ክፍለ ጊዜ 20/21

ገጽ፡- 7/7: ለህጻናት እና ለወጣቶች ጠቃሚ የሆኑ ሌሎች እንቅስቃሴዎች

ለህጻናት እና ለወጣቶች ጠቃሚ የሆኑ ሌሎች እንቅስቃሴዎች

ዘላቂ የሆነ (sustainable) አኗኗርን እና ስነ-ምህዳራዊ የአትክልት ሥራን (ecological gardening) የመለማመጃ እንቅስቃሴዎች

የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደር እ.ኤ.አ. የ2030 ስትራቴጂ ሪፖርት ህጻናትን ዘላቂነት ያለው አኗኗር ስለመኖር ማስተማርን የካትታል። ከኢንዱስትሪ ዕድገት እና ከከተሞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ በርካታ አካባቢዎች ተበክለዋል (በሰው ልጆች እና በተፈጥሮ መካከል ያለው ነባር ሚዛን ታውኳል)። መጪው ትውልድ አካባቢን በመጠበቅ ይህን ሚዛን መልሶ ስለማስተካከል ያለውን ግንዛቤ መገንባት ይኖርበታል። ይህ ክፍለ ጊዜ ያገለገለ ጠርሙስን እና ፕላስቲክን መልሰው ጥቅም ላይ በማዋል አነስተኛ ገቢ ማግኘት የሚችሉበትን መንገድ ጨምሮ ለህጻናት የሚሆኑ ታሪኮችን እና እንቅስቃሴዎችን የያዘ ነው።

በሌላ የዘላቂነት ክፍለ ጊዜ ስነ-ምህዳራዊ የአትክልት ሥራ ለመስራት የሚያገለግሉ ተጨባጭ ክህሎቶችን ለመማር፣ ብዝሀ-ህይወትን ለመረዳት እና እንደ ውሀ፣ እንሰሳት እና እጽዋት ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶችን ለመጠበቅ የሚረዱ እንቅስቃሴዎችን ማቀድ ትችላላችሁ።

ህጻናትን እና ወጣቶችን ስለ መብቶቻቸው ማስተማር

በእንክብካቤ ውስጥ ያሉ ህጻናት ከኤስ ኦ ኤስ መንደር የመውጣት ምዕራፎችን በሙሉ ጨምሮ በህይወታቸው ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ማናቸውንም ጉዳዮች በተመለከተ መረጃ የማግኘት እና የመደመጥ መብት አላቸው። በህጻናት መብቶች ስምምነት (Convention on the Rights of the Child) መሠረት “እራሳቸውን በነጻነት የመግለጽ፣ እያደገ እና እየተለወጠ በሚመጣው አቅማቸው መሠረት እዲሁም አስፈላጊውን ሙሉ መረጃ ማግኘታቸውን መሠረት ባደረገ መልኩ ምክክር እንዲያደርጉ እና አስተያየታቸው ከግምት ውስጥ እንዲካተት መብት አላቸው። እንዲህ ያለውን ምክክር እና መረጃ አሰጣጥ ህጻኑ በሚመርጠው ቋንቋ እንዲከናወን ለማስቻል አስፈላጊው ጥረት ሁሉ መደረግ አለበት።” እባክዎ ገጽ ስድስትን ይመልከቱ። የአፍሪካ ህጻናትም እንዲሁ በአፍሪካ የህጻናት ቻርተር (African Children’s Charter) ጥበቃ ይደረግላቸዋል። እዚህ ጋር ዶ/ር ኤልቪስ ፎካላ ሁለቱ ስምምነቶች በአፍሪካ ቤተሰቦች ውስጥ እንዴት ተግባራዊ እንደሚደረጉ እና እንክብካቤ ሰጪዎች እና አሳዳጊዎች እንዴት ለልጆቻቸው እነዚህን መብቶች የማስተማር ግዴታ እንዳለባቸው ያስረዳሉ።

 

 

ህጻናት በእንክብካቤ ውስጥ እያሉ መብቶቻቸውን እንዲገነዘቡ እና ተግባራዊ እንዲያደርጉ የሚረዱ እንቅስቃሴዎች

በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ህጻናት ስለ መብቶቻቸው መማር ብቻ ሳይሆን በቤተሰቡ ውስጥ እንዴት ተግባራዊ እንደሚያደርጓቸውም ጭምር መማር አለባቸው። ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

አትማችሁ ለህጻናቱ ግድግዳ ላይ መስቀል የምትችሉት በቀላሉ የተዘጋጀ የመብቶቹ ዝርዝር እዚህ ጋር ቀርቧል።

በአንድ ጊዜ አንድ መብት በማቅረብ እና በቤተሰቡ ውስጥ ስላለው ትርጉም በመወያየት ህጻናት ትርጉሙን ለመረዳት ይችላሉ። ለምሳሌ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻችሁ ውስጥ ህጻናት ስለ መብቶቻቸው መማር ብቻ ሳይሆን በቤተሰቡ ውስጥ እንዴት ተግባራዊ እንደሚያደርጓቸውም ጭምር መማር አለባቸው። ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

በቤተሰቡ የዕለት ተዕለት ህይወት ውስጥ አስተያየት ለመስጠት የሚረዱ እንቅስቃሴዎች

ለምሳሌ እያንዳንዱ ህጻን ለእራት ምን መስራት እንደሚፈልግ እና ይህም ለምን ለቤተሰቡ ጤና ጥሩ ነው ብሎ እንደሚያስብ በየተራ ጠይቁ። አንዳቸው ሲናገሩ ሌሎቻቸው ከማቋረጥ ይልቅ እርስ በእርስ እንዲደማመጡ ጠይቋቸው። ከዚያም የመጨረሻውን ውሳኔ በድምጽ ብልጫ ወስኑ። እርስ በእርስ መደማመጥ እና መስማማት ከቻሉ እነሱ መወሰን እንደሚችሉ ንገሯቸው። ካልሆነ ግን አናንተው ውሳኔውን ትወስናላችሁ። ይህንን ሞዴል (መደመጥን፣ ክርክራችንን ማቅረብን እና በድምጽ ብልጫ መወሰንን መማር) ለማናቸውም የቤተሰብ ውሳኔዎች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

 

 

የሥራ ዕቅድ ርዕስ መ፡- ለዕቅድ ዝግጅት እንቅስቃሴዎች የሚደረግ የቡድን ውይይት

በማህበረሰቡ ውስጥ ህይወት በሚጀመርበት ወቅት የሚሰሩ በርካታ ሥራዎች አሉ፤ ስለሆነም እባካቸሁ ተወያይታችሁ በቅደም ተከተል አስቀምጧቸው፡- መጀመር የምትፈልጉት በየትኛው የእንቅስቃሴዎች ሀሳብ ነው? ከዚያም በአካባቢያችሁ ላሉት ፍላጎቶች ተስማሚ በሆነ መልኩ ማስተካከያ የተደረገበት ዕቅድ አዘጋጁ።

ከሚከተሉት በአጭሩ የቀረቡ ሀሳቦች ውስጥ መምረጥ ትችላላችሁ፡-

  • በዕድሜ አነስ ላሉ ህጻናት እና በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ላሉ ህጻናት የሚሆን ተጨባጭ የቤት ውስጥ ክህሎቶች ስልጠና እና ጨዋታዎች
  • ዘላቂነት ያለው አኗኗር መኖርን እና ስነ-ምህዳራዊ የአትክልት ሥራ መስራትን መለማመጃ እንቅስቃሴዎች
  • ህጻናትን ስለ መብቶቻቸው እና ተግባራዊ ማድረግ ስለሚችሉባቸው መንገዶች ማስተማር

አንድ ርዕስ ከመረጣችሁ በኋላ እባካችሁ እንዴት እና መቼ በርዕሱ ላይ እንደምትሰሩ ዕቅድ አውጡ።