ክፍለ ጊዜ 21/21
ገጽ፡- 5/6: ርዕስ መ፡- ከመንግስት ሠራተኞች፣ ከማህበረሰቡ እና ከቤተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ መስራትርዕስ መ፡- ከመንግስት ሠራተኞች፣ ከማህበረሰቡ እና ከቤተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ መስራት
ከአካባቢው የመንግስት ሠራተኞች ጋር አብሮ መሥራት
መልሶ መቀላቀል ስኬታማ እንዲሆን ከአካባቢ የመንግስት ሠራተኞች ጋር በቅርበት ተቀናጅቶ መሥራትን እንዲሁም የሚመለከተውን ህጻን ወይም ወጣት መቆጣጠራችሁን ይጠይቃል። የህጻኑን አዲስ ይፋዊ ማንነት የሚመለከቱ ህጋዊ ውሳኔዎች በሙሉ መታቀድ እና መፈጸም ያለባቸው ከህጻናቱ ጋር በመሆን ነው። ከጊዜ ሰሌዳዎች እና ከሚያስፈልጉ ነገሮች ጋር በተያያዘ ያሉ የሕግ ሥነ-ስርዓቶች እና ተግዳሮቶቻቸው ከሀገር ሀገር ይለያያሉ። በዚህ ረገድ ዓላማችን በመጠበቅ የሚያልፉትን ጊዜያት በተቻለ መጠን ማሳጠር ነው፤ በተለይም ደግሞ ህጻኑ ከትውልድ ቤተሰቡ ጋር መልሶ ከመዋሀዱ በፊት ጊዜያዊ የአደራ ቤተሰብ ውስጥ ከተቀመጠ።
በኤስ ኦ ኤስ ሀዋሳ፣ ኢትዮጵያ የአካባቢ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ በረከት ሠራተኞች ከአካባቢ ባለስልጣን አካላት ጋር እንዴት ተቀናጅተው እንደሚሰሩ ያብራራሉ።
ከትውልድ ቤተሰብ ጋር መልሶ መቀላቀልን በማህበረሰቡ ውስጥ ማስተዋወቅ
ሌላኛው ወሳኝ ሥራ የሀይማኖት እና ሀይማኖታዊ ያልሆኑ የማህበረሰብ መሪዎችን ማዘጋጀት ነው። መልሶ መቀላቀል እና በአካባቢ ደረጃ እንክብካቤን ማጠናከር የሚለውን ጠቅላላ ሀሳብ ማብራራት ስለ ህጻኑ እና ስለ ዘመዶቹ አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖር ያደርጋል። በአካባቢው ባሉ ህዝባዊ ዝግጅቶች እና በቴሌቪዥን ወይም በሬዲዮ ላይም ሊከናወን ይችላል።
በኤስ ኦ ኤስይሀጻናት መንደር ሀዋሳ ፕሮግራም፣ የአማራጭ ህጻናት ክብካቤ ማናጀር የሆኑት አቶ በረከት ለማህበረሰብ መሪዎች እንዴት እንደምናሳውቅ ያብራራሉ።
ህጻኑን ከትምህርት ቤቱ ጋር ማስተዋወቅ እና ትምህርት
ህጻኑ ትምህርት ውስጥ መልሶ መቀላቀሉን ለማረጋገጥ ህጻኑ ወይም ወጣቱ ከማህበራዊ ክህሎቶች አንጻር ስለሚገኝበት ሁኔታ ለወደፊት የመጀመሪያ ደረጃ ወይም የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራኑ መረጃ ሊሰጣቸው ይችላል። ከአካላዊ ወይም ከመማር ችሎታ ጋር የተያያዙ ጉዳቶችን ወይም ልዩ ፍላጎቶችን ለተመለከቱ መረጃዎች ልዩ ትኩረት ስጡ።
እንደ ሁኔታው አንድ መምህር አዲሱን ተማሪ አስቀድመው እንዲያስተዋውቁት እና የክፍሉ ተማሪዎቸ እንደጓደኛ እንዲያካትቱት እንዲያሳስቧቸው ልትጠይቁ ትችላላችሁ። ይህም ከዕድሜ አቻዎቹ ሊመጡ ይችላሉ ተብለው የሚጠበቁ ማናቸውንም የተሳሳቱ አመለካከቶች መፍታትን ያካትታል። ስለ ጀርባ ታሪኩ ግልጽ መሆን የሚመረጥ ቢሆንም በጣም የተሻለው የማስተዋወቂያ መንገድ የህጻኑን ወይም የወጣቱን ምርጫ ማክበር ነው።
ወደ ትውልድ ቤተሰብ መመለስን ማመቻቸት
መልሶ የመቀላቀል ሂደቱን ለማስጀመር የህጻኑ ዘመዶች የኤስ ኦ ኤስ መንደሩን እንዲጎበኙ ሊታቀድ ይችላል። በአንደኛው ጉብኝት ወቅት አብሮ ምግብ እንደማብሰል ያሉ ተጨባጭ እንቅስቃሴዎችን ልታዘጋጁ ትችላላችሁ። ይህን ማድረግ ህጻኑ እና የቤተሰቡ አባላት የሚያደርጓቸውን መስተጋብሮች ለማስተዋል ይረዳችኋል እንዲሁም ከህጻናት እና ወጣቶች የግንኙነት እና ቁርኝት ፍኖተ ካርታው ባስተዋላችሁት ነገር ላይ ተጨማሪ መረጃ ይሰጣችኋል። ህጻኑ እምነት በተሞላበት መልኩ መስተጋብር የሚያደርገው ከማን ጋር ነው? እገዛ፣ እንክብካቤ እና ከለላ ሲፈልግ ወደ ማን ነው የሚሄደው? ያለመተማመን፣ የፍርሀት እና የመራቅ ስሜት የሚየያሳየውስ ማን ላይ ነው? ከዚያም ማናቸውም ያለመተማመን ስሜቶች በግልጽ ውይይት ተደርጎባቸው ሊፈቱ ይችላሉ።
ይህ ሂደት ህጻኑን በቤተሰቡ ውስጥ ለሚያሳልፈው ጊዜ ያዘጋጀዋል።
የቡድን ውይይት እና የሥራ ዕቅድ
እባካችሁ ተወያይታችሁ አቅዱ፡-
- ማናቸውንም የህግ ችግሮች ለመፍታት ከመንግስት ሠራተኞች ጋር ተቀናጅተን መስራት የምንችለው እንዴት ነው?
- መልሶ ስለመቀላቀል በማህበረሰብ መሪዎች ዘንድ ግንዛቤ መፍጠር የምንችለው እንዴት ነው?
- ለህጻኑ አቀባበል እንዲያደርጉለት መምህራንን እና የዕድሜ እኩዮቹን ማዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?
- በቤተሰብ ጉብኝቶች ወቅት መተማመን ያለባቸው እና መተማመን የሌለባቸው መስተጋብሮችን ማስተዋል የምንችለው እንዴት ነው?