦ ኤስ መንደር መውጣት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ህጻናት እና ወጣቶች እንዲገባቸው ለማድረግ ለሚረዱ ውይይቶች እና ተግባራት የሚያገለግሉ አንዳንድ ሀሳቦች እና አስተያየቶች እዚህ ጋር ቀርበዋል። በሂደቱ ውስጥ በንቃት ሊሳተፉ እና አስተያየታቸው እና ሀሳባቸው ሊሰማላቸው ይችላል። የሥራ ዕቅዱ ሁለት ምዕራፎች አሉት።
ምዕራፍ 1፡- በእያንዳንዷ እናት ቤት ውስጥ ከህጻናቱ ጋር ግልጽ ውይይቶችን ማድረግ
በአሳዳጊአቸው ቤት ውስጥ ያለው ከባቢ ሁኔታ የሚያውቁት እና የመተማመን ስሜትን የሚፈጥርባቸው በመሆኑ ለወደፊቱ ከኤስ ኦ ኤስ መንደር መውጣት ስለሚለው ሀሳብ ህጻናትን ለመጀመሪያ ጊዜ ለማነጋገር ጥሩ ቦታ ነው። እንደ መክሰስ ሰዓት ወይም ምሽት ያለ ሁሉም ህጻናት የሚገኙበትን ሠዓት ይለዩ።
ለህጻናት ማሳወቅን በተመለከተ ጠቃሚ የሆኑ ምክሮች
ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ስለመውጣት ህጻናትን ማነጋገርን የተመለከቱ አንዳንድ መመሪያዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-
- እርስዎ እና ልጆችዎ የምትረጋጉበትን ቦታ እና ጊዜ ይምረጡ። እርስዎ እራስዎ በልጅነትዎ እንዴት የመኖሪያ ቦታ ለውጥ አጋጥሞዎት እንደነበረ እና ከዚያ ምን እንደተማሩ የሚያስረዳ አንድ ታሪክ ለህጻኑ ይንገሩት።
- ለወደፊቱ የሆነ ጊዜ ላይ ከኤስ ኦ ኤስ ሊወጣ እንደሚችል ለህጻኑ በተረጋጋ እና አዎንታዊ በሆነ መልኩ ይንገሩት።
- ማናቸውም ህጻናት በመቃወም፣ በፍርሀት ወይም በሀዘን ምላሽ የሰጡ እንደሆነ ስሜታቸውን እንዲገልጹ እና ስለሚያስቡት ነገር እንዲያወሩ ይፍቀዱላቸው። አያቋርጧቸው ወይም ስለሚኖሩት ጥቅሞች በማብራራት ለማሳመን አይሞክሩ። ወዲያውኑ ለሚኖሯቸው ምላሾች እና ጥያቄዎች ጊዜ ይስጧቸው።
- አሁንም ቢሆን እናታቸው እንደሚሆኑ እና የሚለወጠው ነገር በማህበረሰቡ ውስጥ መሆናችሁ ብቻ እንደሆነ በመግለጽ ህጻናቱን ያጽናኗቸው።
- ምንም ነገር ከመደረጉ በፊት በድጋሚ ብዙ ጊዜ እንደምታወሩ ለህጻናቱ ይንገሯቸው።
በቤት ውስጥ ከሚደረገው ስብሰባ በኋላ ቡድኑ ስለሂደቱ ሀሳብ ሊለዋወጥ እና ሂደቱን ሊገመግም ይችላል፡-
- ህጻናቱ ለዜናው ምን ዓይነት ምላሽ ሰጡ?
- የስነ–ልቦና ጠባሳቸው እንደገና የመቀስቀስ ምልክት ያሳዩ ማናቸውም ህጻናት ነበሩ (ለአንዳንዶቹ የስነ–ልቦና አማካሪ ያስፈልገናል)?
- በዕለት ተዕለት ሁኔታዎች ውስጥ ከወላጆቻቸው ጋር ተጨማሪ የተናጠል ውይይቶች የሚያስፈልጓቸው የትኞቹ ህጻናት ናቸው?
- የግድ መልስ ልናገኝላቸው የሚገባው ለየትኞቹ ጥያቄዎቻቸው ነው?
- ለህጻናቱ ከማሳወቅ ምን ተማርን?
ምዕራፍ 2፡- ከሁሉም የኤስ ኦ ኤስ መንደሩ ውስጥ ያሉ ህጻናት ጋር የሚደረግ የመረጃ መስጫ ስብሰባ
አንድ ወይም ከዚያ በላይ አሳዳጊዎች በስራቸው ላሉ ህጻናት ካሳወቁ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በኤስ ኦ ኤስ መንደሩ ውስጥ ያሉት ህጻናት በሙሉ እንዲያውቁ የሚደረግበት ስብሰባ መዘጋጀት ይኖርበታል። ይህ የሚስፈልገው ለምንድ ነው?
ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ለመውጣት ያቀደችው አንድ አሳዳጊ ብቻ ብትሆንም እንኳን ዜናው በፍጥነት ሁሉም ሠራተኛ ጋር ደርሶ በኤስ ኦ ኤስ መንደሩ ውስጥ ያሉ ህጻናት ሠራተኞች ሲያወሩ እዚህም እዚያም አንዳንድ ነገሮችን ይሰማሉ። ህጻናት ስሚጠብቃቸው ነገር የተሳሳቱ ግንዛቤዎች እና ጭንቀቶች እንዳይፈጠሩባቸው ለመከላከል ሲባል በኤስ ኦ ኤስ መንደሩ ውስጥ ያሉ አሳዳጊዎች እና ህጻናት በሙሉ የሚሳተፉበት የመረጃ መስጫ ስብሰባ ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው። እንደ የፕሮግራም ሥራ አስኪያጆች እና መምህራን ያሉ ሌሎች ሠራተኞችም ሊሳተፉ እና አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ይችላሉ።
ለዚህ የሚያገለግል አንድ ሀሳብ እንደሚከተለው ቀርቧል፤ እባካችሁ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ አድርጉበት፡-
- በእያንዳንዱ የኤስ ኦ ኤስ መንደር መኖሪያ ውስጥ ያሉ ህጻናት በቡድን በቡድን ከእናታቸው ጋር ይቀመጣሉ።
- የኤስ ኦ ኤስ መንደሩ ዳይሬክተር ወይም የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ከኤስ ኦ ኤስ መንደሩ የሚወጣባቸውን ጠቅላላ ምክንያቶች እና የጊዜ ሰሌዳዎች ያቀርባሉ።
- ከዚህ ቀደም በኤስ ኦ ኤስ መንደር የኤስ ኦ ኤስ እናት የነበረች ሴት የማህበረሰብ የኤስ ኦ ኤስ እናት ከመሆን ጋር በተያያዘ ያላትን ተሞክሮ ታቀርባለች።
- በአደራ እንክብካቤ ውስጥ የሚኖሩ አንድ ወይም ሁለት ወጣቶች ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ከመውጣታቸው በፊት እና ከወጡ በኋላ የነበራቸውን ተሞክሮ እና በአሁኑ ወቅት በማህበረሰቡ ውስጥ በሚኖሩበት ወቅት ያላቸውን ተሞክሮ ይገልጻሉ። እንዴት ጓደኞችን እንዳፈሩ፣ ትምህርት ስለመጀመር፣ የተማሯቸውን ክህሎቶች፣ ለሌሎች ህጻናት ያሏቸውን ምክሮች።
የ15 ደቂቃ የቡድን ሥራ፡-
በእያንዳንዱ ቡድን ውስጥ ያሉ ህጻናት ይወያያሉ እንዲሁም ለአሳዳጊዎቻቸው እና ለሁለት ወጣቶች ያሏቸውን ጥያቄዎች ያቀርባሉ። የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊዎች ጥያቄዎቹን ለታዳሚዎቹ ያቀርቡ እና አግባብነት ያላቸው ሰራተኞች መልስ ይሰጣሉ።