ክፍለ ጊዜ፡- 20/21
ገጽ፡- 5/7: ርዕስ ሐ፡- አነስተኛ የህጻናት ማሳደጊያ ቤተሰብ ሆነው በማህበረሰቡ ውስጥ መኖር መጀመርርዕስ ሐ፡- አነስተኛ የህጻናት ማሳደጊያ ቤተሰብ ሆነው በማህበረሰቡ ውስጥ መኖር መጀመር
በርዕስ ሀ እና ለ ውስጥ በሠራችኋቸው ሥራዎች ሁሉም ወላጆች እና ህጻናት አሁን በቂ መረጃ አግኝተዋል። እባካችሁ አሥር ደቂቃ ወስዳችሁ ከሥራ ዕቅድ ለ ጋር በተያያዘ የነበሯችሁን ተሞክሮዎች በአጭሩ አስቀምጡ፡-
አሳዳጊዎች እንደመሆናችን መጠን በቤታችን ውስጥ ላሉት ህጻናት ካሳወቅንበት መንገድ ምን ትምህርት ቀሰምን?
ከኤስ ኦ ኤስ መንደር የመረጃ መስጫ ስብሰባው ምን ትምህርት ቀሰምን?
አሳዳጊዎችን እና ህጻናትን በአዲሱ ማህበረሰባቸው ውስጥ ማካተት
በአዲሱ ማህበረሰብ ውስጥ ስኬታማ በሆነ መልኩ ለማካተት ቁልፍ የሆኑ ሁለት ወሳኝ ጉዳዮች አሉ፡-
አሳዳጊዎች እና ህጻናት አዳዲስ ግንኙነቶችን እና ማህበራዊ ትስስሮችን መመስረት አለባቸው (ከጎረቤቶች እና ከልጆቻቸው ጋር፣ ከአካባቢ አመራሮች ጋር፣ ከመንገድ ላይ ነጋዴዎች፣ ከመምህራን እና ከተማሪዎች ጋር)። እንደ ማንኛውም የማህበረሰቡ አካል ተቆጥራችሁ ተቀባይነት እንድታገኙ ለማድረግ ዕቅድ ማውጣትን ይጠይቃል።
ሁለተኛው ቁልፍ የሆነ ጉዳይ በስራችሁ ያሉ ህጻናትን እና ወጣቶችን በዕለት ተዕለት ተግባራት እና እንቅስቃሴዎች ውስጥ ማካተት እና ለእነሱ ኃላፊነቶችን መስጠት ነው። አድገው እራሳቸውን የሚችሉት እና ለአዋቂነት የበቁ የማህበረሰቡ አባል ሆነው መኖር የሚችሉት ያንን ስታደርጉ ብቻ ነው። በኤስ ኦ ኤስ መንደሩ ውስጥ ሌላ ዓይነት የዕለት ተዕለት ተግባራትን ለለመዱ ህጻናት ይህ አዲስ ለውጥ ፈታኝ ሊሆንባቸው ይችላል።
የእማማ ቱሊፖን ተሞክሮዎች እናዳምጥ!
እማማ ቱሊፖ በኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊነት ጀምረው ነበር በኋላ ላይ የአደራ እናት የሆኑት። እዚህ ጋር የሳቸውን የግል ዕድገት እና የአደራ ልጆቻቸው ያስመዘገቡትን አዎንታዊ ዕድገት ይገልጻሉ።
በቡድናችን ውስጥ ዕቅድ ማቀድ፡- ከአዲሱ ማህበረሰብ ጋር ትስስር መመስረት የምንችለው እንዴት ነው?
በግልጽ መረጃ መለዋወጥ አስፈላጊ ነው የሚለው ነገር የማህበረሰቡ አባላትንም ይመለከታል። መረጃ ከሌላቸው እነሱም ስለ የማህበረሰብ አሳዳጊዎች እና ያለ ወላጅ ስለሚያድጉ ህጻናት የሀፍረት እና የተሳሳቱ አሉታዊ አመለካከቶች ሊኖሯቸው ይችላሉ። ቤተሰቡ የሚኖርበት ቤት ከተመረጠ በኋላ የሚሰሩ አንዳንድ ሥራዎችን የተመለከተ ሀሳብ እንደሚከተለው ቀርቧል (የራሳችሁን ሀሳቦች አክሉበት)።
1. ከማህበረሰብ መሪዎች፣ ከአካባቢ የመንግስት ኃላፊዎች እና ከማህበራዊ ሠራተኞች ጋር የቡድን ውይይቶችን ማድረግ
በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ የሀይማኖት እና ሀይማኖታዊ ያልሆኑ አመራሮች የአነስተኛ የጋራ መኖሪያው አባላት ስኬታማ በሆነ መልኩ መካተት ያለመካተታቸውን እና ለወደፊቱ ድጋፍ ማግኘት አለማግኘታቸውን የመወሰን አቅም ያላቸው ወሳኝ ሰዎች ናቸው። ለማህበረሰቡ አመራሮች አክብሮትን ለማሳየት ሲባል በኤስ ኦ ኤስ መንደሩ ዳይሬክተር ወይም የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ጋባዥነት የሚደረጉ የቡድን ውይይቶች መሪ-ለመሪ በሆነ መልኩ ሊዘጋጁ ይችላሉ።
በተጨማሪም እባካችሁ የአካባቢውን የመንግስት ኃላፊዎች እና ማህበራዊ ሰራተኞች በመጋበዝ የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊዋ እና ህጻናቱ ስላላቸው አዲስ የህግ አቋም እና አድራሻ ስምምነት አድርጉ እንዲሁም ለውጡን በተመለከተ ለማናቸውም ዘመዶች አሳውቁ።
2. ከአዲሶቹ ጎረቤቶች ጋር የመተዋወቂያ ዝግጅት ማዘጋጀት
የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጁ እና እናትየው በአዲሱ ቤት ውስጥ በሰፈሩ ውስጥ ካሉ ወላጆች ጋር ኢ-መደበኛ የሆነ ስብሰባ ያዘጋጃሉ። ሥራ አስኪያጁ የኤስ ኦ ኤስ ህጻናት ለምን ወደ ማህበረሰባቸው መመለስ እንደሚያስፈልጋቸው የሚያስረዳ አጭር ገለጻ ካደረገ በኋላ ድጋፋቸውን ይጠይቃል። እናትየውም የምትሰራውን ሥራ እንዲሁም ከአዲስ ጎረቤቶቿ ጋር ይበልጥ ለመተዋወቅ እንዴት ጉጉት እንዳላት ትገልጻለች። ከዚያም ሥራ አስኪያጁ ከሄደ በኋላ ሻይ ቡና እና ምግብ ቀርቦ ይበልጥ ኢ-መደበኛ የሆነ ስብሰባ ሊጀመር ይችላል። እናትየው ጎረቤቶቿን እና የአካባቢውን ባህል እና እንቅስቃሴዎች እንዴት ማወቅ እና ማክበር እንደምትችል ትጠይቃለች። የአደራ እናት ስለመሆን ማናቸውም ጥያቄዎች ያሏቸው ሰዎች ካሉም እንዲጠይቋት ትጋብዛለች። የስብሰባው መጨረሻ ላይ ህጻናቱ እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ እሷ እና ሌሎቹ ወላጆች የተለያዩ ተግባራትን እና ጨዋታዎችን የሚያዘጋጁበት አነስተኛ ግብዣ በኋላ ላይ እንዳላት ገልጻ ጎረቤቶቿን እንዲመጡ ትጋብዛቸዋለች።
3. ህጻናትን ከአዲሱ ትምህርት ቤታቸው ጋር ማስተዋወቅ
የህጻኑ (ወይም የህጻናቱ) የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊ እና መምህር ከወደፊት መምህራቸው (መምህሮቻቸው) ጋር ስብሰባ ሊያዘጋጁ ይችላሉ። ትውውቅ ካደረጉ በኋላ በአሁኑ ወቅት ያለው መምህር ህጻኑ የሚገኝበትን ሁኔታ፣ የመማር ችሎታውን እና በክፍል ውስጥ የሚያሳየውን ባህሪ ያስረዳል። እናትየው ደግሞ የስነ-ልቦና እና ማህበራዊ ችሎታዎቹን እና ጥንካሬዎቹን ትገልጻለች። ለወደፊቱ ሊከሰቱ የሚችሉ ልዩ ፍላጎቶችን እና የአካል ጉዳቶችን በተመለከተ ገጽ 22 ላይ የሚገኘውን መልሶ የመቀላቀል መመሪያ ይመልከቱ።
በትምህርት ቤቱ ትምህርት የሚጀምርበት ቀን ላይ መምህሩ ለህጻኑ አቀባበል ያደርግለታል እንዲሁም እንደ ጓደኛቸው እንዲያቀርቡት ለክፍሉ ተማሪዎች ትእዛዝ ይሰጣል። ህጻኑ የሚስማማ ከሆነ ህጻኑ እንዴት የኤስ ኦ ኤስ መንደር ውስጥ ይኖር እንደነበረ እና አሁን ደግሞ አዳዲስ ጓደኞችን ለማፍራት ጉጉት ያለው መሆኑን መምህሩ ሊገልጽ ይችላል።
የኤስ ኦ ኤስ መንደሩ ከትምህርት ቤቱ የማይርቅ ከሆነ የክፍሉ ተማሪዎች የኤስ ኦ ኤስ መንደሩን ሊጎበኙ እና በኤስ ኦ ኤስ መንደሩ ውስጥ ስለመኖር ሊማሩ ይችላሉ እንዲሁም ጨዋታዎች እና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ሊዘጋጁ ይችላሉ።
የሥራ ዕቅድ ርዕስ ሐ፡- ስጋቶችን ለመቀነስ የሚደረግ የቡድን ውይይት እና የጉዳይ ጥናት
- በእነዚህ የትውውቅ ሀሳቦች ላይ በአካባቢአችን ላለው ሁኔታ ተስማሚ በሆነ መልኩ ማስተካከያ ልናደርግባቸው የምንችለው እንዴት ነው?
- ሊኖሩ የሚችሉ ስጋቶችን አስቀድሞ ለማወቅ እና ለመከላከል እባካችሁ ይህን የጉዳይ ጥናት አንብቡት እንዲሁም ከአንዲት የአደራ እናት እና ከሴት የአደራ ልጇ ጋር ተወያዩበት።
- እባካችሁ የአደራ ቤተሰቡን በማህበረሰቡ ውስጥ የምታካትቱበትን የሥራ ዕቅድ አዘጋጁ።
- እባካችሁ ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ከወጡ በኋላ በአሳዳጊዎች እና በህጻናት ላይ መደበኛ ክትትል እና ቃለ መጠይቆች የምታደርጉበትን የሥራ ዕቅድ አዘጋጁ።