ክፍለ ጊዜ 20/21
ገጽ 2/7፡- ከኤስ ኦ ኤስ መንደር በመውጣት የማህበረሰብ አሳዳጊ መሆን ለምን አስፈለገ? ስለ አዲሱ የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች ስትራቴጂከኤስ ኦ ኤስ መንደር በመውጣት የማህበረሰብ አሳዳጊ መሆን ለምን አስፈለገ? ስለ አዲሱ የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች ስትራቴጂ
ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች ወላጆችቻቸውን ያጡ ህጻናትን ከአካባቢ ጦርነት እና ያለመረጋጋት ለመከላከል ከፍተኛ ጥራት ያለው እንክብካቤ እና ትምህርት የሚሰጡ የህጻናት ማሳደጊያዎች በመሆን እ.ኤ.አ. በ1949 የተቋቋመ ድርጅት ነው። በአሁኑ ወቅት የኤስ ኦ ኤስ መንደሮች ዓላማ በማህበረሰቦች ውስጥ ብሔራዊ የአቅም ግንባታን ማነሳሳት እና መደገፍ ነው። አዲሱ የኤስ የኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች ስትራቴጂ 2030 እና “ጥራት ያለው አማራጭ እንክብካቤ” የተሰኘው ፕሮግራም ህጻናት በትውልድ አካባቢ ባህላቸው ውስጥ ለማደግ ላላቸው መብት አጽንኦት የሚሰጥ ነው። እ.ኤ.አ. 2030 ላይ አብዛኛዎቹ በኤስ ኦ ኤስ መንደሮች ውስጥ ያሉ ህጻናት የማህበረሰብ አሳዳጊዎች ሆነው ከሚያገለግሉ የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊዎቻቸው ጋር የሚኖሩ ወይም ከዘመዶቻቸው ጋር መልሰው የሚዋሀዱ ይሆናል። ይህ ከፍለ ጊዜ በአነስተኛ የጋራ መኖሪያ ውስጥ የአካባቢ የኤስ ኦ ኤስ የማህበረሰብ አሳዳጊ ሆኖ ወደመኖር የሚደረገውን ሽግግር ለማቀድ የሚያገለግል ነው። (ህጻናትን ከቤተሰቦቻቸው ጋር መልሶ ማገናኘትን በተመለከተ እባክዎ ክፍለ ጊዜ 21ን ይመልከቱ።)
የህጻናት እና የወጣቶች እድገት ከኤስ ኦ ኤስ መንደሮች ከወጡ በኋላ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚሻሻል በአሰራሩ ላይ ከተደረጉ የሙከራ ጥናቶች ለማወቅ ችለናል። በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በማህበረሰብ ውስጥ ልጆች አሳዳጊ የሆኑ የቀድሞ የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊዎች ከበፊቱ በተሻለ በጣም ጥሩ ህይወት እየኖሩ እንደሆነ ይናገራሉ። ስኬታማ የሆነ መልሶ መቀላቀል እንዲኖር በእርጋታ የሚጓዝ እና በአግባቡ የታቀደ ሂደት ለወላጆች እና ለህጻናት እንደሚያስፈልግ ሪፖርቱ ያሳያል። በዚህ ከፍተኛ የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ውስጥ አልፎ በማህበረሰብ ውስጥ የመኖርን ጥቅሞች ማጣጣም የሚችሉበት ሁኔታ ላይ ለመድረስ በቡድን ውይይቶች ውስጥ ዕቅድ ማውጣትን እና ከህጻናት ጋር በርካታ ውይይቶችን ማድረግን የሚጠይቅ ነው። |
ብሔራዊ ዳይሬክተር የሆኑት ኪሰቶ ሞስራዊ የቦትስዋናው ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች እ.ኤ.አ. በ2016 ከህጻናት መንደሮች ወደ አደራ እንክብካቤ (foster care) ያደረገውን ሽግግር እንደሚከተለው ይገልጹታል።
ዋናው ተግባር፡- በሽግግሩ ወቅት ለህጻናት አስተማማኝ መሰረት መሆን
በሺዎች የሚቆጠሩ የኤስ ኦ ኤስ መንደር ህጻናት ከኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊዎች ባገኙት ጥራት ያለው የዕድሜ ልክ እንክብካቤ የተነሳ በትምህርታቸው እና በህይወታቸው ስኬታማ ለመሆን ችለዋል።
አሁን ደግሞ ህጻናት ከኤስ ኦ ኤስ መንደር ወጥተው በአካባቢው ባህል ውስጥ ወደ መኖር በሚያደርጉት ለስጋት አጋላጭ የሆነ ሂደት በሁሉም ምዕራፍ ውስጥ አስተማማኝ የሆነ ግንኙነት እንዳላቸው እንዲሰማቸው የእናንተ ዕውቀት እና ልምድ እንዲያግዛቸው ግድ ይላል። ህጻናት የመተማመን/የደህንነት ስሜት ሊሰማቸው የሚችለው የኤስ ኦ ኤስ አሳዳጊዎቻቸው በሚገባ ዝግጅት ያደረጉ ከሆነ እና በማህበረሰቡ ውስጥ ለመኖር ምቾት እና ዝግጁነት የሚሰማቸው ከሆነ ብቻ ነው።