ክፍለ ጊዜ 21/21

ገጽ፡- 3/6: ርዕስ ለ፡- የኤስ ኦ ኤስ እናቶች ለሽግግሩ መዘጋጀት የሚችሉት በምን መልኩ ነው?

ርዕስ ለ፡- የኤስ ኦ ኤስ እናቶች ለሽግግሩ መዘጋጀት የሚችሉት በምን መልኩ ነው?

በርዕስ ለ ውስጥ ከቤተሰብ ጋር መልሶ ለመዋሃድ በሚደረገው ዝግጅት ውስጥ ወሳኝ የሆነ አንድ የስነ-ልቦና ሂደት ላይ ትሰራላችሁ፡- የኤስ ኦ ኤስ እናቶች አንድን ህጻን በሚያስረክቡበት ወቅት የመተማመን ስሜት እና አዎንታዊ ስሜት ሊሰማቸው የሚችለው እንዴት ነው?

የኤስ ኦ ኤስ እናቶች አንድን ህጻን ለማስረከብ እራሳቸውን ማዘጋጀት የሚችሉት እንዴት ነው?

በአማራጭ እንክብካቤ ውስጥ ያሉ ህጻናት እና ታዳጊዎች እንክብካቤ ሰጪዎቻቸው የሚሰሟቸው ስሜቶች በቀላሉ ተጽዕኖ ያሳድሩባቸዋል። በተለይም ደግሞ የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊአቸው የስሜት ድባብ ተጽዕኖ ያሳድርባቸዋል።

የህጻኑ የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊ ከቤተሰቡ ጋር መልሶ መዋሀዱ ለህጻኑ የላቀ ጥቅም የሚያስገኝ ነው ብሎ ማመኑ እና የመተማመን ስሜት የሚሰማው መሆኑ በጣም አስፈላጊ ነው። እያንዳንዱ ጥርጣሬ እና ጭንቀት በጥልቀት ውይይት ተደርጎበት ካልተፈታ በስተቀር አንድ ባለሞያ አሳዳጊ አንድን ህጻን ለሌሎች ሰዎች በሚያስረክብበት ወቅት እንደተረጋጋ ማስመሰል አይችልም።

ማንኛውም የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊ አንድን ህጻን ለቤተሰቦቹ በሚመልስበት ወቅት የሚሰማው ተፈጥሮአዊ ስሜት ሀዘን (ከሚወዱት ህጻን ወይም ወጣት ጋር መለያየት የሚፈጥረው የህመም ስሜት) ሊሆን ይችላል። ህጻኑ ወይም ወጣቱ ለዜናው ምን ዓይነት ምላሽ ይኖረዋል (አስተማማኝ የሆነ ቁርኝት አለኝ የሚለውን ስሜት ያጣው ይሆን?) የሚል ፍርሀትም እንዲሁ።

ነገር ግን ከትውልድ ቤተሰብ ጋር መልሶ መቀላቀል አሰቃቂ በሆነ መልኩ መለያየት ማለት አይደለም። ነገሩን ከልብ መቀበል ማለት በሂደት ህጻኑን ከቤተሰቦቹ ጋር የመጋራት እና ህጻኑ በትውልድ ቤተሰቡ ውስጥ ተጨማሪ አስተማማኝ ቁርኝቶች እንዲኖሩት የማገዝ ረጅም ጊዜ የሚወስድ ሂደት ነው። “ይህ የእኔ ልጅ ነው” ከሚለው ስሜት “ይህ የእኛ ልጅ ለው” ወደሚለው ስሜት መሸጋገር ጊዜ ይወስዳል።

 

 

አንዲት ፍቅር የተሞላች የኤስ ኤስ እናት እና የህጻኑ ቤተሰብ እንዴት ስኬታማ በሆነ መልኩ አንድን ህጻን እንደተጋሩት የሚያስረዳውን ይህን ምሳሌ አድምጡት፡አንዲት ህጻን ከቤተሰቦቿ ጋር መልሳ ከተዋሀደች ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የኤስ ኤስ መንደር ውስጥ ወዳለችው የኤስ ኤስ እናቷ ለአንድ ወር ያህል ለመመለስ ዕድሉ ተሰጣት፤ ነገር ግን ታናሽ እህቷን ከመንከባከብ ጋር ተያይዞ በጣም ከታናሽ እህቷ ጋር ተቆራኝታ ስለነበር ለአጭር ጊዜ ብቻ ወደ

ኤስ ኦ ኤስ መንደሩ ለመመለስ ወስናለች!

60 ደቂቃ የቡድን ውይይት፡

እባካችሁ ስሜቶቻችሁን፣ ጥርጣሬዎቻችሁን እና ተስፋዎቻችሁን በነጻነት ግለጹ፡-

  • ልጃችንን ለዘመዶቹ በምናስረክብበት ወቅት የሚሰሙን የግል ስሜቶች መንድን ናቸው?
  • ነገሩን ለመቀበል ከባድ ያደረጉብኝ በራሴ ህይወት ውስጥ ያጋጠሙኝ ከባድ መለያየቶች ነበሩ?
  • ህጻኑ ከቤተሰቡ ጋር መልሶ መዋሀዱን ለመቀበል የስነ-ልቦና ምክር ያስፈልገኛል?
  • ከቤተሰባቸው ጋር መልሰው መዋሀዳቸው ከህጻናቱ ጋር ባለን ቁርኝት እና ግንኙነት ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ ያሳድራል?
  • ከቤተሰብ ጋር መልሶ መዋሀድ የሚለው ነገር የወደፊት ሥራዬ ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ ያሳድራል?

    እነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች አዎንታዊ በሆነ መልኩ ነገሩን መቀበል ላይ እስከሚደረስ ድረስ በሂደቱ ውስጥ በርካታ ጊዜ ውይይት ሊደረግባቸው ይችላል።

    ቀጣዩ የሚጠበቅ ጥያቄ የሚከተለው ነው፡- አንድ ህጻን ከቤተቡ ጋር እንዲቀላቀል በሚመረጥበት ወቅት ምን ከግምት ውስጥ መግባት አለበት?