ክፍለ ጊዜ 21/21

ገጽ፡- 4/6: ርዕስ ሐ፡- የህጻኑን ወይም የወጣቱን ግንኙነቶች እና ቁርኝቶች መለየት

ርዕስ ሐ፡- የህጻኑን ወይም የወጣቱን ግንኙነቶች እና ቁርኝቶች መለየት

አንድ ህጻን ወይም ወጣት ከቤተሰቡ ጋር መልሶ እንዲዋሀድ በሚመረጥበት ወቅት ውይይት ሊደረግበት እና ሊታቀድ የሚገባው ጉዳይ ምንድን ነው?

የግለሰቡን ማህበራዊ ግንኙነቶች በሙሉ በትክክል መገምገም የምንችለውስ እንዴት ነው?

 

 

 

 

 

 

 

 

 

አንድ ህጻን ከቤተሰቡ ጋር መልሶ ለመዋሀድ ዝግጁ የሚሆነው መቼ ነው?

አንድን ህጻን ወይም ወጣት ከቤተሰቡ ጋር መልሶ እንዲዋሀድ የመምረጡ ስራ በተናጠል የሚከናወን ሂደት ነው። እያንዳንዱ ጉዳይ የተለየ ነው። ማናቸውንም ተጨባጭ እና ወሳኝ ጉዳዮች በተመለከተ እባክዎ ይህን መመሪያ ይመልከቱ።

ከቤተሰብ ጋር መልሶ መዋሀድ ስኬታማ እንዲሆን ዋነኛው ወሳኝ የሆነ ጉዳይ አስተማማኝ የሆነ የግንኙነት ትስስር መኖሩ እንደሆነ ጥናቶች ይጠቁማሉ።

ትክክለኛውን ህጻን ወይም ወጣት የመምረጥ ያለመምረጡን ጉዳይ በአብዛኛው የሚወስነው የሥራ አስኪያጆች እና የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊዎች የሚወስዱት ግምት፣ ህጻኑን በቅርበት ማወቃቸው እና በሠራኞች መካከል ያለው ቅርርብ እና ተጋግዞ የመስራት ሁኔታ ነው። መረጃን መሰረት ያደረጉ ውሳኔዎችን ለመወሰን እንዲረዳዎት ከቤተሰብ ጋር መልሶ ከመቀላቀል ጋር የተያያዙ አንዳንድ ተሞክሮዎች እና በእንክብካቤ ሰጪ ለውጦች ዙሪያ የተሰሩ ጥናቶች እዚህ ጋር ቀርበዋል። ጠቅለል ያሉ በመሆናቸው የግድ ለእያንዳንዱ ህጻን አግባብነት ላይኖራቸው ይችላል (እባካችሁ እያንዳንዱን ጉዳይ በተመለከተ ሞያዊ ግምታችሁን አክሉበት)።

አንድ ህጻን ወይም ወጣት የእንክብካቤ ሰጪዎች ለውጥ ለማድረግ ዝግጁ የሚሆነው መቼ ነው?

በአጠቃላይ ማንኛውም ዕድሜ ላይ ያሉ ህጻናት ከቤተሰባቸው ጋር መልሰው ለመዋሀድ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። በተግባር ሲታይ አብዛኛውን ጊዜ ከቤተሰባቸው ጋር መልሰው የሚዋሀዱት በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ልጆች እና ወጣቶች ናቸው።

አንድ ህጻን ዕድሜው ባነሰ ቁጥር ከአንድ እንክብካቤ ሰጪ ወደ ሌላ እንክብካቤ ሰጪ ለመሸጋገር ከሚኖረው ችሎታ አንጻር ይበልጥ ለለውጥ ምቹ ይሆናል። ከሦስት ዓመት ዕድሜ በታች ያሉ ህጻናት አብዛኛውን ጊዜ ከአዲስ እንክብካቤ ሰጪ ጋር አስተማማኝ ቁርኝት መመስረት እንደሚችሉ ጥናቶች ያሳያሉ። ለአንድ ዓመት አካባቢ ያህል አብረው ከኖሩ በኋላ ጨቅላው ወይም ድክ ድክ የሚለው ህጻን አዲሱን እንክብካቤ ሰጪውን በስሜት ወላጁ አድርጎ ማየት የሚጀምር በመሆኑ ሽግግሩ ስኬታማ ይሆናል።

ከሦስት ዓመት አንስቶ እስከ አሥራ ሁለት ዓመት አካባቢ ዕድሜ ያላቸው ህጻናትን በተመለከተ በተለይም ደግሞ ህጻኑ ከኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊው ጋር ለመቆራኘት አጭር ጊዜ ብቻ የነበረው ከሆነ ሽግግሩ ፈታኝ ሊሆን ይችላል። እዚህ ወቅት ላይ ወሳኝ ክህሎቶችን፣ ጨዋታን እና ትምህርትን ለማዳበር የስሜት እና አካላዊ መረጋጋት አስፈላጊ ናቸው። ለውጥ ህጻኑ ትምህርት ላይ ያለውን ብቃት ሊያውክ እና ከእኩዮቹ ጋር ያለውን ማህበራዊ ትስስር ሊያቋርጠው ይችላል። አንድ ህጻን በሂደት ከቤተሰቡ ጋር እንዲዋሀድ ህጻኑ ከፍተኛ ተነሳሽነት ሊኖረው እና ቤተሰቡ ውስጥ አስተማማኝ የሆነ የልጅ አስተዳደግ ክህሎት ሊኖር ይገባል። 

በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ልጆች እና ወጣቶች አብዛኛውን ጊዜ ፍላጎቶቻቸውን እና ምኞቶቻቸውን መገንዘብ እና መግለጽ እንዲሁም ከቤተሰባቸው ጋር መልሶ መዋሀድን በተመለከተ መረጃን መሰረት ያደረጉ ምርጫዎችን ማድረግ ይችላሉ። እዚህ ወቅት ላይ የወላጅ እንክብካቤ ከሚያደርጉላቸው ሰዎች ጋር መለያየት እና እራስን ችሎ መኖር ተፈጥሮአዊ ነው። ወጣቶች ከኤስ ኦ ኤስ መንደሩ ውጭ ባለው ህይወት ዙሪያ ተሞክሮዎች አሏቸው፤ አብዛኛውን ጊዜም የማህበረሰቡ አካል የመሆን ፍላጎት አላቸው። የጉርምስና መጀመር የስሜት እና አካላዊ ያለመረጋጋቶችን ሊፈጥር ስለሚችል ብስለት እስከሚመጣ ድረስ መቆየትን ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል።

 

ልዩ ፍላጎቶች ያሏቸው ወይም ሌሎች የአካል ወይም የአእምሮ ጉዳቶች ያሉባቸው ህጻናት

የአካል ወይም የአእምሮ ጉዳት ያለባቸውን ህጻናት ከትውልድ ቤተሰባቸው ጋር መልሶ መቀላቀል ብዙ ማህበረሰቦች ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ፈታኝ ነው። በመጀመሪያ ከቤተሰባቸው ጋር መልሰው የሚዋሀዱት ስኬታማ በሆነ መልኩ በማደግ ላይ ያሉ እና ለውጥን ለመላመድ ይችላሉ ተብለው የሚጠበቁ ህጻናት ወይም ወጣቶች እንዲሆኑ ይመከራል። በዚህም ሠራተኞች ይበልጥ ፈታኝ ለሚሆነው የአካል ወይም የአእምሮ ጉዳተኛ የሆኑ ልጆችን መልሶ የመቀላቀል ሥራ ልምድ ያካብታሉ። በምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ የነበሩ ተሞክሮዎችን የያዙት እነዚህ መመሪያዎች ሂደቱን ለማቀድ ያግዟችኋል።

 

 

30 ደቂቃ የቡድን ውይይት

እባካችሁ ተወያይታችሁ እንደራሳችሁ እሳቤዎች የሥራ ዕቅድ አዘጋጁ፡-

  • አንድ ህጻን ወይም ወጣት ስንት ዓመት ሊሆነው ይገባል የሚለውን በተመለከተ ያለን ሀሳብ ምድን ነው?
  • ከዕድሜ ጋር በተያያዘ ምን ምን መልካም ዕድሎችን እና ስጋቶችን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለብን?
  • የአንድ ህጻን ከቤተሰቡ ጋር መልሶ ለመዋሀድ ዝግጁ መሆን፡- ይህን ዕውቀት በምን መልኩ ተግባራዊ ልናደርገው እንችላለን?

በመቀጠል የአንድን ህጻን በርካታ ትስስሮች እና ቁርኝቶች በትክክል ለመገምገም የሚያገለግል አንድ መገልገያ መጠቀም ትችላላችሁ።

 

የህጻናት እና የወጣቶች ግንኙነት እና ቁርኝት ፍኖተ ካርታ አጠቃቀም

 

አንድ ህጻን ያሉትን በጣም ወሳኝ የሆኑ ትስስሮች እና ግንኙነቶች ጠቅላላ ቅኝት (ከቤተሰቡ ጋር መልሶ ከመዋሀዱ በፊት፣ በሚዋሀድበት ወቅት እና ከተዋሀደ በኋላ) ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?

ህጻኑ አስተማማኝ በሆነ መልኩ የተቆራኘው ከማን ጋር ነው የሚለውን በተመለከተ ሥራ አስኪያጆች እና እንክብካቤ ሰጪዎች የራሳቸውን ግምገማ ማናወናቸው አስፈላጊ ነው። የህጻኑን የራሱን አመለካከት ማወቅም እንዲሁ፡- የመተማመን እና በጣም የመቀራረብ ስሜት የሚሰማው ከማን ጋር ነው፤ ያለመተማመን ስሜት የሚሰማውስ ስለማን ነው? በተጨማሪም ዘመዶቹ ከህጻኑ ጋር ያላቸውን ግንኙነት የሚገልጹት በምን መልኩ ነው? ይህን ፍኖተ ካርታ መጠቀም በውይይቶች አማካኝነት መልሶችን ለማግኘት ያግዝዎታል።

የቁርኝት ፍኖተ ካርታው ለመጠቀም ቀላል ነው። ዓላማው ለሚመለከታቸው ሰዎች በሙሉ ግልጽ የሆነ ጠቅላላ ቅኝት መስጠት ነው፡- ህጻኑ ወይም ወጣቱ ቁርኝት ያለው ከማን ጋር ነው? የመተማመን ወይም ያለመተማመን ስሜት የሚፈጥርበት ማን ነው?

ፍኖተ ካርታው የአንድን ህጻን ወይም ወጣት ማህበራዊ ትስስር ጥራት የምትገመግሙባቸው ሦስት የእይታ አቅጣጫዎቸን ይሰጣችኋል፡-

ሞያዊ እይታ፣ የህጻኑ እይታ እና የዘመዶቹ እይታ።

እባካችሁ የህጻናት እና የወጣቶች ግንኙነት እና ቁርኝት

ፍኖተ ካርታውን ከፍታችሁ ፕሪንት አድርጉ። የሚያስፈልገውን ያህል ብዛት ፕሪንት አድርጉ እና መመሪያውን ከመጠቀማችሁ በፊት አንብቡት።

ፍኖተ ካርታውን በሚከተለው አግባብ እንድትጠቀሙት እንመክራለን፡-

  • የኤስ ኦ ኤስ እናቶች እና የፕሮግራም ስራ አስኪያጆች ፍኖተ ካርታውን ይሞላሉ፡- ይህ ህጻን ወይም ታዳጊ ያሉትን ወሳኝ ቁርኝቶች በተመለከተ ያለን ሞያዊ እይታ ምንድን ነው?
  • የህጻኑን እይታ በተመለከተ፡- ህጻኑን ወይም ወጣቱን የሚያውቀው አንድ ሰው ቃለ መጠይቅ ይደረግለታል እንዲሁም ፍኖተ ካርታውን በመሙላት ያግዛል። የህጻኑን ወሳኝ የሆኑ አስተማማኝ የሆኑ እና አስተማማኝ ያልሆኑ ግንኙነቶች የሚገልጸው በምን መልኩ ነው?
  • ዘመዶቹን በቤታቸው መጎብኘት፡- ፍኖተ ካርታውን ማቅረብ እና እንዲሞሉት ማገዝ። ከህጻኑ ጋር እራሳቸው ያላቸውን ቁርኝት የሚያዩት እንዴት ነው? ህጻኑ እንዴት ያየናል ብለው ያስባሉ?

ህጻኑ ከትውልድ ቤተሰቡ ጋር መልሶ በሚቀላቀልበት ወቅት ሰዎች ያሏቸው አመለካከቶች ይቀየራሉ፤ ስለዚህ እባካችሁ ፍኖተ ካርታውን ህጻኑ ከቤተሰቡ ጋር መልሶ ከመዋሀዱ በፊት፣ በሚዋሀድበት ወቅት እና ከተዋሀደ በኋላ ተጠቀሙ። ከሦስቱ ምዕራፎች ውስጥ የትኛውም ምዕራፍ ላይ ፍኖተ ካርታውን ከተጠቀማችሁ በኋላ እባካችሁ እንደሚከተለው ውይይት አድርጉ እንዲሁም ዕቅድ አውጡ፡-

 

 

የ45 ደቂቃ የቡድን ውይይት እና የሥራ ዕቅድ፡-

  • ሦስቱ እይታዎች (ሞያዊ፣ የህጻኑ እና የቤተሰብ) ይጣጣማሉ ወይስ የተለያዩ ናቸው?
  • በሂደቱ ውስጥ የሚሳተፉ ሰዎች በሙሉ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ የምንሰራው በምን መልኩ ነው?
  • አስተማማኝ ቁርኝቶችን ማጠናከር እና ለማያስተማምኑት ግንኙነቶች መፍትሄ ማበጀት የምንችለው በምን መልኩ ነው?

ግምገማዎቻችሁ ለመቀጠል እንድትወስኑ ካደረጓችሁ ቀጣዩን እርምጃ የምታቅዱበት ጊዜ ደርሷል ማለት ነው፡-

ከመንግስት ሠራተኞች ጋር በመስራት አስተማማኝ በሆነ ከባቢ ሁኔታ ውስጥ ህጻኑን ለመቀበል ማህበረሰቡን እና ቤተሰቡን ማዘጋጀት።