ክፍለ ጊዜ 21/21

ገጽ፡- 6/6: ርዕስ ሠ፡- ከቤተሰብ ጋር መልሶ ከመዋሀድ በኋላ ክትትል በማድረግ ስጋቶችን መቀነስ

ርዕስ ሠ፡- ከቤተሰብ ጋር መልሶ ከመዋሀድ በኋላ ክትትል በማድረግ ስጋቶችን መቀነስ

በመልሶ መቀላቀል ዙሪያ በተሰሩ የሙከራ ጥናቶች ከመልሶ መዋሀድ በኋላ በምትሰሩት ሥራ ውስጥ ልዩ ትኩረታችሁን የሚሹ በርካታ የተለመዱ ስጋቶች እንዳሉ ከኤስ ኦ ኤስ የሙከራ ጥናቶች ለማወቅ ተችሏል። 

መቆራረጥ እና ከትውልድ ቤተሰብ ተለይተው የሚያልፍ ጊዜ ርዝመት

በኤስ ኦ ኤስ መንደር (ወይም በሌሎች ሁኔታዎች) ውስጥ ማደግ ከዘመዶች ጋር ያሉ ወሳኝ ቁርኝቶችን ጨምሮ ከአካባቢው ባህል ጋር መቆራረጥን አስከትሎ ሊሆን ይችላል። ታዳጊ ወይም ወጣቱ ከአፍ መፍቻ ቋንቋው ውጭ ሌላ ቋንቋ ተምሮ ሊሆን ይችላል። ሌላ አመለካከት አዳብሮ ሊሆን ወይም ደግሞ ይበልጥ በራሱ የሚያስብ፣ ይበልጥ የተማረ እና በትውልድ ባህሉ ውስጥ የተለመደው ያህል ታዛዥ ያልሆነ ሆኖ ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም ከዘመዶቹ ጋር ያለው የስሜት ቁርኝት ሊጠፋበት እና መጀመሪያ ላይ እንደ ባዳ ሊያያቸው ይችላል። የወጣቶቹ የትምህርት ደረጃም በአዲሱ ትምህርት ቤት ውስጥ ካለው ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል። በእነዚህ ልዩነቶች የተነሳም የክፍላቸው ተማሪዎች ሊያገሏቸው ይችላሉ።

 

ሰነዶች፡- የመታወቂያ ወረቀቶች እና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ማግኘት

በመልሶ መቀላቀል ወቅት የሚገጥሙ ተግዳሮቶች ምሳሌ እንደሚከተለው ቀርቧል፡- የኤስ ኦ ኤስ ሀጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ  ብሔራዊ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሳህለማርያም አበበ፡- “የእኛ ልጆች በሕጉ መሠረት የእንክብካቤ ሰጪዎቹ ልጆች ተብለው የተመዘገቡ ናቸው። እንደ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት ያሉ በርካታ ለከፍተኛ ስጋት ተጋላጭ የሆኑ ህጻናት እና ወጣቶች የህክምና አገልግሎትን፣ የመንግስት ትምህርት ቤቶችን፣ ፓስፖርትን፣ ወዘተ ተደራሽ የሚያደርግላቸውን የመታወቂያ ካርድ ማግኘት አይችሉም። አንድ ሰው የመታወቂያ ካርድ ማግኘት የሚችለው የተመዘገበ ቤት ወይም ንብረት ባለቤት የሆነ ሰው ማቅረብ የሚችል ከሆነ ብቻ ነው። የበርካታ ወላጆች እና ህጻናት አንደኛው ስጋት ይህ ነው”።

 

የመጀመሪያው ዓመት ላይ ቤተሰቡ እና ህጻኑ ወይም ወጣቱ ላይ የሚደረግ ክትትል

ከቤተሰብ ጋር መልሰው በሚዋሀዱበት ወቅት የባህል እና የስሜት መልሶ መዋሀድ ገና ጅማሮ ላይ የሚሆን በመሆኑ ዘላቂ ስኬት እንዲመጣ ክትትል አስፈላጊ ነው። የኤስ ኦ ኤስ እናቶች፣ የቤተሰቡ እና የህጻኑ ጭንቀት በከፍተኛ ሁኔታ የሚጨምረው ከመልሶ መቀላቀል በኋላ ከአንድ ዓመት በፊት እና በኋላ እንደሆነ ጥናቶች ይጠቁማሉ። ይህም በተደጋጋሚ በመጋጨት፣ ባለመግባባት እና በሂደቱ ውስጥ የሚሳተፉ ሰዎች በሙሉ በሚያቀርቧቸው ቅሬታዎች ሊገለጽ ይችላል።

ችግሮችን በተረጋጋ እና ስልታዊ በሆነ መልኩ ለመተንተን እና ለመፍታት የግንኙነት እና ቁርኝቶች ፍኖተ ካርታውን በምክክሮች እና በውይይቶች ውስጥ ተጠቀሙ። ማናቸውንም ተግዳሮቶች እና ያለመግባባቶች ለመፍታት የመጀመሪያው ዓመት ላይ የሚረገው መደበኛ ክትትል የቤተሰብ ምክር አገልግሎትን ያካተተ መሆን አለበት።

የቡድን ውይይት እና የሥራ ዕቅዶ

  • ህጻኑን ወይም ወጣቱን የአካባቢውን ባህል እንዲላመድ መንገር እና ማዘጋጀት የምችለው እንዴት ነው?
  • በዕለት ተዕለት ከባቢ ሁኔታ ውስጥ የተሳሳተ አመለካከትን እና ማግለልን ለመከላከል መስራት የምንችለው እንዴት ነው?
  • ከመንግስት ሠራተኞች ጋር በመሆን የሕግ ሥነ-ስርዓቶችን ማቀላጠፍ የምንችለው እንዴት ነው?

በቤተሰቡ እና በህጻኑ ላይ ክትትል የምናደርገው የት እና እንዴት ነው?